2022-06-09 18:03:40
የሐዋርያት ሥራና የእግዚአብሔር መልአክ (ክፍል 2)
ባለፈው ክፍል የክርስቶስን አምላክነትና አስተምህሮተ ሥላሴን የሚቃወሙ ወገኖች፥ በሐዋርያት ሥራ 7 ላይ ተንተርሰው ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ይገለጥ የነበረው መለኮታዊው የእግዚአብሔር መልአክ አለመሆኑን ለማሳየት የሚያነሷቸውን ተቃውሞዎች መመለስ ጀምረን ነበር።
የክፍሉን አውድና የሰማዕቱን የእስጢፋኖስን የንግግር አላማ ካየን በኋላ፥ የመጀመሪያውን ተቃውሞ (objection) ለመመለስ ሞክረናል። እርሱም "መልአክ" ወይንም በግሪክ "ἄγγελος/አንጌሎስ" የሚለው ቃል መልእክተኛ ማለት ሲሆን፥ የተላከ ማለት ብቻ እንደሆነና አንድ አካል በዚህ ስያሜ ስለተጠራ ብቻ ፍጡር መንፈስ እንዳልሆነ አይተናል። ቃሉ አሰራርን እንጂ ባህርይን የሚገልጽ ቃል ስላልሆነ፥ ለየትኛውም አይነት አካል ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። የተላከ መሆኑን ብቻ እንደሚያመለክት ተመልክተናል
በተጨማሪም ለምን እስጢፋኖስ ቃል በቃል "መልአኩ ክርስቶስ ነው" እንዳላለም ለማየት ሞክረናል።
ዛሬም እግዚአብሔር ቢፈቅድ፥ እንዴት እስጢፋኖስ ያ ለሙሴ የተገለጠለው መልአክ ክርስቶስ መሆኑን እንደመሰከረ ለመመልከት እንሞክራለን
እስጢፋኖስ በፊቱ ለነበሩት ካህናት ከአብርሃም አንስቶ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ነገር ከተናገረ በኋላ፥ ከሐዋ 7:20 አንስቶ ስለ ሙሴ ታሪክ መናገር ይጀምራል። ከተወለደ በኋላ የፈርዖን ልጅ እንዳነሳችው፥ የግብፆችን ጥበብ እንደተማረ፥ ነገር ግን ግብጻዊውን በመግደሉ ወደ ምድያም ምጻተኛ ሆኖ ለመኖር እንደሸሸ ተረከላቸው
ከዚያም፥ አርባ አመት ሲሞላው በሲና ተራራ በምድረ በዳ በቁጥቋጦው ውስጥ በእሳት ነበልባል መልአክ እንደተገለጠለት በቁ.30 ላይ ነገራቸው።
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ሐዋ 7:30 ሲተረጉሙት "የጌታ መልአክ ታየው" ቢሉም፥ ግሪኩ ግን "መልአክ ታየው" ነው የሚለው።
"Καὶ πληρωθέντων ἐτῶν τεσσεράκοντα ὤφθη αὐτῷ ἐν τῇ ἐρήμῳ τοῦ ὄρους Σινᾶ #ἄγγελος ἐν φλογὶ πυρὸς βάτου"
[Acts 7:30 Greek]
አዲሱ መደበኛ ትርጉምና ሌሎች ኢንግሊዘኛ ትርጉሞችም ከግሪኩ ጋር በሚስማማ መልኩ "መልአክ ታየው" ወይንም "an angel appeared to him" በማለት በትክክል ተርጉመውታል፦
“ከአርባ ዓመት በኋላ፣ በሲና ተራራ አካባቢ ባለው ምድረ በዳ፣ በሚነድ ቍጥቋጦ ነበልባል ውስጥ #መልአክ #ተገለጠለት።”
ሐዋርያት 7፥30 (አዲሱ መ.ት)
“After forty years had passed, an #angel #appeared to Moses in the flames of a burning bush in the desert near Mount Sinai.”
Acts 7:30 (NIV)
“And when forty years had gone by, there #appeared to him in the wilderness (desert) of Mount Sinai an #angel, in the flame of a burning bramblebush.”
Acts 7:30 (AMP)
“After 40 years had passed, an #angel #appeared to him in the desert of Mount Sinai, in the flame of a burning bush.”
Acts 7:30 (HCSB)
“When forty years had passed, an #angel #appeared to him in the flames of a burning bush in the desert near Mount Sinai.”
