Get Mystery Box with random crypto!

The Motivator

የቴሌግራም ቻናል አርማ the_motivators — The Motivator T
የቴሌግራም ቻናል አርማ the_motivators — The Motivator
የሰርጥ አድራሻ: @the_motivators
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 498

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-20 17:42:26 የሰርክ ፀሎት

የማያረጅ ፣ የማይቀጭ ፣ ወረት አልባ ፍቅር ስጠኝ ፤ ማግኘቴ ውስጥ የምሰጠው ፣ የማግዘው ፣ የሚደሰት  ይኖረኝ ዘንድ ቸር ልብ ስጠኝ ፦

የምችለውን ችግር  ስጠኝ ፣ መኖሬ በሰው ቸርነት ይቀጥል  ዘንድ የምለምን አልሁን ፦

ሳጠፋ ይቅርታ የሚጠይቅ ልቦና ስበደል  ይቅርታ አድራጊ ልብ ስጠኝ፦

ገመና የምሸሸግ ፣ ብልግናን የማላጎላ ፣ ዘመዴ የሆነውን የሰው ልጅ የምወድ እና የምረዳ አድርገኝ ፦

እንግዳ እንደሆንኩ ስኖር በዚች አለም ይገባኝ ዘንድ ልቦናዬን አብራልኝ

ስለሆነልኝ ፣ ስለምታረግልኝ ነገር እኔ ባሪያህ አመሰግንሃለሁ                   

አሜን

@the_motivators
32 views(¯`*•.Đāvě .•*´¯), 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 11:35:09 #ሕይወትህን_የሚለውጡ_ምክሮች

#1_100%_ሃላፊነት_ውሰድ

-ሰበቦችን እና ቅሬታዎችን ተው።
-ትክክለኛ ጊዜ እስኪመጣ አትጠብቅ።
-የምትፈልገውን ምቹ ሁኔታ ለራስህ ፍጠር።

#2_ከራስ_ጋር_በመሆን፣
      -በማንበብ እና
      -በመፃፍ ጊዜህን አሳልፍ።

#3_መርዛማ_ግንኙነቶችን_ቋጭ

ወደ ኋላ እየገተተህ ያለን ማንኛውንም ግንኙነት አቋርጥ።

ከሱስ፣ ከሰዎች፣ ከቦታዎች እና ከመጥፎ ትዝታዎች ጋር ያለህን ማንኛውንም መጥፎ ግንኙነቶች አቋርጥ።

#4_ካለፈው_ጋር_ሰላምን_ፍጠር

ለትላንት ጥፋትህ ትንሽ ምሕረትን እና ርሕራሄን ለራስህ አሳይ።

ትላንት አልፏል፤ በመጥፎ ትዝታው ዛሬን እንዳታጣ ከትላንት ጋር ስላምን ፍጠር።

#5_ግልጽ_ግቦችን_አውጣ፤
ለግቦቹ መሳካትም ቃል ግባ፤
ያለማቋረጥም ጠንክረህ ስራ።


@the_motivators
@the_motivators
54 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 22:17:14 #የሕይወት_ቤንዚን_ቀመርህን_ፈልግ!

እውነተኛ ታሪክ

የጀርመን ኦርጋኒክ ኬሚስት ፍሬድሪክ ቮን ስትራዶኒትዝ የቤንዚን ቀመር ውስጥ የሚገኙትን ስድስት ካርበኖች እና ስድስት አቶሞች ለማስተካከል ለብዙ ዓመታት በትጋት ቢጥርም ጉዳዩን ለመፍታት የሚያስችል ትክክለኛ መዋቅር ማግኘት አልቻለም።

በድካም እና በመሰልቸት ጥያቄውን ወደ ድብቁ አእምሮው አዞረ። ብዙም ሳይቆይ የገዛ ጅራቱን ነክሶ እንደ ፒን ዊል የዞረ እባብ በድንገት ወደ አእምሮዉ ብልጭ አለለት።

ይህ ከስውር አእምሮው የተሰጠው መልስ ለረጅም ጊዜ ሲፈለግው የነበረውን የአተሞች 'ቤንዚን ሪንግ' ተብሎ የሚጠራውን መፍትሄ ሰጠው።

#በአጭሩ- የምትፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን፣ በድብቁ አእምሮህ ሃይል በእውነት የምታምን ከሆነ ድብቁ አእምሮህ ሁልጊዜ ሊኖርህ ወደማይችሉ መልሶች ሊመራህ ይችላል።

ንኡስ አእምሮህ የወሳኝ የአካል ክፍሎችህን ተግባር ብቻ ሳይሆን፣ ችግሮችን የመፍታት ብቃትም አለው- ልክ ለታዋቂው ኦርጋኒክ ኬሚስት እንዳደረገው።

የአንተስ የሕይወት ቤንዚን ቀመር ምን ይሆን? እስቲ ለድብቁ ለአእምሮህ ስጠውና እንዲፈታው አድርግ፡፡

ድብቁ አእምሮህን ኃይል ለማወቅና በትክክል ለመጠቀም ደግሞ ድብቁ አእምሮህ ድብቁ ኃይልህ መጽሐፍን እንድታነብ ትመከራለህ፡፡
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

#ድብቁ_አእምሮህ_ድብቁ_ኃይልህ መጽሐፍ


@the_motivators
@the_motivators
40 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 22:16:27 Channel photo updated
19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 22:08:16 #ማንም_የሚጎትትህ_አትሁን!

