Get Mystery Box with random crypto!

#ECSOC የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ ቤት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ዳግም የተቀሰ | TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)

#ECSOC

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ ቤት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ዳግም የተቀሰቀሰው ትጥቅን ያካተተ ግጭትን እንዲረጋጋ እና የተጀመረው የሰላም ሂደት በአስቸኳይ እንዲቀጥል አበክሮ ጠይቋል።

ም/ቤቱ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል መልሶ ያገረሸው የትጥቅ ግጭት በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿጻ።

ከዚህ በፊት የተፈጠረው የትጥቅ ግጭት ተነግሮ የማያልቅ የሰው ልጅ ስቃይ እና ከፍተኛ መሰረተ ልማቶች መውደም ምክንያት መሆኑን ይታወቃል ያለው ም/ቤቱ አሁን ዳግም የተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት እንዲረጋጋና ግጭቱ እንዳይባባስ አፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ አሳስቧል።

በተጨማሪም ም/ቤቱ አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁሙ መከበር ለሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት ቀጣይነት እና ለሰላም ሂደቱ ስኬታማነት ወሳኝ እንደሆነ ገልጾ አለመግባባቶች በፖለቲካዊ ውይይት መፈታት እንዳለባቸው በጥብቅ እንደሚያምን ገልጿል።

ለዚህም የሰላም ማስፈን ሂደቱ በአስቸኳይ እንዲቀጥልና ሀገሪቱንና ዜጎቿን ከተጨማሪ ጥፋት ለመታደግ የሰላም ሂደቱ በቅን ልቦና እንዲካሄድ ምክር ቤቱ ጠይቋል።

የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግንዛቤ በማስገባት የአፍሪካ ህብረት (AU) የፌደራል መንግስትን እና ህወሃትን የማደራደር ሚናውን በእጥፍ በማሳደግ ሰላማዊ እልባት ላይ እንዲደረስ የበኩሉን እንዲወጣ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

የሰላም ማስፈን ሂደቱን አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ በማንኛውም መንገድ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት እና ዝግጁነትም በድጋሚ አረጋግጧል።