Get Mystery Box with random crypto!

Isaiah 48 Apologetics

የቴሌግራም ቻናል አርማ thetriune — Isaiah 48 Apologetics I
የቴሌግራም ቻናል አርማ thetriune — Isaiah 48 Apologetics
የሰርጥ አድራሻ: @thetriune
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.97K
የሰርጥ መግለጫ

✟ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✟
"14 The grace of the Lord Jesus Christ, and the love of God, and the communion of the Holy Ghost, be with you all. Amen."
(2Corinthians 13:14)
📌 ሌላኛው ቻናላችን:- @ovadiah

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 13:08:36 አዲስ ጽሑፍ በዶ/ር ሻሎም መኮንን
ለምን ሒጃብ?

http://ewnetlehulu.net/hijab-health-problems/

ከሰባት - አስር ደቂቃ ይነበብ!!
293 views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:26:08
"★መንግሥት በአስቸኳይ ይህንን የርኩሰት ፊልም ያስቁም!"

★ ክርስቲያኖች ተጠንቀቁ!! " ፍልሰት" በሚል ርዕስ በቃና ቲቪ የሚተላለፈውን የሴት ሰዶማውያን /ሌዝብያን / ፊልም ፈጽሞ እንዳታዩ። ★ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ለገንዘብ የሚስገበገቡ፣የራሳቸውን ጥቅም እንጂ በትውልድ ሕይወት ላይ የሚያመጣውን መጥፎ ተጽኅኖ የማያገናዝቡ ስግብግብ ግለሰቦች ያገኙትን የውጪ ፊልም ሁሉ በገንዘባቸው እያስተረጎሙ ትውልድን እያረከሱ ሃገርን እያቆሸሹ ይገኛሉ።

ይህ "ፍልሰት" የሚል የማታለያ ትርጉም የተሰጠው ፊልም "Orfaos da Terra" ከሚል የፓርቹጋል ቋንቋ የተወረሰ ሲሆን የፊልሙ ዋና ዓላማ በስደትና በፍቅር ስም የሴት ሰዶማዊነትን /ሌዝቢያዊነትን/ በትውልድ ልብ ውስጥ ለማስገባትና ወጣቶችን በረከሰ ተግባር ለማጥመድ በምሥጢር ታቅዶ የተሰራ ፊልም ነው። ፊልሙ እጅግ በረቀቀ ዘዴ ወጣቶችን በመሳብ ልባቸውን እያንጠለጠለ የአዕምሮ እጥበት/Brain wash/ በማድረግ ሴት ከሴት ጋር በዝሙት መጨመላለቅን እንደ ዘመናዊነትና እንደ ሥልጣኔ ለማሳየት የተዘጋጀ አጋንንታዊ ፊልም ነው።

እንዳይታወቅባቸው ግን በጦርነት ምክንያት የሚፈጠር ስደት አስመስለው ነው ያቀረቡት። ፊልሙ በማር የተለወሰ መርዝ ነው።... ስለዚህም ይህ" ፍልሰት " በሚል ርዕስ በተከታታይ ለሕዝብ በይፋ በቃና ቲቪ የሚተላለፍ ነውረኛ ፊልም በአስቸኳይ መቆም አለበት።.
771 views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 18:41:37 በዳን 9:25 እና በኢሳ 53:8 ጥቅም ላይ የዋለው ቃል ከዚህ ጋር አንድ አይነት ትርጉም ያለው ቃል ነው። ይህ ማለት በዳን 9:25 እንደሚቆረጥ የተነገረለት ቅቡዕ፥ ከሕያዋን ምድር የተወገደው መሲህ ነው ማለት ነው። ይህ ዳን 9:24-27 መሲሃዊ ትንቢት መሆኑን ያረጋግጣል

በተጨማሪም በሁለቱም ክፍሎች፥ መሲሁ የኀጢአትን ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንደሚሰጠው ይናገራሉ። ይህ ለምን እንደሞተ ግልፅ የሚያደርግ ነገር ነው። መሲሁ የሞተው የኀጢአትን ጉዳይ ለመፍታት ነው። የእርሱ ሞት የበደልን ምህረትን ስለሚያስገኝ፥ በሞቱ የኀጢአትን ጉዳይ ፈጸመው። ይህ በማያሻማ ሁኔታ ዳን 9:24-27 መሲሐዊ ትንቢት መሆኑን ያረጋግጣል።

መደምደሚያ

ዳንኤል 9:24-25 አንድ የኀጢአትን ጉዳይ የሚፈታ፥ አለቃ የሆነ፥ ደግሞም የሚገደል ቅቡዕ እንደሚመጣ ይናገራል። ከላይ በብዙ ማስረጃዎች እንዳየነው፥ ይህ ቅቡዕ መሲሁ ነው።

የክርስቶስ ኢየሱስ መሲህነትን የማይቀበሉ አይሁዳውያን ይህ ክፍል በግልፅ መሲሁ ክርስቶስ ኢየሱስ መሆኑን ስለሚያረጋግጥ፥ መሲሐዊው ትንቢት መሆኑን ክደዋል። ነገር ግን ክፍሉ መሲሃዊ ነው

በታሪክ ከክርስቶስ ኢየሱስ በቀር የኀጢአትን ጉዳይ ለመፈጸም ሁለተኛው ቤተ-መቅደስ ከመፍረሱ በፊት መጥቶ የሞተ ማንም ስለሌለ፥ እውነተኛው መሲህ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ያረጋግጣል። ከእርሱ በቀር ማንም ይህን መስፈርት ያሟላ የለምና። ዳንኤል 9:24-27 ለዚህ ሀቅ ዋና ማስረጃ ነው

ጌታ ይርዳን!
535 views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 18:39:40 እዚህ ጋር "ዳዊት" ተብሎ የሚጠራው የእሰይ ልጅ ሳይሆን፥ መሲሁ ነው። ከላይ እንደተነጋገርነው፥ በመጽሐፍ ቅዱስ መሲሁ በብዙ ስሞች ተጠርቷል። ከነዚህ ስሞች መካከል አንዱ "ዳዊት" ነው። እግዚአብሔር ለዳዊት ከሆዱ ፍሬ በዙፋኑ እንደሚያስቀምጥ ስለማለለት (2 ሳሙ 7:12-16 መዝ 132:11) በእርሱ ዙፋን ላይ የሚቀመጠው መሲሁ፥ ዳዊት ተብሎ ተጠርቷል። (ሆሴ 3:5 ኤር 30:9 ሕዝ 34:23-24) ስለዚህ በዚህ ቦታም "ዳዊት" የሚለው እርሱን ነው።