አንድ ቀጠሮ ያለበት ሰው በመንገድ እየተጣደፈ ሲጓዝ ሌላ ነገረኛ ሰው ገጠመው። ነገረኛው ቀጠሮ የረፈደበትን በስድብ ያጣድፈው ጀመር። ሰውየው ሰአቱን ይመለከታል፣ የቀጠሮውም ሰዓት ሊረፍድበት ሆነ። እናም ድምጹን ከፍ አድርጎ -

"ወዳጄ አሁን ሰዓት ረፍዶብኛል። የቀረህ ስድብ ካለ ስመለስ ትጨርሰዋለህ" ብሎ ትቶት መንገዱን ቀጠለ።

የዚህ ሰው እጣ ፈንታ በነገረኛው ሰው አልተወሰነም። ጸብ መፍጠር ይችላል።

ሲሰዳደብም እዛው መዋል ይችላል። ሆኖም የእሱ እጣ ፈንታ በማንም አልፎ ሂያጅ የሚገደብ አልነበረም።

ከመንገዱም አላስቀረውም።

የብዙዎቻችን ህይወት ከዚህ በተቃራኒ ነው። ሰዎች ከመንገዳችን እያስወጡ ወደራሳቸው አቅጣጫ ይወስዱናል። አንዱ ይመጣና ወደዚህ ይወስድሃል፣ ሌላው ወደዚያ ይጎትትሃል።

በዚህ አይነት መንገድ ምንም ነገርን ማሳካት አትችልም።

ለመጥፎ ሰዎች ንግግር ምላሽን መስጠት ስትጀምር ለእነሱ ተገዢ ባሪያ ትሆናለህ።

እንደፈለጉትም ያደርጉሃል።

ማንም የሚጎትትህ አትሁን!

@the_motivators
@the_motivators
57 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 08:51:35 #መንገድህን_ቀጥል!!!

1. የምትኖርበት ቤት ማንነትህን አይወክልም!

አሁን ያለህበት ቤት ወደፊት የምትኖርበትን ስፍራ እስክታዘጋጅ መቆያህ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የምትኖርበት ቤት ማንነትህን እንዲተረጉመው ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡ 

2. የምትሰራበት ስፍራ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን የምትሰራው ስራ ጨዋና የስራ ሰው የመሆንህ ማሳያና ለወደፊት ማዳበር ለምትፈልገው ነገር መሸጋገሪያ ድልድይ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የምትሰራው ስራህ የማንነትህ መለኪያ እንዲሆን ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

3. የምታገኘው ደሞዝ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን የምታገኘው የገቢ መጠን ራእህን በመከታተል ላይ ሳለህ ለጊዜው ያለህን ፍላጎት ማሟያና ቀዳዳ መድፈኛ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ ደሞዝህ የማንነትህን ደረጃ እንዲመድብ ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

4. የትምህርት ደረጃህ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን በጭንቅላትህ ውስጥ ያለው እውቀት ወደፊት ማወቅ ለምትፈልገው ነገር መነሻ፣ እንዲሁም ጥበብን ጨምረህበት የወቅቱን ሁኔታህን መግፊያ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የትምህርት ደረጃህ ሰው የመሆንህን ዋጋ እንዲጨምረውና እንዲቀንሰው ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

5. ሰዎች ስለአንተ የሚያስቡት ነገር ማንነትህን አይወክልም!

ሰዎች ስለአንተ የሚያስቡት ሃሳብ በመላ ምት ላይ የተመሰረተ፣ ከራሳቸው ምልከታ፣ ውስንነትና ልምምዳቸው ጋር የተዛመደ፣ ማመን የሚፈልጉትን ነገር እንደምክንያት የሚጠቀሙበት ሁኔታ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ማንነትህን እንዲተረጉሙት ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

ከላይ የዘረዘርኳቸውን እውነታዎች በሚገባ ስትገነዘብ በዙሪያህ ካሉ ሁኔታዎች ባሻገር ዘልቀህ የመሄድ አቅም ይሰጥሃል፡፡ ይህንን ሃሳብ በመታጠቅ ቀና ብለህ ራእይን ተመልከት፣ እቅድን አውጣ፣ ባለህ አቅም የመጀመሪያዋን እርምጃ ተራመድ፣ ግራና ቀኝ ሳትል በርትተህ መንገድህን ቀጥል . . . ትደርሳለህ !!!

