Get Mystery Box with random crypto!

ልሣነ ጥበብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tibebe11 — ልሣነ ጥበብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tibebe11 — ልሣነ ጥበብ
የሰርጥ አድራሻ: @tibebe11
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.35K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ በተዋሕዶ እምነታችን ኪነ-ጥበብ ክፍል አባላት የተከፈተ መንፈሳዊ ቻናል ነው ለማንኛውም አስተያየት እነዚህን ይጠቀሙ
⤵️
@Mihret1221
@saramareyame
ወደ ዩቲዩብ ቻናላችን ይግቡ⤵️
https://www.youtube.com/channel/UCvxjRL2WW1qVbM8L1yoe6Cw
ወደ ፌስቡክ ገጻችን ይግቡ ⤵️
https://www.facebook.com/የተ

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-04 00:16:47 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?


ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
ዘማሪት አቦነሽ አድነው
ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ
እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር JOIN የሚለውን ይጫኑት
ይህን ይጫኑት ... ይህን ይጫኑት
.
█▓▒░        ◄JOIN◄░►JOIN       ▒▓█
█▓▒░         ►JOIN◄░►JOIN      ▒▓█
█▓▒░         ►JOIN◄░►JOIN      ▒▓█
█▓▒░        ►JOIN◄░►JOIN       ▒▓█
3.0K views21:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 17:59:41 "ልብ አብዝቶ የጸለየውን ያህል በዚህ መጠን ልብ ትሑት ይሆናል፡፡ ትሑት ቢሆን እንጂ ትሑት ካልሆነ የሚለምን፣ የሚማልድ የለም፡፡ ፈጣሪ ጽኑ፣ ክቡር፣ ትሑት፣ ኅዙን፣ ልቡና የጸለየውን ጸሎት አልቀበልም አይልምና፡፡

ልቡናም በመከራ ትሑት ካልሆነ ትዕቢትን መተው አይቻለውም፡፡ ትሕትና መከራን ያርቃልና፤ ሰው ትሑት በሆነ ጊዜ ይቅርታን ያገኛል፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር እንደተሰጠችው ያውቃል፡፡ ያድነኛል ብሎ በማመን ዕውቀት ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ሰው ረድኤተ እግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠችው ያወቀ እንደሆነ ያድነኛል ብሎ ያምናል፡፡ የድኅነት መገኛ እንደሆነች፣ የሃይማኖት መገኛ እንደሆነች፣ ከመከራ ማዕበል ሞገድ ከውስጧ የሚያድን ወደብ እንደሆነች፣ በመከራ ድንቁርና ላሉ ዕውቀታቸው እንደሆነች፣ የድኩማን መጠጊያ በመከራ ጊዜ የሚያርፉባት ክንፍ እንደሆነች፣ በጽኑ ደዌ ጊዜ የሚድኑባት ረድኤት እንደሆነች፣ በጭንቅ ጊዜ የሚያርፉባት የሕይወት ተክል እንደሆነች፣በጠላት ፊት የተቃጣ ፍላጻ እንሆነች ያውቃል፡፡

ማር ይስሐቅ

𝚓𝚘𝚒𝚗 @Gubaye_Afe_Werk
3.0K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 20:00:00 በኢትዮጵያ የተሰወሩ ፒራሚዶች ያሉበት ቦታ ታወቀ !



እነዚህ ፒራሚዶች እና ቤተ መቅደሶች የሚገለጡበት ዘመን ታወቀ


እውነት በኢትዮጵያ መሬት በሰማያዊ ሀይል ተቀብረው የሚገኙ ፒራሚዶች እና ቤተ መቅደሶች አሉ ? እንዴትስ ተሰሩ ?

ስለ እነዚህ ፒራሚዶችና ቤተመቅደሶች አስገራሚ ምስጢሮች


በቅዱሳን አባቶቻችን ስለተሰወረው ድንቅ መፅሐፍ


እነዚህን እና ሌሎች ሚስጢራትን ስለ ኢትዮጵያ ስውር ቤተ መቅደሶች እንዲሁም ፒራሚዶች ማወቅ ከፈለጉ በ Youtube ቻናላችን ሙሉ ትምህርቱን ማግኘት ትችላላቹ ከስር ያለውን Open የሚለውን ተጭነው ! እንዲሁም ሌሎች ድንቅ ፕሮግራሞችንም ማግኘት ይችላሉ በዛውም የ Youtube ቻናላችንንም Subscribe ያርጉ !