ቀጥሎም፥ እርሱን ለወገኖች አለቃ አድርጌ ሰጥቼዋለሁ ይላል። "አለቃ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ "נָגִיד/ናጊድ" ሲሆን፥ በዳን 9:25 ላይ ያለው ራሱ ቃል ነው። ይህ ማለት ሁለቱ ክፍሎች ተያያዥነት አላቸው ማለት ነው። የሚመጣው አለቃው ቅቡዕ፥ ለወገኖች የተሰጠው አለቃው ዳዊት (መሲሁ) ነው። ይህ ከምንም ዳንኤል 9 ስለ ክርስቶስ የሚናገር ትንቢት መሆኑን ያረጋግጣል።

ከዚህም ባሻገር፥ በኢሳ 55:3 ላይ በዳዊት አማካኝነት የዘላለም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እንደሚገባ እግዚአብሔር ይናገራል። ይህ በዳን 9:24 ላይ ካለው ሀሳብ ጋር ይገናኛል። ዘላለማዊ ጽድቅ የሚመጣው በዚህ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አማካኝነት ነውና። እግዚአብሔር ዘላለማዊ ኪዳንን በመሲሁ አማካኝነት ማምጣቱ በብዙ ቦታ የተነገረ ነገር ሲሆን (ኤር 31:31) በዳንኤል 9 የተተነበየው ዘላለማዊ ጽድቅ የዚሁ ኪዳን አካል ነው። ይህ ዳንኤል 9 መሲሐዊ ትንቢት ለመሆኑ ተጨማሪ ማሳያ ነው

"አባቶቻችሁም በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል፤ ባሪያዬም #ዳዊት ለዘላለም #አለቃ ይሆናቸዋል።"
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 37:25)

በዚሁ ስፍራም መሲሁ አለቃ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እንመለከታለን። እግዚአብሔር በሚመጣው ዘመን ባሪያው ዳዊት (መሲሁ) ለዘላለም አለቃ እንደሚሆን ይናገራል። በዚህ ስፍራ አለቃ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "נָשִׂיא/ናሲያ" ሲሆን (H5387) በዳን 9:25 ላይ ከተጠቀሰው ቃል ጋር አንድ አይነት ትርጉም ነው ያለው። አዛዥ፥ ገዢ፥ መሪ የሚል ትርጉም ነው ያለው።

እግዚአብሔር ለዘላለም መሲሁ የእስራኤል ሕዝብ ገዢ ይሆናል በማለት የተናገረው፥ መሲሁ ዘላለማዊ ዙፋን ስላለው ነው (መዝ 45:6-7 ዳን 7:13-14 ኢሳ 9:6-7) በተጨማሪም መሲሁ ለወገኖች (ለእስራኤል ሕዝብ) አለቃ እንደሚሆን ተነግሯል (ኢሳ 55:4) ስለዚህ በሕዝ 37 አለቃ ይሆናል የተባለው መሲሁ ለመሆኑ ጥርጣሬ የለውም።

በዳን 9:25 ግን የሚመጣው ቅቡዕ፥ አለቃ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ በግልፅ እንደሚያሳየው፥ የሚመጣው ቅቡዕ አለቃ በእስራኤል ለዘላለም አለቃ የሚሆነው መሲሁ ነው። ማለትም፥ ዳንኤል 9:24-27 ፍጹም መሲሐዊ ትንቢት ነው ማለት ነው።

በሕዝ 37:25 የምንመለከተው ሀሳብ በሕዝ 34:24 ላይም ተደግሞ እንመለከታለን፦

"እኔም እግዚአብሔር አምላክ እሆናቸዋለሁ ባሪያዬም #ዳዊት በመካከላቸው #አለቃ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።"
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:24)

ልክ እንደ ሕዝቅኤል 37፥ በዚህ ስፍራም መሲሁ "አለቃ" ተብሎ ተጠርቷል። ዳን 9:25 ላይ የተነገረለት ቅቡዕ የተጠራበት ስም ነው። ይህ በይበልጥ፥ ዳን 9:24-27 መሲሃዊ ትንቢት መሆኑን ያሳያል

6) ይቆረጣል

በዳንኤል 9 ስለ ሚመጠው ቅቡዕ ከተነገሩት ሌሎች ነገሮች መካከል፥ እንደሚቆረጥ ነው።

"ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ #መሢሕ #ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል።"
(ትንቢተ ዳንኤል 9:26)

"ይገደላል" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "כָּרַת/ካሬት" ሲሆን (H3772) በቀጥታ ሲተረጎም "መቆረጥ" ማለት ሲሆን፤ መገደልን፥ መሞትን የሚያመለክት ቃል ነው። ቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ መሞትን እና በተለይም በሰው እጅ መገድልን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። ለምሳሌ፦

"ቴማን ሆይ፥ ሰዎች ሁሉ ከዔሳው ተራራ #በመገደል #ይጠፉ ዘንድ ኃያላንህ ይደነግጣሉ።"
(ትንቢተ አብድዩ 1:9)

በዚህ ቦታ እግዚአብሔር በኤዶማዊያን ላይ ስለሚተላለፈው ፍርድ ሲናገር እንመለከታለን። እርሱም፥ ተገድለው እንደሚጠፉ ነው። "ይጠፉ" የሚለው ቃል በዳን 9:24 ላይ "ካሬት" ተብሎ የተተረጎመው ራሱ ቃል ሲሆን፥ በሰው እጅ ተገድሎ መጥፋትን ያመለክታል። ለዚያ ነው "ተገድለው" የሚለው። ሌላ ምሳሌ፦

"ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ #ሰይፍ አመጣብሃለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከአንተ ዘንድ #አጠፋለሁ።"
(ትንቢተ ሕዝቅኤል 29:8)

በዚሁ ስፍራም፥ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ ስለሚመጣው ፍርድ ሲናገር እንመለከታለን። እርሱም፥ ሰይፍን እንደሚያመጣበትና ሰውንና እንስሳውን እንደሚያጠፋበት ይነግረዋል። አሁንም "አጠፋለሁ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል በዳን 9:25 ላይ ያለው "ካሬት" የሚለው ቃል ነው። በዚህ ቦታ ግብጻውያን በሰይፍ እንደሚገደሉ ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። ይህ እንደሚያሳየው፥ ይህ ቃል በሰው እጅ መገደልን ያመለክታል።

