Get Mystery Box with random crypto!

# Development_እና_Happiness በኢኮኖሚ ማደግ እና የዜጎች ደስተኝነት ምን ያገናኛቸዋል | Tesfaab Teshome

# Development_እና_Happiness
በኢኮኖሚ ማደግ እና የዜጎች ደስተኝነት ምን ያገናኛቸዋል?
*********
ለምሳሌ፡- ከፍተኛ የገቢ ደረጃ ላይ የደረሰ አንድ ሰው
የሚኖርበት አካባቢ ንጹ ካልሆነ፤ ልጆቹን የሚያስተምርበት ጥሩ
ትምህርት ቤት ከሌለ፤ ከፍሎ የሚታከምበት ጥሩ ሃኪም ቤት
ከሌለ፤ ሰው በመሆኑ ብቻ የማይከበር ከሆነ፤ ወንጀል በመብዛቱ
አደጋ ይደርስብኛል ብሎ የሚሰጋ ከሆነ፤ የፈለገውን ሃይማኖት
የመከተል መብት ከሌለው፤ በሃይማኖት፤ በፖለቲካ ወይም በዘር
ሁኔታው መሸማቀቅ የሚደርስበት ከሆነ፤ በየመንገዱ የተቸገሩ
ሰዎችን የሚመለከት ከሆነ፤ የመንግስት ባለስልጣናት ተጽኖ
የሚያደርጉበት ከሆነ፤ ወዘተ ይህ ሰው ሃብታም ነው ወይስ ድሃ?
በ21ኛው ክፍለ ዘመን የዜጎችን የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ በነፍስ
ወከፍ ገቢ ብቻ መለካት ግዜ ያለፈበት ነው፤ ለዚህም ሲባል
በኢኮኖሚ መበልጸግ (Economic Development) መታየት
ያለበት ዜጎች ባላቸው የደስተኝነት ልክ ነው የሚሉ
ኢኮኖሚስቶች መብዛት ጀምረዋል በዋናነት Amartya Sen’s
እና Richard Layard ደስተኝነት የሰዎችን ጠቅላላ የኑሮ
ሁኔታን ከሚወስኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው ይላሉ
(Happiness is part of human well-being)፤ ብዙ
የጥናት ግኝቶች እንዳረጋገጡት የዜጎች ጠቅላላ ገቢ ሲጨምር
ዜጎች ደስተኝነታቸው አና እርካታቸው በተመሳሳይ መልኩ
እንደሚጨምር ነው፡፡
Richard Layard፡- የዜጎች የደስተኝነት ሁኔታ በ7 ምክንያቶች
ተጽኖ ይደርስበታል ይላል እነሱም የቤተሰብ ሁኔታ፤ የገቢ ሁኔታ፤
የስራ ሁኔታ፤ የማህበረሰብ እና የጓደኞች ሁኔታ፤ የጤና ሁኔታ፤
ነጻነት እንዲሁም ለራሳችን የምንሰጠው ዋጋ ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- 4 ጓደኛማቾች ቢኖሩ እና ከመካከላቸው ብቸና ገቢ
ያለው አንድ ሰው ብቻ ሆኖ በተዝናኑ ቁጥር ምን ያህል ግዜ እሱ
ብቻ ሂሳብ እየከፈለ ይቆያል? ይሄ ጉዳይ በማህበራዊ ግንኙኘቱ
ደስተኛ እንዳይሆን ያደርገዋል፤ ስለዚህ ብቻውን ዘወትር ወጪ
ላለማውጣት የጋራ ግንኙነቱን ሊቀንስ ይችላል፤ ነገር ግን ሁሉም
በቂ ገቢ ያላቸው ቢሆን ቶሎ ቶሎ እና ረጅም የመዝናኛ ግዜ
እንዲኖራቸው ያስችላል Richard Layard የሚለው ይህንን
ነው የጓደኞች ሁኔታ የሰዎችን የደስተኝነት ደረጃ ይወስናል፡፡
በዓለም ላይ ያሉ ሁሉም ሀገራት መሪዎችም ሆኑ ህዝቦች
በምድር ላይ የተሰጣቸው ሃላፊነት የሚከተሉትን የዜጎች የእድገት
ዓላማዎች ማሳካት ነው፤ ጥቂት የስካንድንቪያ(Scandinavia)
ሀገራት ሲያሳኩት አሜሪካንን ጨምሮ እጅግ በጣም ብዙ ሀገራት
እስካሁን ማሳካት አልቻሉም! ዓላማዎቹ…..
በቀዳሚነት ዜጎች ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን
እንዲሟሉላቸው ያስፈልጋል ማለትም ምግብ፤ ውሃ፤ ልብስ፤
ቤት፤ የጤና ሽፋን፤ ጥበቃ ወዘተ፤ ከዚህ ሲያልፍ ብዙ የስራ
እድል፤ የተሻለ ትምህርት፤ ባህላቸውን የመጠበቅ መብት፤
በራሳቸው ነገሮችን የማድረግ ነጻነት (Not being used as a
tool by others for their own ends) ፤ የመከበር፤
እውቅና የማግኘት፤ በራስ የመተማመን ሁኔታ፤ እንዲሁም
በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች የፈለጉትን አማርጦ
የመጠቀም እድል እና ከጥገኝነት የመላቀቅ አቅም እንዲኖራቸው
ማድረግ ነው፡፡

@Tfanos