Get Mystery Box with random crypto!

Scholarships

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikuswere — Scholarships S
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikuswere — Scholarships
የሰርጥ አድራሻ: @tikuswere
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.51K
የሰርጥ መግለጫ

Information is power!
The greatest weapon to defeat powerity is Education!
🙏ሼር በማረግ ቻናሉን ይደግፉ🙏

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 20:57:35 ከ 300 በላይ የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት እጃቸው በመስጠት ነብሳቸዉን አትሪፈዋል ተብሏል።
ምንጭ ኢትዮ 360 እና የዉስጥ ምንጮቻችን
261 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:55:45 Tigray forces are advancing to South and Oromo forces are attacking in the west....
263 views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:54:25 DESSIE TO ADDIS Ababa
267 views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:53:42 Lalibela
266 views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 22:52:41 የስላቮች መናኸሪያ፣ የቫራንጊያሶች ወይም የቫይኪንጎች መናገሻይቱ፣ የኪየቫን-ሩስ መንደላቀቂያዋ ከተማ በ1240 ሞንጎሎች እንዳጠፏት ያክል አልሞተችም።የምስራቅ አዉሮጳዊቱ ባግዳድ መሆን አለመሆኗም አለየም።አልሞተችም ግን ጥልማሞት ሰፍሯባታል።የማስጠንቀቂያ ደዉል ጩኸት፣ የቦምብ፣ ሚሳዬል ነጎድጓድ የሞት ምፅአቱን ሰዓት በሰዓት ያረዳባታል


ዝብግኒየቭ ካዚሚየር  ብርዜንዚንስኪ ነብይ አልነበሩም።ግን በ20ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ፖላንድ ካፈራቻቸዉ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ካሳደገቻቸዉ ዕዉቅ የፖለቲካ ሳይንቲስቶች አንዱ ነበሩ።በ1997 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ነዉ) ታላቁ የቼዝ ገበታ The grand Chssboard) ባሉት መፅፈሐፍ «ሩሲያ ዩክሬንን ካጣች  ለሞስኮ ታላቅ መልከዓምድራዊ፣ስልታዊ፣ፖለቲካዊም ድቀት ነዉ» ብለዉ ነበር።እኛ የፖላንድ ዉልዱ፣የአሜሪካ ማደጎዉ የፖለቲካ ርዕሰ-ርዑሳን፣ ዲፕሎማትና አማካሪ፣ አሜሪካና ተባባሪዎችዋ የዓለምን ፖለቲካዊ ሥርዓት ሊያናጋ የሚችለዉን የዩሮ-ኤሽያን ቀዉስ ለመከላከል ሁነኛ መርሕ እንዲከተሉ መክረዉም ነበር። ሰዉ ናቸዉ።ግን ዛሬ የሆነዉን ከ25 ዓመት በፊት ተንብዩ እንበል ይሆን?አልንም-አላልን ዩክሬን በሩሲያ ቦምብ፣ሚሳዬል መድፍ-አዳፍኔ እየነደደች ነዉ።ጦርነት።የዋሽግተን፣ለንደን፣ ብራስልስ ዉግዘት እየናረ፣ እየጋመ እየመረረ፣ ጦር መሳሪያ፣ ወታደርና ገንዘብ ወደ ዩክሬንና ጎረቤቶችዋ እየጎረፈ ነዉ።ከዚያስ? ላፍታ እንቀጥል።

በ1994 ሰዉ በገፍና ግፍ የሚረሸን፣ የሚያልቅ፣ የሚሰደድባት ኪጋሊ ነበረች ሩዋንዳ-አፍሪቃ።ከ1995 እስከ ጀምሮ ሳርዬቮ ቀጠለች።በ1995 ሰሬብሬንትሳ ላይ የቦስኒያ ሙስሊም አዋቂ-ወጣት ወንዶች ከየሚስት፣እናት እሕቶቻቸዉ እየተነጠሉ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጦር ሠፈር ጭምር እንደአዉሬ እየታደኑ ተረሸኑ።

