Get Mystery Box with random crypto!

⚀ ክፍል አምስት ⚀ ......➲ በስልኬ በሻሸመኔ እና በሀዋሳ ከተማ መካከል ጥቁር | የኔው ታሪክ 8315

⚀ ክፍል አምስት ⚀



......➲ በስልኬ በሻሸመኔ እና በሀዋሳ ከተማ መካከል ጥቁር ውኃ ተብላ በምትጠራበት ቦታ የበቀለውን ተወዳጁን የሙዚቃ ንጉስ የድምፃዊ ታምራት ደስታን ውብ ትዝታ እየሰማሁ ወደ መናፈሻው ተቃረብኩ።
የሙዚቃው ስሜት በለሆሳስ በውስጤ እየተርመሰመሰ ከንፋሱ ጋር በትዝታ ሰረገላ ላይ በደመና ክምር ውስጥ ይዞኝ እየነጎደ ነው።
ድምፁ በልጅነታችን በተረት የምናውቃትን የተረት ከተማ ኩልል አድርጎ ያስቃኛል። የግጥም እና የዜማው ቁርኝት የልቤን በር ከፍቶ አንድን ሰው እንዳስብ እያደረገኝ ነው።በሌላ በኩል ክረምቱንም በግጥሙ ከትቦታል።
....... የደጃፌን መዝጊያ ክፍት አድርጌው ነበር
ዛሬም አልተዘጋም ሳትመለስ ስትቀር
አይኔ በእምባ ጭጋግ እንደተጋረደ
ስንት ሰኔ ጠብቶ ስንት ክረምት ሄደ

እየቆረቆረኝ እያሰረኝ ከእግር እስከ ራሴ
አጎዛው ሊጥለኝ ሲታገለኝ ተረበሸች ነፍሴ..

እያለ ይቀኛል።ግጥም እና ዜማው እንደ ድር እና ማግ ከድምፁ ጋር ተሰፍቷል ማለት ይቻላል። ሙዚቃውን እናጣጣምኩኝ መናፈሻው ጋ ደረስኩኝ። ሁሌም መናፈሻው ጋር ስደርስ ማዘውተሪያው ፊት ለፊት የድንች ጥብስ ከሚሸጡት ሰዎች ድንች ገዝቶ እየበሉ መሄድ ወደቤት መመለስ ልምዴ ነው። ሙዚቃው ከስሜቴ ጋር ዘለአለማዊ ህያው ምጥቀትን ያላበሰኝ ያህል ከደም ዝውውሬ ጋር የተዋሃደ መሰለኝ።
... አንቺው ጋር ይቀመጥ እባክሺ የፍቅሬ ትዝታ
የማትመጪ እንደሆን ምን አጥቼ እኔ ልንገላታ

ማዘውተሪያውን ተሻግሬ የጅማ ሙዚየሙ በር አከባቢ ስደርስ ከፊት ለፊቴ ያየውትን ማመን አቃተኝ። ልቤ በደስታ ይሁን በድንጋጤ ቶሎ ቶሎ ትመታ ጀመር። ጭንቀት የመከነበት ፤ ደስታ የተንጠፈጠፈበት ፊት አስተዋልኩ። ስታየኝ ፈገግ አለች። እኔም ፈገግኩ። ፍሌም ናት።
በዚህ የመልዓከ ሞት ፈረስ መጋለቢያ ሜዳ በመሰለው ጭጋጋም ምሽት እሷን ማግኘት መታደል ነው ስል አሰብኩኝ።
አንዳች ደስታ ውርር ሲያደርገኝ ይሰማኛል።
የፍሌም ፀዓዳ መሳይ ቀይ ፊቷ እና የሲኦል የፍም ገላ የመሰለው ከንፈሯ ሸሽቶ ጥርስዋ ብቅ ሲል ጉራማይሌዋ በምሽቱ ጭላንጭል ብርሃን ሲታየኝ አለማንም ከልካይ ተንደርድሬ ሄጄ አቀፍኳት። ምንም አላለችም ይልቁንም አፀፋዋን በማቀፍ መለሰች።
"ግሩሜ እንዴት ነህ?" አለችኝ ፈገግታዋ ከፊቷ ሳይረጋ ከለበሰችው ኮት ጋር ትልቅ ሰው መስላለች።..............


ክፍል ስድስት ይቀጥላል........



▃▅▆█ ፍሌም █▆▅▃
https://t.me/teztash
https://t.me/teztash

@rediy21