Get Mystery Box with random crypto!

ጦብያን በታሪክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiainhistory — ጦብያን በታሪክ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiainhistory — ጦብያን በታሪክ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopiainhistory
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 2.50K
የሰርጥ መግለጫ

ኖር
— ስለ ኢትዮጵያ የማነባቸውን /አልፎ አልፎም ጉዞዎቼን/ እዚህ አስቀምጣለሁ ደስ ካላችሁ አንብቡ። ሌሎች ከኢትዮጵያ ያልሆኑ ነገሮችን ባጋራም አብዛኛው ከወዲህ ነው፡፡
Predominantly (but not strictly) about Ethiopia and Ethiopian history.
@hewaniye

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 20:39:19 አንዳንዶቻችሁ ኢንሳይክሎፔዲያ ኤትዮፒካን የት ልታገኙ እንደምትችሉ እየጠየቃችሁኝ ነው: ይኸው—ከዚህ ማውረድ ትችላላችሁ።

https://www.aai.uni-hamburg.de/en/ethiostudies/research/encyclopaedia.html

On second thought: ፕሪቪው ብቻ ናት ለካ። ይቅርታ ይቅርታ። በቃ የምትፈልጉት በግል ጻፉልኝ እና እልክላችኋለሁ።
417 viewsedited  17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 12:05:38 የፖለቲካ እና ጦር ተሿሚዎች

‘አጋፋሪ፡ አጋፋሪ ከዘበኞች ጋር በመሆን በጌታው ላይ ማንም እንዳይነሳ፣ ከእልፍኝ አስከልካይ ጋር በመሆን ደግሞ የጌታውን እና ቤተሰቡን ደኅንነት ይጠብቃል። ዋና ሥራው እስረኞችን መጠበቅ፣ አዳራሽ ውስጥ ነገሮችን መከታተል እና ቤት ውስጥ ያለውን ሕግ እና ደምብ ማስጠበቅ ነበር። የቤት ውስጥ ባሪያዎች እና ሰራተኛውች ከውጭ ጋር የሚያደርጉትንም ግንኙነት ይከታተላል።

ጌታው ከቦታ ወደ ቦታ እየሄደ ከሆነ እና ችሎት የሚቆም ከሆነ አጋፋሪው በጌታው ፈንታ ሰላምታ ይሰጣል፣ ለተሰበሰበውም ስለ ጌታው ቸርነት፣ ፈሪሃ እግዜር እና ፍትሕ አዋቂነት ገለጻ ይሰጣል። አጋፋሪው የጌታውን ልብስ፣ ነጋሪቶች እና ሌሎች ሹማምንትንም ሁኔታ ይከታተላል። በጉዞ ላይ የድንኳን አተካከልንም እሱ ይቆጣጠራል። ደስታ የሚባለው እና የንጉሠነገሥቱ የሆነው ቀይ ድንኳን ሲተከል በዘመቻ ጉዞ ላይ ያለው ጦር መቆም እንዳለበት ምልክት ስለሆነ ወዲያውኑ ነጫጭ እና ጥቋቁር ድንኳኖች ይተከላሉ። እያንዳንዳቸው የሹማምንትን ሥልጣን እና ኃይል ያሳያሉ። ነጭ ድንኳኖች የአጋፋሪ፣ የብላቴን ጌታ እና የጥቃቅን ብላቴን ጌታዎች ናቸው። የውስጥ አሽከር አለቃ እና ረዳቱ አዛዥ ጥቋቁር ድንኳኖችን ይተክላሉ።

የአጋፋሪው ሌላ ዋና ሥራ ከብላቴን ጌታው እና ከጥቃቅን ብላቴን ጌታው ጋር በመሆን አዳዲስ ጨዋ ወታደሮችን እድገት እና ሥልጠና መከታተል ነበር። ብላቴን ጌታ የሚባል ሹመት የተሰጠው ሰው ዲፕሎማሲያዊ ብቃት ያለው፣ መካከለኛ እድሜ ላይ ያለ፣ ብዙ መሬት የተሰጠው እና የሐር ልብስ የሚለብስ በየስብሰባዎች የሚገኝ ሲሆን የጌታውን ወጣት ጦረኞች እንክብካቤ ይቆጣጠራል። ረዳቱ እኚህን ጨዋዎች የቤተመንግሥት ጸባይ ያስተምራቸዋል።’

ፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት
ገጽ 177—78
513 views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:46:40 ‘አዳኞች ከአደን ሲመለሱ ቅድሚያ ለተገደሉት እንስሳት ተስካር መጣል ይገባቸዋል። ያለበለዚያ እርም ይሆን እና ገዳዮቹ ለምጻም ይሆናሉ ተብሎ ይፈራል። በአደን ከ40 ቀን በላይ ከቆዩ ግን መልዕክተኞች ወደአካባቢያቸው ተልከው በእነሱ ፈንታ ሕዝብ (ቤተሰባቸው) የተስካር ድግስ እንዲደግስ ይነግራሉ።

ከአደን ተመልሰው ግዳያቸውን ከጌቶቻቸው፣ አባቶች፣ ዘመዶች ፊት ከጣሉ እና ካሳዩ በኋላ የገዳዮች ቤተሰቦች እና ሚስቶች የተለያዩ ዘፈኖችን ይዘፍናሉ። የገዳይ ሚስት እንደባሏ አረንጓዴ አቡቅደዲ እንድትለብስ ይፈቀድላታል — አንድነታቸውን ለማሳየት ነው። ውኃ ልትቀዳ ስትሄድም ቅድሚያ ይሰጣታል።

ስለ አዳኞቹ ከሚዘፈኑት የተለያዩ ዘፈኖች መካከል አንዳንዶቹ ስድቦችም ነበሩ። ትንሽ ዝሆን (ኤልሞሌ) ገድሎ ለመፎከር የሚዳዳው እንዲህ ይባልበታል፡

«እንግዲህ ጀመረው ሊቀመጥ ሊነሣ
አንድ አልሞሌ ገድሏል ያውም ለሠላሳ»

በረኸኛ እና በለስ የሚቀናው ከሃምሳ እስከ መቶ የሚገድል እንዲህ ይባልለታል፡

«አንድ ግዳይ ነወይ አወይ የልጅ ነገር
ሁለት ግዳይ ነወይ አውይ የልጅ ነገር
አሻ ዝም በሉ ባለሃምሳው ይናገር»

የአዳኝ ሚስቶች፣ ቅምጦች እና ፍቅረኞች እርስ በርሳቸውም ይቀላለዳሉ፣ ይሞጋገሳሉ።

«የገዳይ ወዳጅ ታስታውቃለች
አፋፍ ላይ ቆማ በለው ትላለች

የገዳይ አጋዳይ ሆኖ መጥቶልሻል
ግባ በየው እንጂ እደጅ ያመሻል

የገዳይ አጋዳይ ሆኖ ከመመለስ
አልነበረህም ወይ ልግዋምና ፈረስ

አንቺ ምን ቸገረሽ የገዳይ ውሽማ
አንተርሶሽ ያድራል አዶ እንደ ብርኩማ

የገዳይ ገረድ ታስታውቃለች
ታልቀዳች አይቀዱ ውሃ እንኳ ብትወርድ

እስቲ እንዳሻው በአቦ እንዳለ ያርገኝ
በቀጭኔ ደጋን የሚያስነድፈኝ

ምነዋ ብኮራ ምነው ቢጀንነኝ
ቀጭኔ ተጋዳይ ያገኘሁ እኔ ነኝ

ዝሆን ብትገድል በጣም ደስ አለኝ
አውራሪስ ብትገድል በጣም ደስ አለኝ
ጎሽ ኮረምቱ ገድለህ ኮልባ ላክልኝ» (ኮልባ ጥቁር የጆሮ ጌጥ ነው)’

ፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት
ገጽ 171—173
543 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:47:28 ‘በቡድን የሚሄዱት አዳኞች ሁሉም በለስ እስኪቀናቸው ድረስ ጠብቀው ይመለሳሉ። በለስ ያልቀናቸው ባዶ እጃቸውን ከመመለስ በረሃ መሞትን መርጠው እዛው ይቀራሉ። ገዳዩ የእንስሳውን ጭራ ከቆረጠ በኋላ እንዲፎክር ይፈቀድለታል።

«ዘራፍ ዘራፍ ዘራፍ
እኔ የእገሌ አሽከር
የእንትን ገዳይ. . .»