ከ8ሺሕ በላይ ወንዶች ሲረሸኑ የዓለም አቀፉን ድርጅት ሰማያዊ መለዮ ያጠለቁ፣ የኔዘርላንድስ ወታደሮች የአዉሮጳ-አሜሪካን ዘመናይ ጠመንጃ ታቅፈዉ ይመለከቱ ነበር።ሰሬብሬንትሳ አዉሮጳ ናት። የንስ ሽቶልተንበርግ ኔዘርላንዳዊ ናቸዉ።የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ዋና ፀሐፊ።ባለፈዉ ሮብ-ለሐሙስ አጥቢያ ዩክሬንላይ የሆነዉ ለአዉሮጳ ያለፈ «ታሪክ ነዉ ብለን ነበር» አሉ።

በ1990ዎቹ መጀመሪያ ሞቃዲሾ፣ በ1997  ግሮዝኒ ጠፍታለች።በ2000 ካንዳሐር፣ በ2003 ባግዳድ፣በ2011 ትሪፖሊ፣ በ2012 አሌፖ፣ በ2014 ክሪሚያ፣በ2015 ሰነዓ፣ በ2020 አክሱም፣ ዝርዝሩ ብዙ ነዉ።ዘንድሮ ኪየቭ ከዝርዝሩ መቀየጧ ይሆን? አናዉቅም።

ዩክሬንን የወረረዉ የሩሲያ ጦር ቃል አቀባይ ኢጎር ኮናሼንኮቭ እንዳሉት ግን ኪየቭ ባትሆን ሌሎች የዩክሬን ከተማና አካባቢዎች እየወደሙ ነዉ።በሩሲያና በተባባሪዎቹ ጦር እጅ ወድቀዋልም።

«የሉሐንስክ ሪፐብሊክ ኃይላት በሩሲያ ጦር ኃይል ድጋፍ በከፈቱት ጥቃት ኽቮሮስትያንካ፣ ሱኻኖቭስካ፣ አርትዮም ተቆጣጥረዋል።የሉሐንስክ ጦር ኃይል ክፍለ ጦሮች 19ኝ ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዞ ኖቫዲርን ይዟል።ቮልኖቫክሕ ሙሉ በሙሉ ተከባለች።የሩሲያ ጦር ቤርድያንስክንና ኢነርጎዳርን ከተሞችን ተቆጣጥሯል።»

To be continued
2.1K views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 19:54:00 የሚባረከው ጦርነት ... የሀበሾችና የራሺያዊያን ወግ ..

ራሺያ ዩክሬይንን ነው የወረረችበት ዋነኛው ምክንያት .. ኔቶ ከሶቬት ህብረት የተገነጠሉ ሀገራትን አባል ማድረግ አይችልም የሚለው ውል አልተከበረም በተደጋጋሚም ተጥሷል ብላ ነው።

ባለፉት አመታት የተፈጠረው የክሬሚያ ቀውስ ሆነ ሌሎች ቀጠናዊ ቀውሶችንም አረሳንም። ከጀርባ ያሉት የዘመናት የፖለቲካ መቃቃሮች እንደተጠበቁ ሆነው።

ራሻያዊያን ትናንት ማታ የሞስኮ አደባባይን ሞልተው ጦርነቱና ወረራው ይቁም ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል። በሀበሾች አጠራር .. ጦርነት ያልደገፉ ሰዎች እንደሚጠሩት .."ጁንታ" .. ሆነዋል።

አስቡት ይህ የእርስ በርስ ጦርነት አይደለም። የሁለት ሀገራት ጦርነት ነው .. መነሻውም ከበላይነት ጥቅምን ከማስከበር ፣ ደህንነትን ከማረጋገጥ አንፃር ልናየው እንችላለን።

ይህ ግን በሀገራቸው ለማይደራደሩት ራሺያዊያን ምክንያት አልሆነም። እጅግ አፋኝና ርህራሄ አልባ የሆነውን የፑቲን አስተዳደርን አደባባይ ወጥተው ጦርነቱን አቁም ሲሉ ጠይቀዋል። ሰው ስትሆን ከጥቅምህ ከፍላጎትህ ከምኞትህ በላይ .. ለሰውና ለሰብዓዊነት ትቆማለህ .. ታስባለህ።

አይደለም ሀገርህ ጎረቤትህ እንዲረበሽ እንዲወረር አትፈልግም። ጦርነትን አደባባይ ወጥተህ መቃወም ባትችል እንኳን ጦርነትን ግን ደግፈህ አደባባይ አትወጣም። ራሺያዊያን ግን አደባባይ ወጥተው ጦርነትን አንፈልግም ብለዋል።