ይህን ይጫኑት ... ይህን ይጫኑት
.
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
3.1K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 10:36:58 #መጻጉዕ- የዐቢይ ጾም አራተኛ ሣምንት

በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡ «38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው» እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው "ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም" አለው። "ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ" ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ "የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ" እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡ "በሰንበት ኢየሱስ መጻጉዕን ተነሥ አልጋህን ተሸከም ባለው ጊዜ ቀኑ ሰንበት ነበረ፡፡ መጻጉዕም አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ገባ የእግዚአብሔር ልጅ በሰንበት ፈውሷልና "በሰንበት ድውያንን ፈወሰ የዕውራንንም ዓይኖች አበራ" እያለ 38 ዓመት በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዞ ሲማቅቅ የኖረውን መጻጉዕንና ሌሎቹን በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙትን ሕሙማን መፈወሱን በጠቅላላው ለምፅ ማንጻቱን፣ ዕውር ማብራቱን፣ አንካሶችን ማርታቱን፣ ልምሾዎችን ማዳኑን፣ አጋንንትን ማውጣቱን፣ ወዘተ እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ዕለቱና ሳምንቱ መጻጉዕ ተብሏል፡፡

ስለዚህም ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነዚህ ሁሉ ታሪኮች የመጻጉዕንና የሌሎቹን ሕሙማን ሁሉ ደኅንነት ታሪክ እንረዳለን፡፡ የሰንበቱም ስያሜ ልብ ወለድ አጠራር ሳይሆን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

#የዕለቱ_ምንባቦች፦
1ኛ. የቅ.ጳውሎስ መልእክት ወደ ገላ. 5÷1-26
2ኛ. የቅ. ያዕቆብ መልእክት 5÷14-20
3ኛ. የሐዋርያት ሥራ 3÷1-12

#የዕለቱ_ምስባክ፦
መዝ 4ዐ(41)÷3
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ።

(እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፡፡ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ፡፡) መዝ 4ዐ÷3 የሚለው ይሆናል፡፡

#የዕለቱ_የወንጌል፦
በዮሐንስ ወንጌል 5፥1-25 ድረስ ያለው ነው፡፡

ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታች ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡፡
2.7K views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 20:39:17
“እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።”

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
ምዕ 3፥10-11



ʝ𝖔𝖎𝖓 @Gubaye_Afe_Werk
2.4K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 18:45:22 "የቱንም ያህል ቅዱሳት መፃሕፍትን እናጥና በትእዛዛቱ መኖር ካልተቻለን እግዚአብሔርን ማወቅ አይቻልም። እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ እንጂ በሳይንስ ማወቅ አይቻልም። ብዙ የተማሩ ሰዎችና ፈላስፎች የእግዚአብሔርን መኖር ያምናሉ ነገር ግን እግዚአብሔርን አያውቁትም። እግዚአብሔር እንዳለ ማመን አንድ ነገር እግዚአብሔርን ማወቅ ሌላ ነገር ነው። አንድ ሰው እግዚአብሔርን ያወቀው በመንፈስ ቅዱስ ከሆነ ልቡናው በእግዚአብሔር ፍቅር ቀንና ሌሊት ይቃጠላል። ነፍሱም ምድራዊ ከሆነ አንዳች ነገር ጋር አትጣበቅም።"

አባ ኒቆን

𝚓𝚘𝚒𝚗 @Gubaye_Afe_Werk
2.5K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 11:30:37 "ጥበብ በአገራችን እንደ ራቀን መጽሐፍ በቅናሽ ዋጋ ፣ ሥጋ በጭማሪ ሲሸጥ ማየት በቂ ነው"።

በእንተ ጥበብ 2

ጥበብ አእምሮ ላይ የሚሰማን ደስ የሚል ጨዋታ ፣ ሰውን አታሎ መግባት ፣ ሁሉንም ላለማስቀየም እሺ ፣ እሺ ማለት አይደለም ። ጥበብ ፍትሕን መፈለግና ለእውነት ዋጋ መክፈል ነው ። ጥበብ እውነትን ያከበረ እንጂ የሠዋ ፍቅርን አትሻም ። ጥበብ ሞትን እያሰቡ ቅንነትን በየዕለቱ መጨመር ነው ። የትም ከፍታ ላይ ቢወጡ መውረድ ፣ ከመሬት በታች መሆን አይቀርም ። ያ ሁሉ ክብርና ዝና በሁለት ፊደል ይከተታል ። “ሞተ” በሚለው ይዘጋል ።

