Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━ ሴትን አላምንም ክፍል 9 | ሀበሻን Text Meme

​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━


ሴትን አላምንም

ክፍል 9

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ

እልፍ አእላፍ ሰዎች በድንኳኑ ዙሪያ ላይ ቁመዋል በሀዘን ልባቸው የተሰበረ ፣ ለእንባቸው ገደብ አላበጅ ያሉ ሴቶች ይታዩኛል። የማየው ነገር ህልም እንጂ እውን አይመስልም "እኔን ልጄ" የሚሉ የሲቃ ድምፆች ከትላልቅ እናቶች  ይሰማል። ውሃ ሆንኩኝ ፤ እየተርበተበትኩኝም ቢሆን ወደ ድንኳን ውስጥ ገባሁኝ ክፍት ወንበር ስቤ ተቀመጥኩኝ ማንን ልጠይቅ? አህላም የት ሄደች? ማንስ ነው የሞተው? መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎቼ የኔን የነገን ተስፋ በጉልህ የሚያሳዩ ወሳኝ ነጥቦች። ………" ልጇ ደህና ነው ሙቀት ክፍል ገብቷል ሚስኪን በወጣትነቷ ተቀጨች እስከ መቼ ድረስ ነው ግን በወሊድ ምክንያት የሚከሰት ሞት የሚያበቃው"የሚል ድምፅ ከወደ ጆሮዬ ዘልቆ ገባ … ልሳቅ ፣ ወይስ እልል ብዬ ድንኳኑን የሰርግ አዳራሽ ላስመስለው? የጐመዘዝው ህይወቴ ወደ ጣፋጭነት ሲቀየር ታየኝ ፣ የጠፋው ብርሃኔ ደምቆ ሲበራ ታየኝ። አህላም አልሞተችም እነሱ ጋር ግን የሆነ ሰው ሞትዋል ፤ ሞት ደሞ ለማንም አይቀርም መቅረት ያለበት ደግሞ ለአህላም ብቻ ነው አህላም አልሞተችም።


ልቤ ተረጋጋ ፤ ሰው እንዴት ለቅሶ ላይ ሟችን ያማርጣል የዚህች ልጅ መሞት ህልሙን የሚያጨልምበት ስንት ሰው አለ ? ጨካኝ! አልኩት እራሴን… ለራሴ ደስታ ስል በሰዎች ሞት ላይ ምሳለቅ ፍቅር ወይስ እራስ ወዳድነት ብቻ አላውቅም የማውቀው አህላም አለመሞቷን ነው። …… ድንኳኑን ለቅቄ ስወጣ በአይን የማውቀው የግቢያችንን ተማሪ አየሁት ጠጋ ብዬ ሰላም እንዴት ነህ? የሚለው ጥያቄዬ አስቀደምኩኝ እሱም ሞቅ ያለ ሰላምታውን ከሰጠኝ በሗላ ማን ሞቶ ነው? አልኩት የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ የክላሳችን ተማሪ እህት ነች ድንገት በወሊድ ምክንያት ነው የሞተችው አለኝ። oh የአህላም እህት አላህ "የጀነት" ይበላት አመሰግናለው ሰላም ሁን ብዬው አልፍኩኝ ማታ ደግሜ ስለመምጣ  ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ነበረብኝ ላዳው ውስጥ ገብቼ ወደ ትምህርት ቤት አቀናሁኝ ፤ አነዛን አስጠሊታ እና አስቀያሚ ምሽቶችን አልፌ ዛሬን ደርሻለው።  አይ ፍቅር እስረኛ አድርጐኛል ያውም በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ የሚያሳዝነው ያሰረችኝ መታሰሬን ፣ በእስሩ ውስጥ የሚደርስብኝን ስቃይ ምንም አታውቅም እሷም  ዛሬ የሀዘን እስር ቤት ላይ ነች። እኔም ጋር ድንኳን አልተደኮነም እንጂ የምወዳትን ልጅ ሳላይ 2 ቀን ሞልቶኛል ታድያ ከዚ በላይ ለእኔ ምን ዱብዳ አለ።

 ምሽቱን እነ አህላምዬ ጋር ላሳልፍ ብዬ ከትምህርት ቤት መልስ መኪና አስፈቅጄ ለቅሶ ቤት ሄድኩኝ። ከቀኑ ቀለል ያለ ሰው ቢኖርም አሁንም ሰዎች ይታያሉ አህላምን ማግኝት አለብኝ ግን እንዴት? የቤተሰቡ አባል የሚመስል ሰው ውሃ ይዞልኝ መጣ እኔም "ይቅርታ" ወንድም አህላምን  ማግኝት እችላለው?  ከተረጋጋች አልኩት? ትኩር ብሎ አይቶኝ ይቻላል ማን ብዬ ልንገራት? ማን ይበላት?

በመከራ ውስጥ ሆኖ ስለ አንቺ የሚያስበው  ፣ ጦርነትም ውስጥ ሆነ ስለ አንቺ ሰላም በብዙ የሚጨነቀው ፣ በመሞት ውስጥ ሆኖ ስለ አንቺ  በህይወት መኖር የሚያሳስበው፣ ወንጀለኛ ሆኖ ስለ አንቺ ፅድቅ ከእራሱ በላይ የሚያስጨንቀው  ሰኢድ ይበላት? ሰኢድ... ሰኢድ በላት አልኩት ከሃሳቤ መለስ ብዬ። …… ብዙ ሳይቆይ አህላምን ይዟት መጣ… ልጁንም  የመልካም ሰው መገለጫ አድርጌ አሰብኩት ፣ የፈረሰውን የፍቅር ድልድይ ገንቢ መሃንዲስ ነው ብዬ መሰከርኩለት ፣ የፍቅር ጥም ቆራጭ መልካም ሰው ከቶ ከሱ ውጪ እንዴት ይኖራል?