ከሁለት አመት በፊት ትግራይ ላይ ጦርነት ሲከፈት ... ዘመቻውን አለመደገፍ ብቻ .."በጅምላ ጁንታ" .. ተብሎ ያሰድብ ነበር። አረ ጦርነቱ በውይይት ይፈታ ካልክ .."ስንት ተከፍሎሃል ጁንታው"? .. ብለው ይጠይቁ ነበር።

ጦርነት በፍቅር በልባዊነት የተደገፈባት ሀገር .. እሱንም የእርስ በርስ ጦርነት እንደ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በምድር ላይ ያለ ሀገር የለምም .. ተፈልጎም አይገኝም።

ሌላውን ተውት የሀይማኖት አባቶች ፣ ምሁራን ፣እናቶች ፣አባቶች፣ ህፃናት እራሱ አልቀሩም .. አደባባይ ሲወጡ። ዳግማዊ አድዋ ተብሎ ከውጭ ወረራ ጋር ጦርነቱን አያይዘው ንፁሃን እንዲያልቁ የእራሳቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል።

የትግራይን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ለገባው ለወራሪው የኤርትራ ጦር የሰገዱ ያጨበጨቡ ደግሞ ሚሊዮኖች ናቸው።

ይህ አረመኔያዊነት ነው ... ጉዳዩ የፖለቲካ እንደሆነ እየታወቀ ሌላ ነገር ተደርጎ እንዲቀርብ እንዲታሰብ የተደረገበት መንገድ ማንም ሊረሳው የማይችልና የትግራይ ህዝብን ከፍተኛ መስዕዋትነት ያስከፈለ ነው።

የኢትዮጵያ ታሪክ በእንደዚህ አይነት የጠቆሩ ታሪኮች የጨቀየ ነው። ባንዳነት አኩሪና የሚያስመሰግን ገድል ነው። ገዳይነት የሚያስኮፍስ አለፍ ሲልም .."አሳ በለው" .. ተብሎ በዘፈን የሚገለፅ አኩሪ ጀብድ ነው። ጦርነት ቂም በቀል የክብር ጉዳይ ተደረጎ ይወሰዳል።

ይህ አስተሳሰብ በዚህ ዘመን ሁሉንም አደባባይ ላይ ያሰባሰበና አንድ ያደረገ መሆኑን ስታውቅ .. በኢትዮጵያም በህዝቦቿም ተስፋ ትቆርጣለህ። ተጋሩዎች ከጦርነቱ በላይ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰባቸውና እየደረሰባቸው ያለው በደሎች ነፃ ትግራይን እንዲመሰርቱና እንዲያስቡ መንገድ ከፍቷል።

Finfinne Times
1.7K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 13:52:53 የሩሲያ ቢሊየነሮች ከ24 ባልበለጡ ሰዓታት ውስጥ 39 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማጣታቸው ተገለጸ!(አል አይን)

ጦርነቱ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮፓ ምድር ከፍተኛ የሆነ የገበያ ውድቀት እንዳያስከትል ተሰግቷል

ጄኔዲ ቲምቼንኮን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ የሩሲያ ቢሊየነሮች ለተለያዩ የሃብት እገዳ እርምጃዎች ተዳርገዋል

የሩሲያ ቢሊየነሮች የዩክሬንን ጦርነት ተከትሎ ከ24 ባልበለጡ ሰዓታት ውስጥ ከ39 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማጣታቸው ተገለጸ፡፡

ሩሲያውያኑ ቱጃሮች ከፍተኛ ኪሳራ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ቢጠበቅም በዚህ ደረጃ የከፋ ኪሳራ ያጋጥማቸዋል ተብሎ አልተገመተም ነበር፡፡

ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ሩሲያ በአክሲዮን ገበያ /MOEX/ የነበራት የግብይት ምጣኔ በ33 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ ይህም በስቶክ ገበያ ታሪክ የከፉ ናቸው ከተባሉ ውድቀቶች 5ኛው ሆኖ ተመዝግቧል። ከፈረንጆቹ 1987 ወዲህ የታየ ከፍተኛ የገበያ ማሽቆልቆልም ነው የተባለው፡፡

ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የተጣሉና በመጣል ላይ ያሉ ማዕቀቦች በአውሮፓ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ምጣኔ ሃብታዊ ውድቀትን እንዳያስከትሉ ተሰግቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃይል፣ በትራንስፖርት እና በመሠረተ ልማት ሀብት ላይ ኢንቨስትመንቶችን በማድረግ ላይ የተሰማራው ቮልጋ የተሰኘ የግል የኢንቨስትመንት ቡድን ባለቤት የሆኑት ሩሲያዊው ቢሊየነር ጄኔዲ ቲምቼንኮን ጨምሮ በሌሎችየሩሲያ ቱጃሮች ላይ ቀላል የማይባል የሃብት እገዳ ተጥሏል፡፡

ከግዙፉ የነዳጅ እና ጋዝ ቋሚ የተቀናጁ ኩባንያዎች አንዱ የሆኑነውን የLUKOIL ሊቀመንበር ቫጊት አሌኬሮቭ ሃብት በአንድ ቀን ውስጥ በአንድ ሶስተኛ ቀንሷልም ነው የተባለው፡፡

እንደ ብሉምበርግ ኢንዴክስ ከሆነ የቫጊት አሌኬሮቭ ሀብት በአንድ ቀን ውስጥ በ6.2 ቢሊዮን ዶላር ገደማ በመቀነስ ወደ 13 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ብሏል፡፡

የሞስኮ የነዳጅ አምራችነት ድርሻ በትናትናው እለት ቀን በ33 በመቶ ገደማ ማሽቆልቆሉም ነው የተገለጸው፡፡

የብረታ ብረት አምራች የሆነውን ሴቨርስታል ሊቀመንበር የሆኑት አሌክሲ ሞርዳሾቭ 4.2 ቢሊዮን ዶላር ማጣታቸውን ተከለትሎ ሀብታቸው ወደ 23 ቢሊዮን ዶላር መውረዱም ተነግሯል፡፡

በሌላ በኩል ከ50 በላይ በሚሆኑ ሀገራት ውስጥ የፋይናንስ አገልግሎት የሚሰጥ ዓለም አቀፍ የኖሪልስክ ኒኬል (Norilsk Nickel) ኩባንያ ፕሬዝዳንትና የወቅቱ ቁንጮ ሩሲያዊ ቱጃር ቭላድሚር ፖታኒን 3 ቢሊዮን ዶላር ማጣታቸውንም ዘገባዎች አመልክተዋል።
1.3K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 16:20:45 ~አውሮፓ ትልቁን የበቆሎና ስንዴ ምርት የሚያገኘው ከዩክሬን ነው። ዩክሬን 40% ንግዷ ከአውሮፓ ጋር ነው።
~በአውሮፓ የተፈጥሮ ጋዝ በ30% ጨምሯል። ሩሲያ ከአለም ሁለተኛዋ የተፈጥሮ ጋዝ አቅራቢ አገር ነች።
~በቆሎና ስንዴ ዋጋ በ6% ጨምሯል። ዩክሬን የአለማችንን 16% የስንዴ ገበያ ትሸፍናለች።
~የፋይናንሻል ገበያው በአለም በአማካይ 4% አሽቆልቁሏል።
~ነዳጅ ከ2014 እኤአ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ቀን ወደ 104$ በበርሜል ገብቷል።
~ጀርመን የሩሲያን ጋዝ ካልማገች ፍሪዝ ታደርጋለች።
~ምዕራቡ አለም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ትልቁ የጦርነት ስጋት ውስጥ ገብታለች። ጦርነቱ ትልቅ ስጋት የሆነው አገራቱ የኒውክለር ባለቤቶች መሆናቸውና በቀላሉ መጠፋፋት የሚችሉ መሆናቸው ነው።

Wonde Berhanu kabaw
1.1K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 16:20:20 የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ኔቶ ዛሬ ሐሙስ ካደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ ዩክሬን እና ሩሲያ በሚዋሰኑበት ምሥራቃዊ ግዛት የምድር፣ የባህር እና የአየር ኃይሉን ለማጠናከር መወሰኑን አስታወቀ።

የኔቶ አምባሳደሮች ባወጡት መግለጫ "በጥምረቱ ምሥራቃዊ ክፍል ተጨማሪ የምድር፣ የአየር እና የባህር መከላከያ ኃይል ልናሰማራ ነው" ብለዋል። የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ የንስ ስቶልተንበርግ በምሥራቃዊ አውሮፓ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን የመከላከያ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኑን ለጋዜጠኞች አረጋግጠዋል።

