Get Mystery Box with random crypto!

ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ለማቋቋም የሚያስችለው ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል፡፡ | Tikvah-University

ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ለማቋቋም የሚያስችለው ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍለው መማር የማይችሉ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚያገል ነው የሚል ስጋት በምክር ቤቱ አባላት ተነስቷል።

የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበረሰብ አገልግሎት፣ የፕሬዝዳንቶች ሹመት፣ የኦዲት ስርዓት እና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከቱ ደንብና መመሪያዎች ሊዘጋጁ እንደሚገባ አባላቱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የአዋጁን ፋይዳ ያብራሩት በምክር ቤቱ የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ፤ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ተማሪዎች ጫና እንዳይኖርባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በአራት ተቃውሞ እና በ13 ድምጸ ተአቅቦ አዋጅ ቁጥር 1294/2015 ሆኖ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል፡፡

@tikvahuniversity