በዳን 9 የተነገረለት ቅቡዕ ደግሞ ይቆረጣል ተብሏል። ይህ ማለት ይሞታል፥ በሰው እጅ ይገደላል ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ እንድሚነግረን ደግሞ፥ መሲሁ ለኀጢአታችን ሲል ይሞታል። ይህ በዳን 9 ላይ የተነገረለት ቅቡዑ መሲሁ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል፦

"ከክፉዎችም ጋር #መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር #በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገንበትም ነበር።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:9)

በዚህ ቦታ ላይ እንደምናነበው፥ መሲሁ መቃብሩ ከክፉዎች ጋር ሞቱ ከባለጠጎች ጋር ይሆናል። ማለትም መሲሁ ይሞታል ማለት ነው። ይህ መሲሁ እንደሚሞት የተነገረ ቀጥተኛ ምስክርነት ነው። ስለዚህ በዳን 9:25 የተተነበየለት ቅቡዑ የሚቆረጠው፥ በኢሳ 53:9 ላይ የተተነበየለት መሲህ ስለሆነ ነው። ይህ ዳን 9:24-27 ፍጹም መሲሃዊ ትንቢት ለመሆኑ የማይታበል ማስረጃ ነው።

"በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ #ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:8)

በዚሁ ስፍራም መሲሁ ከሕያዋን ምድር ተመትቶ እንደሚወገድ ተተንብዮ እንመለከታለን። "ተመትቶ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "גָּזַר/ጋዛር" ሲሆን፥ በዳን 9:25 ላይ ከተጠቀሰው ቃል ጋር አንድ አይነት ትርጉም ነው ያለው። "መቆረጥ" ማለት ሲሆን፤ መሞትን፥ በሰው እጅ መገደልን የሚያመለክት ቃል ነው።

ይህ ራሱ ቃል፥ በመጽሐፍ ቅዱስ በሰው እጅ መገደልን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል፦

"ለዘላለም እንደማታስባቸው፥ እንደ #ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ በሙታን ውስጥ እንዳሉ የተጣልሁ ሆንሁ፤ እነርሱም ከእጅህ #ተለዩ።"
(መዝሙረ ዳዊት 88:5)

"ተለዩ" የሚለው ቃል በኢሳ 53:8 ላይ ያለው ራሱ ቃል (ጋዛር) ሲሆን፤ መገደልን፥ መሞትን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። ይህ ክፍል ስለ ተገደሉ ሰዎች የሚናር ክፍል ነውና፥ ቃሉ በሰው እጅ መሞትን ለማመልከት ጥቅም ላይ እንደዋለ እርግጠኛ መሆን እንችላለን።
385 views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 18:39:40 በእንተ ዳንኤል 9 (ክፍል 3)

ባለፉት ክፍሎች እንዴት ዳን 9:24-27 በእርግጥም ስለ ሚመጣው መሲህ የሚናገር መሲሐዊ ትንቢት መሆኑን ለመመልከት ሞክረን ነበር። በዚያ ክፍል ቅቡዑ (የተቀባው) የተጠራባቸው ስያሜዎች በሙሉ፥ በሌሎች ክፍሎች መሲሁ የተጠራባቸው ስያሜዎች ናቸው። ያደርጋቸዋል የተባሉት ነገሮች በሙሉ፥ መሲሁ የሚያደርጋቸው ነገሮች ናቸው

በተደጋጋሚ ለማለት እንደሞከርነው፥ ዳን 9:24-27 ስለ መሲኁ ሳይሆን ስለ ሌላ አካል ነው የሚናገረው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም የተጠራባቸው ስያሜዎችና ያደርጋቸዋል የተባሉት ስራዎች፥ መሲሁ ብቻ የተጠራባቸውና ያደርጋቸዋል የተባሉት ነገሮች ናቸው። ስለዚህ፥ የክርስቶስ ኢየሱስን መሲህነት የማይቀበሉት ረቢዎች ሙግት ፈጽሞ ስህተት ነው ማለት ነው። በክፍሉ ከተቀመጠው ቀነ ገደብ ባሻጋር፥ ቅቡዑ የተገለጠባቸው መገለጫዎች በሙሉ መሲሁ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ይህ ደግሞ ለጌታ ኢየሱስ መሲህነት የማይታበል ማረጋገጫ ነው

ዛሬም በዚሁ ክፍል፥ በዳንኤል 9 ላይ የተገለጠው ቅቡዕ መሲሁ ለመሆኑ ተጨማሪ ማስረጃዎችን እናቀርባለን፦

4) ዘላለማዊ ጽድቅን ያመጣል

በዳንኤል 9 ላይ የምንመለከተው ቅቡዕ፥ ከሚሰራቸው ነገሮች አንዱ ዘላለማዊ ጽድቅን ማምጣት ነው፦

"ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ #የዘላለምን_ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።"
(ትንቢተ ዳንኤል 9:24)

የዘላለምን ጽድቅ ያገባ ዘንድ ማለት፥ የሰው ልጆች የሚጸድቁበትን መንገድ ያመጣል ማለት ነው። በእርሱ አማካኝነት፥ ጊዜያዊ ያይደለ፥ ዘላለማዊ የሆነ ጽድቅ ይኖራል። ሰዎች የሚጸድቁበት ዘላለማዊ ጽድቅ በእርሱ አማካኝነት ይገኛል ማለት ነው። በእርሱ ምክንያት፥ የሰው ልጆች ዘላለማዊ ጽድቅ እንደሚያገኙ የሚናገር ትንቢት ነው። ይህ ቅቡዕ ለሰው ልጆች ዘላለማዊ ጽድቅን ማምጣቱን ለማመልከት፥ "ዘላለማዊ ጽድቅን ያገባ ዘንድ" ተብሎ ተተነበየ

በዳን 9:24 "ጽድቅ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "צֶדֶק/ጼዴቅ" ሲሆን (H6664) "የሞራል ሆነ የሕግ ትክክለኛነት" ማለት ነው። ይህ ቅቡ ሰዎችን ከስህተታቸውና ከውድቀታቸው በማውጣት በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ያደርጋቸዋል፥ ያጸድቃቸዋል ማለት ነው። ዘላለማዊ ጽድቁን የሚያገባው እርሱ ነውና

መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስናጠና፥ የሚመጣው መሲህ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ፥ ሰዎችን ማጽደቅ እንደሆነ እንረዳለን፦

"ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ #ጻድቅ_ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ #ሰዎችን #ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:11)

በዚህ ስፍራ እንደምንመለከተው፥ መሲሁ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ ብዙዎችን ማጽደቅ ነው። ጻድቁ የእግዚአብሔር ባሪያ መሲሁ፥ በእውቀቱ ብዙዎችን ያጸድቃል። በእርሱ ምክንያት ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። በኢሳይያስ 53 "ያጸድቃል" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "צֶדֶק/ጼዴቅ" በዳን 9:24 "ጽድቅ" ተብሎ የተተረጎመው ራሱ ቃል ነው። ይህ እንደ በፊቱ፥ ሁለቱ ክፍሎች ቀጥተኛ ተያያዥነት እንዳላቸው ያሳያል።

በዳን 9:24 የዘላለምን ጽድቅ ያገባ ዘንድ ሲል፥ እየተናገረ ያለው ስለዚህ ነው። መሲሁ ብዙዎችን የሚያጸድቀው፥ ዘላለማዊ ጽድቅን በማግባት ነው። ይህ በእርግጥም በዳን 9 የምንመለከተው ቅቡዕ፥ የሚመጣው መሲሕ መሆኑን ያረጋግጣል።

ባለፈው እንደተነጋገርነው፥ መሲሁ የሰው ልጆች የኀጢአት ይቅርታ ያገኙ ዘንድ ለኀጢአታቸው እንደሚሞት አይተን ነበር። በእርሱ ሞት እነርሱ ምህረትን ካገኙ፥ ጸደቁ ማለት ነው። ስለዚህ የመሲሁ መስዋዕታዊ ሞት (sacrificial death) የዘላለምን ጽድቅ ከማምጣቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው ማለት ነው። በእርሱ ሞት ነው የሰው ልጅ የጸደቀው

(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 23)
----------
5፤ እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ #ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ #ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።

6፤ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ #የሚጠራበትም ስም። #እግዚአብሔር #ጽድቃችን ተብሎ ነው።

በዚህ ስፍራም፥ በዳዊት ዙፋን ላይ ስለ ሚቀመጠው መሲህ የተነገረ ትንቢት እንመለከታለን። እግዚአብሔር ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ እንደሚያበቅ ሲናገር እንመለከታለን

በመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥቋጦ፥ ከመሲሁ መጠሪያዎች አንዱ ነው። መሲሁ በብዙ ስሞች የተጠራ ሲሆን፥ ከእነዚህ መጠሪያዎች አንዱ "ቁጥቋጥ" ነው (ዘካ 3:8 ኢሳ 11:1 ኤር 33:15-16 ዘካ 6:12-13) ስለዚህ በዚህ ቦታ እየተነገረ ያለው ስለ መሲሑ ነው

ይህ መሲህ እንደ ንጉስ በሚንግስበት ጊዜ "እግዚአብሔር ጽድቃችን" ተብሎ እንደሚጠራ ክፍሉ ይናገራል። መሲሁ "እግዚአብሔር ጽድቃችን" መባሉ አምላክ መሆኑን ከማረጋገጥ ባሻገር፥ የጽድቃችን መንስኤ መሆኑን ያሳያል። ምክንያቱም "ጽድቃችን" ተብሎ ተጠርቷልና። ጽድቃችን ማለት የኛ ጽድቅ፥ ያጸደቀን፥ ጽድቅን የሰጠን ማለት ነው። በዚህ ስፍራ፥ መሲሁ ጽድቃችን ተብሎ ተጠርቷል።

በዳን 9 ላይ ደግሞ፥ እንደሚመጣ የተተነበየለት ቅቡዑ የዘላለምን ጽድቅ እንደሚያገባ ተነግሯል። ይህ ማለት የዘላለምን ጽድቅ የሚያገባው ቅቡዕ፥ ጽድቃችን የሆነው መሲሁ ነው ማለት ነው። ዘላለማዊ ግዛት ኖሮት፥ ዘላለማዊ ጽድቅን ሊያመጣ የሚችለው እርሱ ብቻ ነውና።

ይህ ሁሉ በማያሻማ ሁኔታ፥ ዳን 9:24-27 ስለ ሚመጣው መሲህ የተነገረ ትንቢት መሆኑን ያረጋግጣል።

5) አለቃ (Prince) ነው

በዳን 9:24 ላይ እርሱ የሚሰራቸውን ነገሮች መልአኩ ገብርኤል ለነቢዩ ዳንኤል ከነገረው በኋላ፥ የሚመጣው ቅቡዕ "አለቃ" ወይንም "Prince" መሆኑን ይነግረዋል፦

"ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ #አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።"
(ትንቢተ ዳንኤል 9:25)

በዚህ ስፍራ "አለቃ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "נָגִיד/ናጊድ" ሲሆን (H5057) "ገዢ፥ አለቃ፥ አዛዥ፥ ልዑል" የሚል ትርጉም አለው። ይህ እንደሚያሳየው፥ በዳን 9 ላይ የተተነበየለት ቅቡዕ አለቃና ገዢ መሆኑን ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ እንደሚነግረን፥ መሲሁ ከተጠራባቸው ስሞች መካከል አንዱ "አለቃ" ነው፦

"3፤ ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ስሙ ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች፤ የታመነችይቱን #የዳዊትን ምሕረት፥ የዘላለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ። 4፤ እነሆ፥ ለአሕዛብ ምስክር፥ ለወገኖችም #አለቃና አዛዥ እንዲሆን ሰጥቼዋለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 55:3-4)

በዚህ ስፍራ እግዚአብሔር ስለ መሲሁ የሚናገረውን ነገር እንመለከታለን። እርሱም፥ የታመነችውን የዳዊትን ምህረት ከናንተ ጋር አደርጋለሁ ይላል
318 views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:21:53 በዚህ ስፍራም እንዲሁ ሰዎች የኀጢአት ስርየትን ለማግኘት የበደል መስዋዕት ሲያቀርቡ እንመለከታለን። ኀጢአተኞች ለሰሩት ኀጢአት ይቅርታን ሲፈልጉ፥ የበደል መስዋዕትን (አሻም) ያቀርባሉ። ካህኑም፥ ያን የበደል መስዋዕት ተቀብሎ ለኀጢአተኞቹ ያስተሰርይላቸዋል። እነርሱም ይቅር ይባላሉ። ለይቅርታውና ለስርየቱ (ካፓር) መንስኤው የበደል መስዋዕቱ ሲሆን፥ ኀጢአተኞቹ ይቅር የተባሉት በመስዋዕቱ ምክንያት እንደሆነ ግልፅ ነው። ይህ የበደል መስዋዕት የስርየት መንስኤ መሆኑን ያረጋግጣል። የመጨረሻ ምሳሌ፦

"ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት #በበደል_መሥዋዕት በግ #ያስተሰርይለታል፤ የሠራውም ኃጢአት ይቀርለታል።"
(ኦሪት ዘሌዋውያን 19:22)

እዚህ ጋር እንዲሁ፥ ኀጢአተኞች የኀጢአት ስርየትን የሚያገኙት በበደል መስዋዕት መሆኑ ተጽፏል። ኀጢአትን የሰራው ግለሰብ፥ ኀጢአቱ እንዲቀርለት የበደል መስዋዕት (አሻም) ያቀርባል። ካህኑን የበደሉን መስዋዕት በመውሰድ፥ ለኀጢአተኛው ያስተሰርይለታል። ሰውየውም ኀጢአቱ ይቀርለታል። ይህ የበደል መስዋዕት ለስርየት (ካፓር) መንስኤ እንደሆነ ከምንም በላይ ያረጋግጣል።

ተጓዳኝ አንቀጾች፦ ዘሌ 7:7 ዘሌ 14:21 ዘሌ 17:11

በዳን 9:24 ቅቡዑ በደል እንደሚያስተሰርይ ተተንብይዋል። ስለዚህ በቃሉ መሰረት፥ ለበደል ስርየት ምክንያት የሚሆነው እርሱ ነው ማለት ነው።

ከላይ ለማየት እንደሞከርነው ደግሞ፥ የስርየት (ካፓር) ምክንያት የበደል መስዋዕት (አሻም) ነው። ስርየትን የሚያስገኘው የበደል መስዋዕት መሆኑን የእግዚአብሔር ቃል ይናገራልና።

መጽሐፍ ቅዱስ መሲሑ ይሆናል ያለው ይህንኑ ነው። በእግዚአብሔር ቃል አስተምህሮ መሠረት፥ መሲሁ የበደል መስዋዕት (አሻም) ነው፦

" እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈከደ፤ ነፍሱን ስለ #ኃጢአት_መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:10)

በዚህ ስፍራ መጽሐፍ ቅዱስ መሲሁ፥ ነፍሱን የኀጢአት መስዋዕት እንደሚያደርግ ይናገራል። "የኀጢአት መሥዋዕት" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "אָשָׁם/አሻም" ሲሆን በሌሎቹ ቦታዎች ላይ ያለው ቃል ነው። መሲሁ የኀጢአት መስዋዕት ይሆናል። የእርሱ ሞት መስዋዕታዊ ሞት (sacrificial death) ነው። በእርሱ ሞት እኛ ስርየትን እናገኛለን

ስለዚህ በዳን 9:24 ላይ የተነገረውን የበደል ስርየት የሚያስገኘው እንዲህ ነው ማለት ነው። በቤተመቅደሱ የበደል መስዋዕት ስርየትን እንዳስገኘ ሁሉ፥ መሲሁም ነፍሱን የኀጢአት መስዋዕት በማድረግ በደልን ያስተሰርያል ማለት ነው። በደልን የሚያስተሰርየው እንደዛ ነው፥ ነፍሱን የኀጢአት መስዋዕት በማድረግ። ይህ ከምንም በላይ፥ በደልን የሚያስተሰርየው ቅቡዕ፥ ነፍሱን የኀጢአት መስዋዕት ያደረገው መሲህ መሆኑን ያረጋግጣል። ማለትም፥ በዳን 9:24-27 የተነገረለት ቅቡዕ፥ መሲሁ ነው ማለት ነው

ይቀጥላል
391 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:19:11 በእንተ ዳንኤል 9 (ክፍል 2)

ባለፈው ክፍል እንዴት ዳንኤል 9 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መሲሕነትን ከሚያረጋግጡት ትንቢቶች መካከል በዋነኝነት ተጠቃሽ እንደሆነ እና ተቃዋሚዎች እንደሚሉት ሳይሆን፥ በእርግጥም ክፍሉ መሲሐዊ መሆኑን ለማየት ሞክረን ነበር። ደግሞም በአንቀፁ መሠረት፥ የሚመጣው መሲሕ የሚሞተው የኀጢአትን ይቅርታ ለማስገኘት እንደሆነ ተመልክተናል

ዳንኤል 9:24-27 ይመጣ ዘንድ ያለው መሲሕ ሁለተኛው ቤተመቅደስ ከመፍረሱ በፊት እንደሚመጣና እንደሚገደል ይተነብያል። ይህ ክርስቶስ ኢየሱስ እውነተኛው መሲሕ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ግልፅ ያረጋግጣል። ምክንያቱም በታሪክ ከክርስቶስ በቀር ከሁለተኛው ቤተመቅደስ መፍረስ በፊት መጥቶ፥ ለኀጢአት እንደሚሞት የተናገረ መሲሕ (Messiah claimant) የለምና።

በዚህኛውም ክፍል፥ እንዴት ክፍሉ በእርግጥም መሲሐዊ እንደሆነ ለማየት እንሞክራለን፦

3) በደልን ያስተሰርያል

የሚመጣው መሲህ ዓመፃን ከመጨረስና ኀጢአትን ከመፈጸም ባሻገር፥ በደልን እንደሚያስተሰርይ ዳን 9:24 ይናገራል፦

"ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ #በደልንም_ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።"
(ትንቢተ ዳንኤል 9:24)

ልክ እንደ በፊቱ ሁሉ፥ ይህ ቅቡዑ በደልን እንደሚያስተሰርይ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህ ማለት በደልን በማስወገድ፥ ለዚህ ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሔ ያመጣለታል ማለት ነው። በደል፥ የሰው ልጆችን ከእግዚአብሔር ያራቀ ትልቅ ችግር ነው። ይህ ቅቡዕ በመጣ ጊዜ ግን፥ በደልን በማስተሰረይ ለዚህ ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መድሃኒት ይሆናል ማለት ነው