የፖለቲካ እና ጦር ምርጫውን እንዲህ ከገለጸ በኋላ ጓደኞቹ አዶ ወሽባ ይዘፍናሉ፡

«አዶ ወሽባዬ አዶ ወሽባ
አዶ ወሽባዬ አዶ ወሽባ
እንዲያ እንዲያ ሲል ነው ግዳይ. . .»+

«እረ አዶ በሉለት
ይለይለት»

አዶ የዝሆን እግር ሲሆን ከእሱ የሚሠራ ጌጥንም ይወክላል። ወሸባ ደግሞ በቆላማ አካባቢ አለች የምትባል መንፈስ መጥሪያ ነው።

ይሄም ይዘፈናል፡

«ያስፈልጋል ዋጋ ለደጋጋ
ያስፈልጋል ብርቱ ለጎሽ ኮረምቱ»
(ደጋጋ ትልቅ ዝሆን ነው)

አዳኞች ጸጉራቸውን ያሳድጉና በአደን በሚቆዩበት ጊዜ እንዲንጨባረር ያደርጉታል። ጥላ መልክ ያለው ክብ እንዲሆንላቸው ለስላሳ ጸጉር ያላቸው ቅቤ ይቀቡታል። አዳኞች እና ሴቶች ብቻ ነበሩ ጸጉራቸውን ቅቤ መቀባት የሚፈቀድላቸው።*

ፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት
ገጽ 167–168

+ ጉሮ ወሸባዬ ጉሮ ወሸባ እያልን የምንዘፍነው ከአደን ዘፈን የተረከብነው መሆኑ ነው።

* የአጼ ኃይለሥላሴ ሥርዓተ ንግሥ ላይ የነበሩ እንግሊዛውያን መኳንንቱ ቅቤ ተቀብተው መጡ ብለው ጽፈው አይቻለሁ። እኚህ አዳኞች ነበሩ ማለት ነው።
396 viewsedited  05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:04:12 ማስታወቂያ፡ ነገ ዋሊያ ቡክስ (ቱሪስት ሆቴል ጀርባ) ከሰዓት (10:00 — 12:00) ላይ በጋሽ እጓለ ገብረዮሐንስ የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ ላይ ውይይት አለ።
516 views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 12:21:48 ‘ባላምባራስ ብርሃነሥላሴ ይገረሙ የአደን ትውስታቸውን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፡ «አባት ወይንም ጌታችንን ለምነን አስፈቅደን ነበር አደን የምንሄደው። እሺ እንዲሉን ደጅ እንጠናለን፣ አማላጅ እንልካለን። አትሄዱም ከተባልን ለመጥፋት እንዘጋጃለን፣ እሺ ካሉን ግን ወዲያውኑ ዝግጅት እንጀምራለን። የቆላውን ሀገር አዳኞችንም ታድያ እንለምን ነበር አብረናቸው እንድንሄድ።»

ጌቶች እና የበላዮች ትንንሾቹን አደን መሄድ የሚፈልጉትን ትዕግስት እና ታማኝነት ለማስተማር ብለው ረጅም ጊዜ እሺ ሳይሏቸው ይቆዩ ነበር። ከዚያ ግን አንዴ እሺ ካሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ በማዘጋጀት ያግዟቸዋል። በሶ፣ በርበሬ፣ ጨው፣ ኮሶ፣ ቢላዋዎች፣ መጥረቢያ፣ የውሃ መያዣ፣ መጠጫ፣ ጀበርናዎች ወዘተ ይዘጋጃሉ። አዳኞቹ ልብሳቸው ያዘጋጃሉ፣ ጠመንጃቸውን ይወለውላሉ፣ አቅም ያላቸው ደግሞ ጥይት ይገዛሉ።