Acts 7:30 (ISVN)
እስጢፋኖስ የተናገረው ታሪክ በዘጽ 3:1-2 ተረጋግጦ ይገኛል። ዘጽ 3:1-2 እንደሚለው ሙሴ በእግዚአብሔር ተራራ በኮሬብ የአማቱን የዮቶርን በጎች ሲጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት። ኮሬብ የሲና ሌላ ስም ሲሆን፥ በዘጽ 19-24 እግዚአብሔር በእሳት የወረደበት ተራራ ነው። በዚያው ተራራ ነው የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ነበልባል ለሙሴ የተገለጠለት። ለዚህ ነው እስጢፋኖስ ኮሬብንና ሲናን በተቀያያሪነት የተጠቀመው። የአንዱ ተራራ ስሞች ናቸውና
ይህን ከተናገረ በኋላ፥ ሙሴ ባየው ነገር ተደንቆ ነገሩን ለማጣት ሲቀርብ፥ የጌታን ድምፅ እንደሰማ ይናገራል
ሐዋርያት 7 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ሙሴም ባየው ነገር #ተደነቀ፤ ነገሩን ለማጣራት ወደዚያ ሲቀርብ #የጌታ_ድምፅ፤ ³² እኔ የአባቶችህ አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ’ #ሲል_ሰማ። ሙሴም በፍርሀት ተዋጠ፤ ለመመልከትም አልደፈረም።
ይህ ማለት ሙሴ የሰማው፥ ያነጋገረው ጌታን ነው ማለት ነው። በቁጥቋጦው ውስጥ ሆኖ ሙሴን ያነጋገረው ጌታ ነው ማለት ነው። ነገር ግን የተገለጠለት መልአኩ ነበር
ሙሴን በዚህ ስፍራ ያነጋገረው ጌታ መሆኑ፥ በቀጣዩ ጥቅስም ተረጋግጧል፦
“ #ጌታም እንዲህ #አለው፤ ‘የእግርህን ጫማ አውልቅ፤ የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና።”
ሐዋርያት 7፥33 (አዲሱ መ.ት)
ሙሴን ጫማውን እንዲያወልቅ ያዘዘው ጌታ እንደሆነ በቁ.33 ላይ በግልፅ እስጢፋኖስ ተናግሯል። ይህ ማለት ሙሴ በሲና ተራራ ላይ ሲነጋገር የነበረው ከእግዚአብሔር ጋር ነበር ማለት ነው። በቁ.32 ላይ የአባቶቹ አምላክ መሆኑን የነገረው ጌታ ነው በቁ.33 ላይ ጫማውን እንዲያወልቅ ያዘዘው። ይህ ሙሴ ከአምላክ ጋር ሲነጋገር እንደነበር የሚያረጋግጥ ነው
ነገር ግን ለሙሴ የተገለጠው መልአኩ ነበር!
በቁጥቋጦው በእሳት ነበልባል ለሙሴ የተገለጠው መልአኩ ነበር። ይህ ማለት ሙሴን ሲያነጋግረው የነበረው ጌታ መልአኩ ነበር ማለት ነው። የተገለጠለትና የታየው እርሱ በመሆኑ፥ አነጋገረው የተባለውም ጌታ እርሱ ነው። ይህ እስጢፋኖስ መልአኩ አምላክ እንደሆነ ለማመኑ ማስረጃ ነው።
እስጢፋኖስ፥ ሙሴን በሲና ተራራ ያነጋገረው መልአኩ መሆኑን በማያሻማ መልኩ እንዲህ ግልፅ አድርጎታል፦
“እርሱም #በሲና_ተራራ_ከተናገረው_መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ በሕዝቡ ጉባኤ መካከል ነበር፤ የሕይወትንም ቃል ወደ እኛ ለማስተላለፍ ተቀበለ።”
ሐዋርያት 7፥38 (አዲሱ መ.ት)
በቁ.37 ግልፅ እንዳደረገው፥ ሙሴን በሲና ተራራ የተናገረው መልአኩ ነበር። በቁ.33 ግን ጫማህን አውልቅ ብሎ የተናገረው ጌታ መሆኑን ግልጽ አድርጓል። በቁ.32ም እንዲሁ ወደ ሙሴ የመጣው ድምፅ የጌታ ድምፅ መሆኑን ተናግሯል። ነገር ግን በቁ.37 ሙሴን ያነጋገረው መልአኩ ነው አለ
ይህ ሙሴን በሲና ተራራ ያነጋገረው ጌታ፥ መልአኩ መሆኑን በማያሻማ መልኩ ያረጋግጣል። ሙሴን ያነጋገረው አምላክ በቁጥቋጦው የተገለጠለት መልአክ ነው።
ለዚህም ነው በቁ.30 ላይ "የጌታ መልአክ" በማለት ፈንታ "መልአክ" ተገለጠለት ያለው። ቀጥሎ ሙሴን ያነጋገረው ጌታ መልአኩ ነውና። ሙሴን ያነጋገረው ጌታ መልአኩ መሆኑን ለመግለጽ "መልአክ" አለ። ይህ እስጢፋኖስ፥ መልአኩ መለኮት መሆኑን እንደሚያምን ያሳያል
እስጢፋኖስ ስለ መልአኩ የተናገረው ነገር፥ በዋናው የዘጽአት ታሪክ ላይ ተረጋግጦ እናገኘዋለን። ለሙሴ የተገለጠው/የታየው፥ በቁጥቋጦው ውስጥም የነበረው፥ መልአኩ ነበር
“እዚያም የእግዚአብሔር (ያህዌ) #መልአክ በቍጥቋጦው ውስጥ በሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል መካከል #ተገለጠለት። ሙሴም ቍጥቋጦው በእሳት ቢያያዝም እንኳ፣ አለ መቃጠሉን አየ።”
ዘጸአት 3፥2 (አዲሱ መ.ት)
ነገር ግን ቁጥቋጦው ውስጥ ሆኖ፥ ጠርቶት ያነጋገረው እግዚአብሔር ነበር
316 views15:03