"ያስተሰርይ" ተብሎ የተተረጎመው ቃል"ማስወገድ፥ መሰረዝ፥ መደምሰስ፥ መፋቅ" የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን (H3722) ይህ ቅቡዕ በድልን ፈጽሞ እንደሚያስወግድና እንደሚደመስስ ያረጋግጣል። ይህ የሚመጣው ቅቡዑ በደልን እንደሚሰርዝና ለእርሱ መፍትሔ እንደሚሆን ያሳያል። ቅቡዑ በደልን በማስተሰረዩ ጉዳይ፥ በኋላ እንመለስበታለን

በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሠረት ደግሞ፥ የሚመጣው መሲሕ የሚያደርገው ይህንነ ነው፦

"እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ #በደላችንም_ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:5)

በዚህ ስፍራ መሲሑ ስለ በደላችን እንደ ደቀቀ እና በእርሱ ቁስል እንደተፈወስን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ይህ ግልፅ እንደሚያደርገው፥ መሲሁ ስለ በደላችን በመድቀቅ በደላችንን እንደሚያስወግድ ነው። እርሱ ስለ በደል ስለደቀቀ እኛ እንፈወሳለን፤ ከበደላችንም እንነፃለን

በኢሳይያስ 53:5 "በደል" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "עָוֺן/አቮን" ሲሆን በዳን 9:24 ላይ "በደል" ተብሎ የተተረጎመው ራሱ ቃል ነው። ይህ ማለት ሁለቱ ክፍሎች ተያያዥ ናቸው ማለት ነው። መሲሁ በደልን የሚያስተሰርየው፥ ስለ በደላችን በመድቀቅ ነው። የእርሱ ስለበደላችን መድቀቅ፥ ለእኛ ስርየት ነው

በኢሳ 53:5 የተነገረው ቃል፥ በቁ.6 ላይ ተደግሞ እናገኘዋለን፦

"እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን #በደል በእርሱ ላይ #አኖረ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:6)

በዚሁ በቁ.6 ላይ "በደል" ተብሎ የተተረጎመው ቃል በቁ.5 እና በዳን 9:24 ላይ ያለው "አቮን" የሚለው ቃል ሲሆን፥ እግዚአብሔር በመሲሁ ላይ የሁላችንን በደል እንዳኖረበት ይናገራል። ይህ በድጋሚ እንደሚያረጋግጠው፥ መሲሀ ሰዎች ከበደላቸው ነጻ ይሆኑ ዘንድ በደላቸውን ተሸክሞ ይሞታል። በደልን የሚያስተሰርየው፥ የሁሉንም ሰው በደል በመሸከም ነው። ይህ በዳን 9:24-27 የተነገረለት ቅቡዕ፥ መሲሁ መሆኑን ያሳያል

አሁንም፥ በኢሳ 53:5-6 ላይ የተነገረው ቃል በቁ.11 ተደግሞ እንመለከታለን፦

"ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ #ኃጢአታቸውን_ይሸከማል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:11)

በዚሁ ስፍራም እንዲሁ፥ መሲሁ የብዙዎችን ኀጢአት እንደሚሸከም ተተንብዮ እንመለከታለን። እዚህ ጋርም "ኀጢአት" ተብሎ የተተረጎመው ቃል፥ በኢሳ 53:5-6 እና በዳን 9:24 ላይ "በደል" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ነው። መሲሁ የብዙዎችን ኀጢአት ይሸከማል። ይህ በዳን 9:24 ላይ የተነገረውን ስርየት እንዴት እንደሚያስገኝ በማያሻማ መልኩ ግልፅ ያደርጋል። መሲሁ ለበደል ስርየትን የሚያስገኘው፥ በደልን በመሸከም ነው። እርሱ የብዙዎችን በደል በመሸከሙ ምክንያት፥ በደለኛው የሰው ዘር ስርየትን ያገኛል። ይህ ከምንም ነገር በላይ፥ በዳን 9:24-27 የተነገረለት ቅቡዕ መሲሑ መሆኑን ያረጋግጣል

ከላይ ለማመልከት እንደሞከርነው፥ መሲሑ በደልን ያስተሰርያል። "ያስተሰርያል" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "כָּפַר/ካፓር" ሲሆን፥ የኀጢአት መሥዋዕት በመቅረቡ ምክንያት የሚገኝን የኀጢአት ይቅርታ ያመለክታል። ቃሉ በዘሌዋዊያን መጽሐፍ 44 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን፥ ኀጢአትን ለማስወገድ የኀጢአት መሥዋዕት ሲቀርብ የሚገኝ የኀጢአት ይቅርታን የሚያመለክት ቃል ነው።

የኀጢአት መሥዋዕት በዕብራይስጥ "אָשָׁם/አሻም" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን እርሱ እንደ መስዋዕት ሲቀርብ፥ የኀጢአት ስርዓት ይገኛል። ስርየት የሚገኘው፥ የኀጢአት መስዋዕት ሲቀርብ ነው። ለምሳሌ፦

"ስለ ሠራው ኃጢአት ለእግዚአብሔር #የበደል_መሥዋዕት ያመጣል፤ እርሱም ከመንጋው የበግ ወይም የፍየል እንስት ለኃጢአት መሥዋዕት ይሆናል፤ ካህኑም ስለ ኃጢአቱ #ያስተሰርይለታል።"
(ኦሪት ዘሌዋውያን 5:6)

እዚህ ጋር እንደምንመለከተው፥ በደለኛው ኀጢአቱ ይሰረይለት ዘንድ የበደል መሥዋዕት ይዞ ሲመጣ እንመለከታለን። ይዞት የመጣው መስዋዕት የኀጢአት መስዋዕት ይሆንና ካህኑ ያስተሰርይለታል። ለስርየቱ ምክንያት የሆነለት መስዋዕቱ ነው። የበደል መስዋዕቱን (ወይንም "አሻም" በዕብራይስጥ) ይዞ በመቅረቡ ኀጢአቱ ሊሰረይለት ችሏል። የስርየቱ መንስኤ (ወይንም "ካፓር" በዕብራይስጥ) የኀጢአት መስዋዕቱ መሆኑ ግልፅ ነው። ሌላ ምሳሌ፦

"በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኃጢአት ዕዳ ይከፍላል፥ አምስተኛውንም እጅ ይጨምርበታል፥ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም #በበደል_መሥዋዕት አውራ በግ #ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።"
(ኦሪት ዘሌዋውያን 5:16)

