Get Mystery Box with random crypto!

#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች 1፤ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ | Think Abyssinia

#ቲንክአቢሲኒያ_የመክሰስ_መረጃዎች

1፤ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ኅዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በማረፉ የተሰማኝ ኀዘን ከባድ ነው" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት የኅዘን መግለጫ። "ለሀገሩ በአጭር እድሜው ብዙ የሠራ ከያኒ ነው፤ ሀገር በተደፈረች ጊዜ ሕመሙን እየቻለ ግንባር ተገኝቶ ሠራዊቱን አጀግኗል፤ ሠልጣኞችን አበርትቷል፤ ነፍሱ በሰላም ትረፍ” ብለዋል።

2፤መንግስት የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ወደ ውጭ ሀገራት መላክ ጀመረ።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በ2011 ዓ.ም በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠኑ ባሙያዎችን ወደ መካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ ለመላክ ከተለያዩ አገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምት እየተደረገ መሆኑን በፓርለማው በተናገሩት መሰረት ወደ 180 ነርሶችና የተሽከርካሪ መካኒኮች ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስና ኔዘርላንድ መላካቸውን ዋዜማ የስራ ክሕሎት ሚኒስቴር ሀላፊዎችን ዋቢ አድርጋ ዘግባለች።

3፤ተቋርጦ የነበረው የቪዛ ማራዘምና የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት ተጀመረ።

ከሐምሌ 18/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው ቪዛቸዉ እና የመኖሪያ ፈቃዳቸው የሚፀናበት ጊዜ ከአንድ ወር በላይ ላለፈባቸው ግለሰቦች የቪዛ ማራዘምና የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት ከመስከረም 16 2015 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎቱን መስጠት መጀመሩን የኢፌዲሪ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል።

4፤የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤን የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ።

ጃፓናውያን የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ብሄራዊ የቀብር ስነ ስርዓት አከናውነዋል። በብሄራዊ የቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የሟች ባለቤት አኪ አቤን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሃዘንተኞች በቶክዮ መገኘታቸው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሌላ በኩል በጃፓን ለንጉሳውያን ቤተሰቦች ብቻ የሚደረገው ብሄራዊ የቀብር ስነ ስርዓት ቢያንስ 12 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ ወጪ ማስወጣቱ አነጋገሪ ሆኗል፡፡ 

5፤ስድስት የቀድሞ የፋሲል ከነማ ተጫዋቾች በክለቡ ላይ ቅሬታቸውን አሰሙ።

ፋሲል ከነማ በ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቁ ለተጫዋቾቹ የ10 ሚልየን ብር ሽልማት ለማበርከት ቃል ገብቶ በቅርቡ ለአብዛኛው የቡድኑ አባላት የገንዘብ ሽልማቱን ቢያበረክትም በያዝነው ዓመት ከክለቡ ጋር ለተለያዩ ስድስት ተጫዋቾች ይህ ሽልማት አለመፈፀሙ በተጫዋቾቹ ላይ ቅሬታ አስነስቷል። ክለቡ በበኩሉ የገንዘብ ሽልማቱ የተሰጠው ከ2015 በጀት ለዚህ ዓመት ከቡድኑ ጋር አብረው ለሚገኙ ተጫዋቾች የማነቃቂያ ሽልማት መሆኑን ገልጿል።

መልካም በአል
• @ThinkAbyssinia •