የድርጅቱ አባላት የሆኑት የምስራቅ አዉሮጳ ሐገራት ኢስቶኒያ፣ ላቲቪያ፣ ሉቱኒያ እና ፖላንድ የሰሜን የግዛት አንድነት፣ የፖለቲካ ነጻነት ወይም ጸጥታ አደጋ ውስጥ ሲወድቅ ሌላ ስብስባ እንዲጠራ ጠይቀዋል። ለግጭቱ ቅርበት ካላቸው አገራት አንዷ የሆነችው ሉቱኒያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጋለች።

የሩሲያ ወታደራዊ ሔሊኮፕተሮች በዛሬው ዕለት ከኪየቭ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ጎስቶሜል የተባለ የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት እንደተናገሩ ሬውተርስ ዘግቧል። ባለሥልጣናቱ እንዳሉት ከሩሲያ ሔሊኮፕተሮች መካከል ሶስቱን ዩክሬን መትታ ጥላለች።
የዩክሬን የድንበር ጥበቃ ባለሥልጣናት የሩሲያ ጦር ኪየቭ የተባለውን የዩክሬን ግዛት እና ዚይቶምይር የተባለውን ግዛት አገሪቱ ከቤላሩስ ከምትዋሰንበት ድንበር ጥሰው ለመግባት መሞከራቸውን ገልጸዋል።

የኪየቭ ከተማ ከንቲባ ቪታሊ ክሊትሽኮ ዓለም ከዩክሬን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። የቀድሞው ቦክሰኛ "በጦርነት ውስጥ ነን። ለአገራችን እየተዋጋን ነው። ነገር ግን የመላውን ዓለም እርዳታ እንፈልጋለን። በሩሲያ ላይ ጠንካራ ማዕቀብ መጣል አለበት" ብለዋል። በኪየቭ ከተማ ያለው ሁኔታ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ቢሆንም ከንቲባው በነዋሪዎች ዘንድ ሥጋት መኖሩን ግን አልሸሸጉም።
ፈረንሳይ ለዩክሬን የምትሰጠውን ድጋፍ እንደምታጠናክር አስታውቃለች። ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ "ሩሲያ በዩክሬን ላይ ጦርነት ካወጀች በኋላ" የፈረንሳይ የመከላከያ ምክር ቤትን መሰብሰባቸውን የኤሊዜ ቤተ-መንግሥት አስታውቋል። የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "ጦርነትን መምረጥ አስከፊ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ነው። ግዙፍ እና ከባድ ዋጋ በፍጥነት ያስከፍላል" ብለዋል።

ቱርክ "ኢ-ፍትኃዊ እና ሕገ-ወጥ" ያለችው ሩሲያ የጀመረችውን ወታደራዊ እርምጃ በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች። የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "ወታደራዊ ተልዕኮው ተቀባይነት የሌለው ነው ብለን እናምናለን" ያለ ሲሆን "የሩሲያ ፌዴሬሽን ይኸን ኢ-ፍትኃዊ እና ሕገ-ወጥ እርምጃ በአፋጣኝ እንድታቆም ጥሪ" አቅርቧል።

ሩሲያ በቱርክ ጎረቤት ዩክሬን ላይ ጥቃት ከከፈተች በኋላ ፕሬዝደንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን በዋና ከተማዋ አንካራ የጸጥታ ስብሰባ አካሒደዋል። የሩሲያ እርምጃ "የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት" ነው ከሚል ድምዳሜ የደረሰው ስብሰባ "ተቀባይነት የለውም" ማለቱን የፕሬዝደንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ይኸ ኩነት በፍጥነት የሚቀያየር ነው። ዶይቼ ቬለ ጉዳዩን በመከታተል አዳዲስ ዘገባዎችን ያቀርባል። ከምሽቱ አንድ ሰዓት የሚጀምረው የራዲዮ ሥርጭት በዚሁ ጉዳዮች ላይ ዘገባዎች ይኖሩታል።

https://p.dw.com/p/47WdQ?maca=amh-Facebook-dw
1.0K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 16:09:26
Belarus sided with Russia

-First ground Russian troops have landed in Ukraine via Belarus. (According to Aljazeera)

-Ukraine asks Turkey not to allow Russian Amy ships via Black Sea

-Ukrainian president calls on all citizens to defend their country
860 views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