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ


@the_motivators
@the_motivators
78 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 20:40:45 አሜሪካዊው ቢሊዬነር #ስቲቭ_ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው አስደናቂ መልዕክት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
((ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው))

በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል ነው፣
,
አሁን፣በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ፣አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን ነገር ሁሉ ወደሗላ  ሳስበው ፣ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ፥፥
,
አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ ልትቀጥረው ትችላለህ፣ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን ልትቀጥረው አትችልም፥
,
ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ ፣ዳግም ሊገኙም ይችላሉ፥ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ ነገር ግን አለ… እርሱም #ህይወትህ ነው፥
,
አንድ ሰው የቀዶ ጥገና ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም፣
,
በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን  የህይወታችን መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ አይቀርም፣
,
★ለቤተሰብህ፣ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ አስቀምጥላቸው፣
,
★ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት ይኑርህ
,
እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት ፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል
,
በኪሳችን ውድ ቦርሳም ያዝን ርካሽ ቦርሳ ፣በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም ፣
,
የኣንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ ርዝመት አይቀየርም፣ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥፥የምንደርሰውም ያው እዚያው ቦታ ነው ፣
,
ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና  አድሮ የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም፣
,
ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፣
,
…የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ ይገባሃል
,
አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ ፣አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል  ቁልቁል ትወርዳለህ፣
,
እውነተኛው ደስታ የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት ብቻ ነው፥፥
ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ ፣በምትጫወተው ጨዋታ፣ በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ ፣
,
5 ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ …
ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ አታስተምራቸው፥፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው፥፥ ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል፣
,
ምግብህን እንደ መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ ፣
,
የሚወድህ ሰው በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል፣
,
"ሰው ሆኖ በመፈጠር"ና "ሰው በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው፥
,
ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው፣
,
በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ሩቅ ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ

@the_motivators
@the_motivators
86 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 15:18:25 #ነጻ_እስክትሆን_ባሪያ_ሁን!

ኒቼ አንድ ድንቅ ሃሳብ አለው - ስለ ነጻነት።

እሱ እንደሚያምነው "ባርነት" ባላደገው ሰውና በነጻው ሰው መሃል ያለ ነው። ነጻ ለመሆን መጀመሪያ ባርያ መሆን አለብህ።

ለተወሰነ ጊዜ ለማይለወጥ፣ ለማይቀየር ስነስርዓትም መገዛት ይኖርብሃል፤ ነጻነትህን እስክታውጅ ድረስ።

ለምሳሌ ፈረንሳይኛ ቋንቋን መማር ፈለግክ፤ ስትጀምረው ቀላል አይሆንም።
ምንም የምታውቀው የፈረንሳይኛ ቃልም የለም። ብዙ ሺ ነገሮችንም ማስታወስ ይጠበቅብሃል።

እንደ ጀማሪ ትኮላተፋለህ፣ ትሳሳታለህ፣ ትወድቃለህ፣ ትነሳለህ። እናም ያለህ ብቸኛ አማራጭ ራስህን ለስርዓት ማስገዛት ነው።

"ይህን አደርጋለሁ፣ በቀን ውስጥ ይህን ያህል ቃላትን..." እይዛለሁ እያልክ የማይለወጡ ህጎችን ታወጣለህ። ፈረንሳይኛ ቋንቋ እያንገሸገሸህ የምትማረው ሳይሆን ወደኸው የምታደርገው እስኪሆን ድረስ ነጻነትህን ለማግኘት ትታገላለህ፤ የመጨረሻ ግብህ የሚሆነውም ነጻነትህን ማግኘት ነውና።

ነጻ እስክትሆን ድረስ ባሪያ ሁን- ባሪያ ሆነህ ግን እንዳትቀር ተጠንቀቅ፡፡

@the_motivators
@the_motivators
44 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 18:59:39 #ሊሞቱ_የደረሱ_ሰዎች_የሚቆጫቸው_10_ነገሮች

#Ethiopia  | በተለያየ ህመም ምክኒያት በህይወት ጥቂት ጊዜ የቀራቸው ሰዎች ቀሪ ጊዜያቸውን ያለ ስቃይ እንዲያሳልፉ ህክምና የሚያገኙበት ቦታ Hospice ይባላል። ሆስፒስ ውስጥ የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች እነዚህን ከጥቂት ሳምንታት እስከ ጥቂት ወራት የቀራቸው ሰዎች በህይወታቸው ምን እንደሚቆጫቸው ጠይቀዋቸው የሚከተሉትን 10 ነጥቦች አግኝተዋል።