በዚሁ ስፍራም የበደል መስዋዕት፥ የኀጢአት ስርየትን ሲያስገኝ እንመለከታለን። ኀጢአተኛው ለሰራው ኀጢአት አውራ በግ ያቀረባል፥ ያም አውራ በግ የበደል መስዋዕት (አሻም) ይሆንና፥ ካህኑ በጉን ያስተሰርይለታል። ኀጢአተኛውም ይቅር ይባላል። ይህ በግልፅ እንደሚያሳየው፥ የስርየቱ (ካፓር) መንስኤ ለኀጢአት ይቅርታ የቀረበው የበደል መስዋዕት መሆኑን ነው። የበደል መስዋዕቱ ስርየትን አስኝቷል። ሌላ ምሳሌ፦

"ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው #ለበደል_መሥዋዕት እንደ ግምጋሜህ መጠን ወደ ካህኑ ያመጣዋል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሳተው ስሕተት #ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።"
(ኦሪት ዘሌዋውያን 5:18)
333 views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 23:38:06 በቁ.8 ላይ "ኃጢአት" ተብሎ የተተረጎመው ቃል በቁ.5 እና በዳን 9:24 ላይ ያለው "ፔሻ" የሚለው ቃል ሲሆን፥ መሲሁ ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ተመትቶ እንደሚሞት ይናገራል። ይህ በድጋሚ እንደሚያረጋግጠው፥ መሲሁ ለኃጢአት ይቅርታ እንደሚሞት ነው። ዓመፃን የሚጨርሰው፥ ስለ እርሱ በመሞት ነው። ይህ ዳን 9:24-27 የተነገረለት ቅቡዕ በእርግጥም መሲሑ መሆኑን ያረጋግጣል።

3) ኃጢአትን ይፈጽማል

ዓመጻን እንደሚጨርስ ከተናገረ በኋላ፥ ኃጢአትንም እንደሚፈጽም ዳን 9:24 ይናገራል፦

"ዓመፃን ይጨርስ፥ #ኃጢአትንም_ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።"
(ትንቢተ ዳንኤል 9:24)

"ይፈጽም" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "መጨረስ፥ መደምደም፥ ማብቃት" የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን (strong's H2856) አሁንም ይህ ቅቡዕ የኃጢአትን ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚፈታው ያረጋግጣል። ለኀጢአት መድኃኒት ይሆናል

ልክ እንደ በፊቱ፥ መጽሐፍ ቅዱስ የሚመጣው መሲህ ይህንን እንደሚያደርግ ያስተምራል፦

"ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን #ኃጢአት #ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:12)

በዚያው በኢሳይያስ 53፥ መሲሑ የብዙዎችን ኃጢአት እንደሚሸከም ተተንብዩ እንመለከታለን። ይህ በድጋሚ እንደሚያረጋግጠው፥ መሲሁ የብዙዎችን ኀጢአት በመሸከሙ ምክንያት እነርሱ የኀጢአትን ይቅርታ ይቀበላሉ።

በዚህ ስፍራ "ኀጢአት" ተብሎ የተተረጎመው ቃል "ኻታ/חֵטְא" ሲሆን በዳን 9:24 ላይ "ኀጢአት" ተብሎ የተተረጎመው ራሱ ቃል ነው። ይህ ማለት ሁለቱ ክፍሎች ቀጥተኛ ተያያዥነት አላቸው ማለት ነው። መሲሁ ኀጢአትን የሚፈጽመው፥ እርሱን በመሸከም ነው። የብዙዎችን ኀጢአት ተሸክሞ የኀጢአት ይቅርታን በማስገኘቱ ኀጢአትን ፈጽሟል። ይህ በዳንኤል 9:24-27 የተነገረለት ቅቡዕ ሌላ ግለሰብ ሳይሆን፥ ራሱ መሲሑ መሆኑን ያረጋግጣል

ይቀጥላል
379 views20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 23:38:05 በእንተ ዳንኤል 9 (ክፍል 1)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነቢያት እንደሚመጣ የተተነበየለት እውነተኛው መሲሕ መሆኑን ከሚያረጋግጡት ዋነኛ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች መካከል አንዱ ዳንኤል 9 ነው። ዳን 9:24-27 የሚመጣው መሲሕ የሚመጣበትን ጊዜና መጥቶ ምን እንደሚያደርግ የሚናገር አስደናቂ ትንቢት ነው። በትንቢቱ መሰረት፥ መሲሁ ሁለተኛው ቤተ መቅደስ ከመፍረሱ በፊት ይመጣና፤ ይገደላል፥ ምንምም አይቀረውም። ስለዚህ በነቢያት ትንቢት መሠረት፥ መሲሑ የመጣው ከሁለት ሺህ አመት በፊት ነው ማለት ነው።

ነገር ግን የክርስቶስን መሲህነት የማይቀበሉት አይሁዳውያን፥ ዳን 9:24-27 በዚህ መልኩ አይረዱትም። ከነ አካቴው መሲሃዊ ትንቢት መሆኑን ይክዳሉ። በእነርሱ አፈታት መሠረት፥ በዳን 9 የተነገረለት ቅቡዕ (የተቀባው ሰው) መሲሁ ሳይሆን ሌላ ሰው ነው። በትንቢቱ የሚገኘውንም የጊዜ ገደብ የሚቆጥሩት በሌላ አቆጣጠር ነው። ይህ ግን ፈጽሞ የተሳሳተ አረዳድ ነው

የዚህ ጽሑፍ አላማ በዳን 9:24-27 የተቀመጠውን የጊዜ አቆጣጠር ማብራራት አይደለም። ይልቁንም፥ ክፍሉ የሚናገረው ስለ ሌላ ግለሰብ ሳይሆን፥ ስለ መሲሑ መሆኑን ማሳየት ነው። ክፍሉ ስለ መሲሑ መሆኑን ካረጋገጥን፥ በትክክል የትንቢት ፍጻሜ ጌታ ኢየሱስ መሆኑን እናረጋግጣለን ማለት ነው። ማስረጃዎቹ እነሆ፦

1) የተቀባው (መሲህ) ተብሏል

"ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ #መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።"
(ትንቢተ ዳንኤል 9:25)

