Get Mystery Box with random crypto!

የምትኖሩት ኑሮ #ዋናውን ነው? ልጅ እያለሁ እናቴ የነበረንን ጥሩ #ብርድ_ልብስ ለሙቀትም ሆነ | Tesfaab Teshome

የምትኖሩት ኑሮ #ዋናውን ነው?


ልጅ እያለሁ እናቴ የነበረንን ጥሩ #ብርድ_ልብስ ለሙቀትም ሆነ ለምቾት እናውጣው ስላት ለክፉ ቀን ነው የተቀመጠው ትለኝ ነበር!


አንዳንድ ቤተሰቦች ቤት ጥሩ ሰሀን፤ ሲኒ፤ ብርጭቆ፤ መጥበሻ፤ ወዘተ በብፌ ውስጥ ተቆልፎበት በተጣመመ ሰሀን መመገብ፤  በተሸረፈ ሲኒ መጠጣት ልምድ ነው።


አንዳንዶች ጋር ልብስ ሳይቀር ቀን እየጠበቀ ቁም ሳጥን ውስጥ ተንጠልጥሎ በዓመት አንዴ ብቻ ሊለበስ ይችላል (በዓመት አንዴ ሲዘንጥ ለራሱም ለሌሎችም እንግዳ ይሆናል!)።


የተለያዩ የኢኮኖሚክስ አስተምሮቶች ውስጥ የሰዎች ህይወት ወደ ፊት ባሉ ቀናት እንደሚመጣ ነው የሚመስሉት!


በኢኮኖሚክስ ቁጠባ መሰረታዊ ምክር ነው! ስለዚህ ከወጪ ቀንሶ መቆጠብ ግድ ነው #ለምሳሌ፦ ከጥሩ ምግብም ሆነ መጠጥ መቀነስ፤ ጥሩ ከመልበስ መቀነስ፤ ከመዝናናት መቀነስ፤ ወዘተ ማለት ነው።



አብዛኛው ኢኮኖሚያዊ ጥናቶች ገቢ ትዳር ከመያዝ እና ከልጆች ቁጥር ጋር ያለው ግንኙነት ቀጥተኛ ነው! #ለምሳሌ፦ ለመሰረታዊ ወጪዎች ገቢ ካልበቃ ትዳር ገቢው እስኪገኝ መቆየት አለበት የሚል ስሜት አለው! የልጆች ቁጥርም በተመሳሳይ።


#ለምሳል፦ ትዳር ለመያዝ፤ ልጅ ለመውለድ፤ ልጅ ለመድገም፤ ወዘተ መጀመሪያ ማሟላት ስለሚኖርባቸው ጉዳይ የሚያስቡ ሰዎችን የምትመለከቱት እድሚያቸው የደረሰ ቢሆንም #ወደፊት የሚል ቃል አለው!


#ለምሳሌ፦ ደሞዛቸው ዝቅተኛ ሆኖ ምንም ሳይኖራቸው ከሚበሉት ከሚጠጡት ቀንሰው ከ4 ዓመት በኋላ ትምህርቱ የተሻለ ገቢ አስገኝቶኝ #ወደፊት የምፈልገውን አደርጋለሁ የሚሉም አሉ።


#ለምሳሌ፦ ብዙዎች ለጡረታ ጊዜዬ በሚል ከመዝናናቱም ከሌሎቹም ቀንሰው #ወደፊት ለሚባለው Undefined ለሆነው ጊዜ ቅድሚያ ይሰጣሉ።


የዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ሰዎች #ወደፊት እንዳሉ ማሰባቸውን ያሳያል! የኢኮኖሚክስ አስተምሮቶችም ሰዎች እና ድርጅቶች #ዛሬ የሚያደርጉት ውሳኔ በሙሉ #ነገ እንዳለ በማመን ነው።


#ለምሳሌ፦ ገቢ ማሳደግ (Income Maximization)፤ ወጪ መቀነስ (Cost Minimization)፤ እርካታ መጨመር (Utility maximization) የሚሉ የኢኮኖሚክስ ሃሳቦች ከዛሬ በተሻለ ነገን እርግጠኝነት የጎደለው በመሆኑ ወደፊትን የሻለ ትኩረት ስለመስጠት ነው።


ይህንን አስተምሮት እየተከተሉ ከሆነ ግለሰባዊ ግብ እና ከተለመደው ማዕቀፍ የዘለለ ነገር ሊኖር እንደሚችልም ማሰብ ተገቢ ነው።



#ለምሳሌ፦ በሰፈራችሁ ወይም መስሪያቤታችሁ  "ያሰኘውን ሳይበላ!፤ እንደጓደኞቹ ደህና ልብስ ሳይለብስ እና በስራ ተወጥሮ አንድ ቀን ሳይዝናና ሞተ!" የተባለ ሰው አላጋጠማችሁም?


ጥያቄው ወደፊት መቼ ነው? ደግሞ ችግሩ ይህ ወደፊት መቼ እንደሆነ አለመታወቁ ነው!


የመኖሪያ እድሜ ጣሪያን ያለፈ ጎልማሳ ወደፊትን ማስቀደሙ አይቀርም! አዛውንቶችን ጠጋ ብላችሁ አውሯቸው ለወደፊት ሲሉ ዛሬ የሚተውት ብዙ ነገር አላቸው።


አንዳንድ ሰዎች በሰራሁት ገንዘብ የተሻለ ካልተመገብኩ፤ የተሻለ ቤት ውስጥ ካልኖርኩ፤ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ሰውነቴን እና አዕምሮዬ ዘና እንዲል ካላደረኩ፤ ጥሩ ስሜት የሚፈጥርልኝን ንፁህ እና አዲስ ልብስ ካለበስኩ፤ ወዘተ ህይወቴን መቼ እኖራለሁ ይላሉ።


አንዳንዶች እኔን ጨምሮ እየኖርኩ ያለሁት እና ይበልጥ ዋጋ የምሰጠው #ለዛሬ ነው ነገር ግን የዛሬ ምቾቴ በቀጣይ ጊዚያትም እንዳላጣው ስለወደፊት ማሰብም መዘጋጀትም ያስፈልጋል በሚል የሚኖሩ አሉ።


ዋናው ጉዳያቸው ወደፊት እንደሆነ በአመለካከትም ሆነ በተግባር የሚያምኑ ሰዎች ዛሬ እየኖሩ ያሉት ለመጪው ዋና ህይወታቸው ዝግጅት እንደሆነ ያስባሉ።



ወደፊት የሚለው ጊዜ ግብ ወይም መስፈርት ከሌለው ግልፅ ስለማይሆን ሰውየውን ህይወቱን ሙሉ እንደደካማ እየቆጠረ እንዲኖር ሊያደርግ ይችላል።


#ለምሳሌ፦ ትዳር የምመሰርተው ቤት እና መኪና ሲኖረኝ ነው ያለ ሰው በ40 ዓመቱ ቤትም መኪናም አግኝቶ በ45 ዓመቱ ቢያገባ እና ቢወልድ ልጁ 18 ዓመት ሲሞላው Already አዛውንት ሆኗል (63 ዓመት)!



በ30 ዓመቱ አባት ሆኖ ቢሆን የ48 ዓመት ጎልማሳ እና የ18 ዓመት ወጣት መዝናኛ ቦታ ቢሄዱ ጨዋታቸው ተቀራራቢ ይሆን ነበር! ዛሬውን እየኖረ ወደፊቱን ማሰቡን ባያቆም እንደማለት ነው!

Via The Ethiopian Economist View

@Tfanos