የሰርክ ፀሎት የማያረጅ ፣ የማይቀጭ ፣ ወረት አልባ ፍቅር ስጠኝ ፤ ማግኘቴ ውስጥ የምሰጠው | The Motivator
የሰርክ ፀሎት
የማያረጅ ፣ የማይቀጭ ፣ ወረት አልባ ፍቅር ስጠኝ ፤ ማግኘቴ ውስጥ የምሰጠው ፣ የማግዘው ፣ የሚደሰት ይኖረኝ ዘንድ ቸር ልብ ስጠኝ ፦
የምችለውን ችግር ስጠኝ ፣ መኖሬ በሰው ቸርነት ይቀጥል ዘንድ የምለምን አልሁን ፦
ሳጠፋ ይቅርታ የሚጠይቅ ልቦና ስበደል ይቅርታ አድራጊ ልብ ስጠኝ፦
ገመና የምሸሸግ ፣ ብልግናን የማላጎላ ፣ ዘመዴ የሆነውን የሰው ልጅ የምወድ እና የምረዳ አድርገኝ ፦
እንግዳ እንደሆንኩ ስኖር በዚች አለም ይገባኝ ዘንድ ልቦናዬን አብራልኝ
ስለሆነልኝ ፣ ስለምታረግልኝ ነገር እኔ ባሪያህ አመሰግንሃለሁ
አሜን
@the_motivators