ረቢዎቹ በዳንኤል 9 ላይ ከሚያነሷቸው ተቃውሞዎች አንዱ፥ "ማሺያኽ/משיח" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "የተቀባው" ወይንም "ቅቡዕ/an anointed one" እንጂ ተብሎ መተርጎም ያለበት፥ መሲሕ ተብሎ መተርጎም የለበትም የሚለው ነው። ለዚህም ምክንያታቸውን ሲያቀርቡ፥ የሚመጣው መሲህ በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ስሞች ቢጠራም "የተቀባው" ወይንም "መሲህ" ተብሎ አልተጠራም፥ መሲህ ተብሎ የተጠራው በሌሎች ጽሑፎች ነው ይላሉ። ስለዚህ ዳንኤል 9 ላይም "ማሺያኽ" ሲል ስለሚመጣው መሲህ አይናገርም፥ ደግሞም "መሲህ" ተብሎ መተርጎም የለበትም ይላሉ።

ይህ ግን ፈጽሞ ስህተት ነው። ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መሲሁ ከተገለፀባቸው መገለጫዎች አንዱ "የተቀባው" ወይንም "the anointed one" የሚለው ነው፦

"ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን #ቀባህ።"
(መዝሙረ ዳዊት 45:7)

ስለ መሲሑ በተዘመረው በዚህ መዝሙር ላይ፥ መሲሑ የተገለጸበትን አንድ መገለጫ እንመለከታለን። እርሱም ጽድቅን ስለ ወደደና አመጽን ስለጠላ፥ አምላኩ እግዚአብሔር በደስታ ዘይት ቀብቶታል። ይህ ከመሲሑ መገለጫዎች መካከል "ቅቡዑ/the anointed one" አንዱ መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ መሲሁ "የተቀባው" ተብሎ አልተገለፀም የሚለው አቋም ስህተት ነው ማለት ነው።

በዳን 9:25-26ም እንዲሁ "የተቀባው" ስለሚል፥ ትንቢቱ ስለ መሲሁ አይደለም ማለት ስህተት ነው። መሲሁ በሌላ ቦታ ላይ የተጠራበት ስያሜ ነውና። በመዝ 45:7 ይየ ጥቅም ላይ የዋለው ቃል "ማሺኺኽ/משחך" ሲሆን በዳን 9:25-26 "መሲሕ" ተብሎ የተተረጎመው ራሱ ቃል ነው። ይህ ዳን 9:24-27 በእርግጥም መሲሐዊው ትንቢት ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው። የሚመጣው መሲህ የተቀባው ነውና፦

"የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር #ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 61:1)

በዚሁ ስፍራም እንዲሁ፥ መሲሁ የተቀባ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እንመለከታለን። ነቢዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ስለ መሲሑ ከተናገራቸው ነገሮች አንዱ፥ የተቀባ መሆኑን ነው። ይህ ከመሲሑ መገለጫዎች አንዱ "የተቀባው" መሆኑን ያረጋግጣል።

ኢሳያስ 61 እጅግ ዝነኛ መሲሐዊ ትንቢት ነው። በዚህ ስፍራ ስለ እርሱ የተባሉት ነገሮች በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስለ መሲሁ የተነገሩ ነገሮች ናቸው። የእግዚአብሔር መንፈስ በላዩ ነው (ኢሳ 61:1 ከኢሳ 11:2 እና ከኢሳ 42:1 ጋር ያነጻ) የተቀባ ነው (ኢሳ 61:1 ከመዝ 45:7 ጋር ያነጻ) የጽድቅን መጎናጸፊያ ደርቧል (ኢሳ 61:10 ከኢሳ 11:5 እና ከኤር 23:5-6 ጋር ያነጻ) የማዳንን ልብስ ለብሷል (ኢሳ 61:10 ከመዝ 72:13 ጋር ያነጻ) ይህ ሁሉ ኢሳያስ 61 መሲሐዊ ትንቢት መሆኑን ግልፅ ያደርጋል። በተጨማሪም በክፍሉ የተዘረዘሩት ነገሮች በሙሉ በሌላ በማንም አልተፈጸሙም። ይህ ምዕራፉ መሲሃዊ ለመሆኑ የማይታበል ማሳያ ነው። ስለዚህ በዚህ ክፍል መሲሁ የተቀባው መባሉ፥ ከእርሱ መገለጫዎች አንዱ መሆኑን ያረጋግጣል።

በዳንኤል 9 እንደሚገደል የተተነበየለት አለቃ "የተቀባው" ተብሎ ተጠርቷል። ይህ ክፍሉ ስለ መሲሑ እንደሚተነብይ የምናረጋግጥበት አንዱ መንገድ ነው። በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከጠራባቸው ስሞች አንዱ ነውና።

2) ዓመፃን ይጨርሳል

በዳንኤል 9:24 የተቀባው አለቃ ዓመፃን እንደሚጨርስ ተተንብይዋል፦

" #ዓመፃን_ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።"
(ትንቢተ ዳንኤል 9:24)

"ይጨርስ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "መከልከል፥ ማገት፥ ማስቆም" የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን (strong's H3607) ይህ ቅቡዕ የአመጻን ጉዳይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚፈታው ያሳያል። የአመጻን ጉዳይ በማያዳግም መልኩ መፍትሔ ያመጣለታል።

በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሠረት፥ የሚመጣው መሲህ ያንኑ ነው የሚያደርገው፦

"እርሱ ግን ስለ #መተላለፋችን #ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:5)

በዚህ ስፍራ መሲሁ ስለ መተላለፋችን እንደቆሰለ እና በእርሱ ቁስል እንደምንፈወስ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። ይህ እንደሚያረጋግጠው፥ መሲሁ ስለ እኛ መተላለፍ በመቁሰሉ እኛ እንፈውሳለን። የእርሱ ስለ እኛ መተላለፍ መቁሰል ለእኛ መፈወስ ነው።

በኢሳይያስ 53:5 "መተላለፍ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "ፔሻ/פֶּשַׁע" ሲሆን በዳን 9:24 ላይ "ዓመፃ" ተብሎ የተተረጎመው ራሱ ቃል ነው። ይህ ማለት፥ ሁለቱ ክፍሎች ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ማለት ነው። መሲሁ ዓመፃን የሚጨርሰው፥ ስለ መተላለፋችን በመቁሰል ነው። የእርሱ መቁሰል፥ የአመጻ መፍትሔ ነው

በኢሳ 52:5 የተነገረው ቃል በቁ.8 ላይ ተደግሞ እንመለከተዋለን፦

"በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ #ኃጢአት #ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:8)
367 views20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 14:52:54
Origen (c.184-253) Contra Celsum, Book II chapter 71
646 views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