ጥበብ ፈራሽነትን እያሰቡ ገዳይነትን መጠየፍ ነው ። እርሱ ሞቶ እኔ አልቀርምና ። ጥበብ ጥበበኞች ነን ከሚሉት እጅግ የራቀች ፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር ባለበት ያደረች ናት ። ጥበብ በማስታወቂያ ኃይል የቆመች ሳትሆን የምትፈለግ ስውር እጅ ናት ። በዓለም ላይ ትልቁ ድንቁርና አዋቂ ነኝ ብሎ ማሰብ ነው ። ጥበበኛ ነን ሲሉ እጅግ መደንቆር ይከሰታል ።

ዓለም ተጠበብሁ ብላ በመጨረሻ የሠራችው እንኳን ሰውን ቅጠል የማያስቀረውን የኒውክለር አረር ነው ። ጥበብ አውቆ ትሑት በሚሆን ሰው ልብ ውስጥ አለች ። የጥበብ መቀመጫው ነፍስ እንጂ ግድግዳ አይደለም ። በግድግዳቸው ላይ ሥዕል ስለሰቀሉ ጥበበኛ ናቸው ማለት አይደለም ። ጥበብ ግን ለጥበብ ዋጋ አላት ። ጥበብ በአገራችን እንደ ራቀን መጽሐፍ በቅናሽ ዋጋ ፣ ሥጋ በጭማሪ ሲሸጥ ማየት በቂ ነው ። ጥበብ የከዳው ትላንትን ፣ ዛሬንና ነገን ያበላሻል ። ትላንት የሌላትን ዛሬ የሚፈጥሩ የጥበብ ጠላቶች ናቸው ። ዛሬ ትላንት ከሌላት ነገም የላትም ።

ኖላዊ
2.6K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-06 22:14:09 በኢትዮጵያ የተሰወሩ ፒራሚዶች ያሉበት ቦታ ታወቀ !



እነዚህ ፒራሚዶች እና ቤተ መቅደሶች የሚገለጡበት ዘመን ታወቀ


እውነት በኢትዮጵያ መሬት በሰማያዊ ሀይል ተቀብረው የሚገኙ ፒራሚዶች እና ቤተ መቅደሶች አሉ ? እንዴትስ ተሰሩ ?

ስለ እነዚህ ፒራሚዶችና ቤተመቅደሶች አስገራሚ ምስጢሮች


በቅዱሳን አባቶቻችን ስለተሰወረው ድንቅ መፅሐፍ


እነዚህን እና ሌሎች ሚስጢራትን ስለ ኢትዮጵያ ስውር ቤተ መቅደሶች እንዲሁም ፒራሚዶች ማወቅ ከፈለጉ በ Youtube ቻናላችን ሙሉ ትምህርቱን ማግኘት ትችላላቹ ከስር ያለውን Open የሚለውን ተጭነው ! እንዲሁም ሌሎች ድንቅ ፕሮግራሞችንም ማግኘት ይችላሉ በዛውም የ Youtube ቻናላችንንም Subscribe ያርጉ !




ይህን ይጫኑት ... ይህን ይጫኑት
.
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
2.4K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 23:24:10 "ነፍሴ የወደደችህ እረኛዬ ሆይ! የተቅበዘበዝሁ እንዳልሆን፥በጎችህን ወዴት እንደምታሰማራ ንገረኝ - መሓ ፩፤፯

“መንጋህን ሁሉ በትከሻህ የምትሸከም መልካሙ እረኛ ሆይ! በጎችህን በወዴት ታሰማራለህ?... የማሰማሪያህን ቦታ እባክህ አሳየኝ፣ የእረፍቱን ውኃ አስታውቀኝ፤ ወደለመለመው መስክ ምራኝ፤ እኔ የአንተ በግ ድምጽህን እሰማ ዘንድ በስሜ ጥራኝ፤ ጥሪህ የዘላለም ሕይወት በጎ ስጦታ ይሆነኝ ዘንድ። … የድህነት መሰማሪያን አገኝ ዘንድ፣ ወደሕይወት የሚገቡ ሁሉ ሊመገቡት ከሚገባው ከሰማያዊው ማዕድም እጠግብ ዘንድ {በጎችህን} የምትመግብበትን {የምታሰማራበትን} ቦታ አሳየኝ”

ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣
የመሓልየ መሓልይ ትርጓሜ
2.1K views20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 21:07:24 "ኑና በእግዚአብሔር ፊት ወድቀን በጽናት ለማልቀስ ጥረት እናድርግ ፣ ከርሱ ፊት ሆነን ዐይኖቻችንን በእንባ እንጋርድ ፣ የመንፈሳዊ መገለጥን ይሠጠን ዘንድ !!"

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

𝚓𝚘𝚒𝚗 @Gubaye_Afe_Werk
2.5K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