Get Mystery Box with random crypto!

' ውጤቱን አልቀበልም ' - ኦዲንጋ ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት አልቀበለም ብለዋል። ትላን | TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)

" ውጤቱን አልቀበልም " - ኦዲንጋ

ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት አልቀበለም ብለዋል።

ትላንትና ሰኞ የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን የኬንያን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዊልያን ሩቶ ማሸነፋቸውን ማሳወቁ አይዘነጋም።

በቦማስ በተደረገው ስነስርዓት ወቅት ጭራሽ በማዕከሉ ያልተገኙት የሩቶ ተፎካካሪ ኦዲንጋ እስከ ዛሬ ከሰዓት ድረስ ስለ ምርጫው ምንም ሳይሉ ቆይተዋል።

ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ የምርጫውን ውጤት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንደሌለውና እሳቸውም እንደማይቀበሉት አሳውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም ሰው እንዲረጋጋ እና ህግ እንዲያከብር አሳስበዋል።
@tikivah_ethiopiaa