1) ደስተኛ አልነበርኩም- ህይወቴን በሚገባ enjoy አላደረግሁም።

2) በእውቀት ራሴን አላሳደግሁም። ለመማር ብዙ እድል ነበረኝ ግን አልተማርኩም።

3) እራሴን አልተንከባከብኩም-ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም፤ ስፖርት አልሰራሁም፤ አመጋገቤ ላይ አልተጠነቀቅኩም፤ የጤና ምርመራ በሰአቱ አላደረግሁም።

4) የኖርኩት በቂምና በጥላቻ ነው-ሁሉም ነገር እንደዚህ ማለፉ ለማይቀር ለምን በቂምና በጥላቻ ራሴንም ሰዎችንም ጎዳሁ?

5) ለቤተሰቤ ጊዜ አልሰጠሁም-ላይ ታች ስል ከልጆቼ ጋር አልተጫወትኩም፤ ወላጆቼን እንደምወዳቸው አልነገርኳቸውም። አብሬያቸው ጊዜ አላሳለፍኩም።

6) ሰዎችን አልረዳሁም- ብዙ የእኔን እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ነበሩ። አቅሙ እያለኝ እኔ ግን 'ቢዚ' ስለነበርኩ አልደረስኩላቸውም።

7) ህልሜን አልኖርኩም- ለብዙ አመታት ለአንድ መስሪያቤት ተቀጥሬ ነው የሰራሁት እንጂ የራሴን ህልም አልኖርኩም።

8) ያለምክኒያት ነው የለፋሁት- በማይጠቅሙኝ ነገሮች ተጠምጄ በጣም ስለፋ ነበር።

9) ለሰዎች ፍቅሬን አልገለፅኩም- ለምወዳቸው ሰዎች 'እወድሀለሁ' ወይም 'እወድሻለሁ' አላልኩም።ፍቅሬን ከመግለፅ ይልቅ እኮሳተራለሁ።

10) ሀይማኖትን እንቅ ነበረ- መንፈሳዊነትን እጠላ ነበር። አሁን መጨረሻዬ ላይ እስከምደርስ ወደ አምላኬ ዞር አላልኩም ነበር።

ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ Dawit Dreams ላይ ከተናገረው የተወሰደ።

ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም። በየሰአቱ በአለማችን 7500 ሰዎች ይሞታሉ። በየቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ 180ሺ ሰዎች ይሞታሉ። ሞት ማን ጋር መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም።  ደስተኛ ሆነን፣ ህልማችንን እየኖርን፣ ራሳችንን እየተንከባከብን፣ብዙም ኮስታራ ሳንሆን፣ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ጊዜ እያሳለፍን በይቅርታ ልብ እንዲሁም በመንፈሳዊነት መኖር ሞት ሲመጣ እዳንፀፀት የሚያግዙ ነጥቦች ይመስሉኛል።

@the_motivators
@the_motivators
29 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 17:15:58 #አትዋሽ_በፍጹም_አትዋሽ!

ከፍ አድርገህ አልም፡፡ ትኩረት ይኑርህ፡፡ ማስተካከል የምትችለውን ነገር አስተካክል፡፡ ባለህ እውቀት አትታበይ፡፡ ፍፁም የሆነ ኩራት ባለመቻቻል፣ በጭቆና፣ በማሰቃየት እና በሞት ስለሚገለጥ ትሁት ለመሆን ጥረት አድርግ።

የራስህን ብቁ አለመሆን፣ ፈሪነት፣ ተንኮለኝነት፣ ቂም እና ጥላቻ እወቅ።

ሌሎችን ከመክሰስህ በፊት እና የዓለምን ጨርቅ ለመጠገን ከመሞከርህ በፊት የመንፈስህን ክፋት ተመልከት። ምናልባት ጥፋቱ የዓለም ሳይሆን የአንተ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባት አላማህን ስተህ ይሆናል፡፡ ምናልባት የእግዚአብሔር ክብር ጎድሎህ ይሆናል፡፡ ምናልባት ኃጢአተኛው አንተ ትሆናለህ፡፡

ሁሉም ለዓለም አቅም ማጣት እና የክፋት መስፋፋት ያደረግከው አስተዋፅኦ ሆኖ ይመዘገባል፡፡

ከሁሉም በላይ በፍጹም አትዋሽ! ስለምንም ነገር በጭራሽ አትዋሽ፡፡ ውሸት ወደ ሲኦል ከሚመሩ ነገሮች መካከል አንደኛው ነው፡፡

@the_motivators
@the_motivators
34 views✰✰(¯`*•.Đāvě .•*´¯)✰✰, 14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