የአዳኞችን ምግብ እና ዝግጅት መከታተል የእናቶች፣ እህቶች፣ ሚስቶች፣ ፍቅረኞች፣ ባሪያዎች እና የቤተሰብ አባላት ሥራ ነበር። ወንድ ቤተሰቦች ለአዳዲሶቹ አዳኞች የመጀመሪያ መሣሪያዎቻቸውን ይሰጧቸዋል። በምግብ በኩል ሁለት አይነት የደረቀ ዳቦ ይዘጋጃል። ይሄ ሁሉ ሲካሄድ ጋሻ ለረጅም ጊዜ ተሰቅሎ ያለበት ቤት ባለቤቱ ከእነዚህ አዳኞች ጋር እንዲሄድ ለማነሳሳት (ለመስደብ) እንዲህ ተብሎ ይገጠምበታል፡

«ባትዋጋ እንኳን በል እንገፍ እንገፍ፥
የአባትህ ጋሻ ትህዋኑ ይርገፍ»’

ፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት
ገጽ 161–162
524 views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 14:38:05
572 views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 14:37:58 ደብረ ሊባኖስ (የሸዋው) ገዳም መቼ እንደተመሠረተ እና ማን እንደመሠረተው ቀድሞ ለሚጽፍልኝ የIan Campbellን The Massacre of Debre Libanos, Ethiopia 1937 + በአንድ ወዳጄ የተሠሩ ቡክማርኮችን እሰጣለሁ።

መጽሐፉ
551 views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 12:59:23 ሰሞኑን ስለጦረኞች፣ ፈረሰኞች እና አዳኞች (በአጠቃላይ ጨዋዎች) ግጥሞች አይተን የለ? እኚህ ሴት (አዝማሪ) በወልዲያ በ1965 እ.ኤ.አ ተቀርጸው ግጥሞቹ ተመሳሳይ ናቸው

ለምሳሌ፡ ፈረሱን ገደለው ቼ ብሎ ቼ ብሎ
ከመቃብር በላይ ስም ይቀራል ብሎ

— ሹፉ



555 viewsedited  09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:08:26 ‘ሕፃናት አደን የሚለማመዱት በወንጭፍ እና በጦር ሲሆን ከአስር ዓመት ጀምሮ ያሉት ደግሞ መሣሪያ እየተሰጣቸው የሚበሉ እንስሳትን — ማለትም እነቆቅ፣ ጅግራን፣ ሶረኒን ማደን ይለማመዳሉ። ድፋርሳ፣ ድክድክ፣ አጋዘን፣ ቀጭኔ፣ ድኩላዎችንም እያደኑ ይመገባሉ። ረሃብ እና ድርቅ በሚመጡበት ጊዜ እነዚህን እንስሳት እያደኑ መመገብ የተለመደ ነበር።

በአደን ላይ ያሉ ጦረኞች ደክዬ እና ሰጎኖች የጦር ውርወራ መለማመጃዎቻቸው ነበሩ። የሰጎን እንቁላሎች የአብያተ ክርስቲያንን እና ቤቶችን ጣሪያዎች ያስጌጣሉ፤ ጦረኞች እና አዳኞች ደግሞ
የሰገንን ላባ ወይንም ሶራን ይጌጡበታል።

በቆላማ አካባቢ አደን ማደን በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ዱር በሚባሉ ሥፍራዎች እየሄዱ ማደን የድፍረት መለማመጃዎች ነበር። ለዚህም ነው እንዲህ ተብሎ የሚገጠመው፡

«ዱብ ዱብ ይላል እንደበረዶ
በልጅነቱ በረሃ ለምዶ»

እጅግ አስቸጋሪ ክልሎች እየገቡ ማደን ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ፈይዳው ትልቅ ነበር።

«ቢገድልም ገደለ ባይገድልም ገደለ
እበረሃ ወርዶ ጦም ውሎ ካደረ»፣

«መናኝና አዳኝ አብረው ገሰገሱ
አዳኝም ለግዳይ መናኝም ለነፍሱ»።’

ፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት
ገጽ 159—160
531 viewsedited  08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