አህላምዬ አዝናለች ቢሆንም ግን በመምጣቴ ደስ ሳትሰኝ አልቀረችም ያንን ከውሃ እና ከምግብ በላይ አስፈላጊ መስሎ የሚታየኝ ፈገግታዋን ቸረችኝ። ወደ መንገዱ እየተራመድን

አህላምዬ?
አቤት…
እንዴት ነሽ በረታሽ?
አልሃምዱሊላህ ምን ማድረግ ይቻላል አላህ ያመጣውን አምኖ መቀበል ግድ ይላል።

"አብሽሪ አላህ ሶብር ይስጣቹ ከህይወት አስቀያሚ ነገር  ውስጥ የሚወዱትን ሰው ማጣት ነው። ሀዘንሽ ከልብ ይገባኛል ግን ሁሉም ወደ ማይቀረው ሀገር ተጓዥ ነው ፤ ሁሉም እንደ ታክሲ ሰልፍ በሞት መስመር ላይ ተሰልፎ ተራውን እየተጠባበቀ ነው ህይወቱን እየገፋ ያለው ፣ ተረኛ ሟችም በሰልፉ መስመር እስከቆመ ድረስ ጊዜው ሲደርስ መሞቱ አይቀርም። ዋናው ቁም ነገሩ መሞት አይደለም ከሞት በሗላ ያለ ህይወት ነው ሞትማ ለማን ይቀራል? ለዚህ አይደል የነገ ሟች የዛሬን ሟች ይሸኛል የሚባለው።  በርታ በይ ፤ በርትትሽ ቤተሰቦችሽን አበርቺ " ሰው ከሰው ሲለያይ አይደለም ወረቀትም ከወረቀት ላይ ሲቀደድ የስቃይ ድምፅ አለው" ሀዘንሽን እረዳለው እኔም አባቴን አጥቼ  በብዙ ተሰቃይቻለው። ግን መመለስ በማይቻል ነገር ላይ ቆዝሞ ማሳለፍ ትርፉ ሌላ ህመም ነው ትእግስት ፍሬዋ ጣፋጭ ነው ታገሺ።………

የገፋትን ሃይል ባላቅም እንባ እየተናነቃት እቅፌ ውስጥ ገባች  …… ከልብ አመሰግናለው  አውቃለው ለህይወትህ ትርጉም የነበረውን ሰው ካጣህ በኃላ የህይወትን
ጠአም ማግኘት ከባድ ነው ። ግን ዛሬ አንተን በማወቄ እድለኛ እንደሆንኩኝ ተሰምቶኛል ፤ ብዙ ሰው ያቃተው በደስታህ ጊዜ አብሮ መኖርና ማሳለፍ ሳይሆን በችግርና በመከራ ጊዜ ከወዳጁ ጎን ሆኖ ሀዘኑንና ስቃዩን አብሮ መካፈል ነው ዋናዉ ይህ ነዉ ሰኢዲዬ በሀዘኔ በህመሜ ሰዐት ከጎኔ በመሆን እና ብርታትና  ጥንካሬ እንዳገኝ ስለመከርከኝ የዛሬዋን ምክር አልረሳም ብላኝ አይንዋ ላይ የቀረውን እንባ አፈሰሰችው። እኔ እንባ የለኝም ትላንት ማታ ስለ እርሷ እያሰብኩኝ እያለው አንዲት የእንባ ዘለላ ቁልቁል በጉንጮቼ ኮለል ብላ ወረዳለች። እኔም "ወዴት ነው የምትሄጂው?"  በማለት ስጠይቃት በአይንህ ውስጥ የምትወዳት ሴት አለች "ለእኔ የሚሆን ቦታ አላገኘውም"  ብላኝ ከሄደች ቆይታለች ታድያ አይኔ ውስጥ አህላም ገብታ ለቅሶዬ ኬት ይምጣ።… … አህላምዬ እራስሽን ጠብቂ ነገ እመጣለው ብዬ ተሰናብቻት ሄድኩኝ ፤ ባትሄድ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ሰምቼ ቆምኩ ሰውነቴ አንዳች የፍቅር እና የመፈለግ ስሜት ወረረኝ እኮ አህላም እኔን እንዲ አለችኝ?  ፊቴን አዙሬ…  ልመለሳ? አልኳት…  አይ መሽቷል ቤት ማሚ ትጠብቅሃለች ስገባ ደውልልኝ አለችኝ።

ልቤ ፈነደቀ አህላምን ያገኝሗት መሰለኝ።  መኪና ወዳቆምኩበት ስፍራ እየተራመድኩኝ አንዳች ስሜት ዙር አለኝ ፊቴን አዙሬ ስመለከት አህላም ቁማለች  ደነገጥኩኝ…  ቀድማኝ እጇን አንስታ ቻው አለችኝ እኔም ቻው ብዬ በእጄ እንድትገባ ምልክት ሰጠዋት።  በፍጥነት መኪናዋን አስነስቼ ወደ ቤት ገሰገስኩኝ ልቤ ሀሴት አርድጓል አዲስ እድል አዲስ ቀን አዲስ ህይወት … ድንገት አንድ ነገር ታወሰኝ እና ፈገግ አልኩኝ ማሚ ሁሌም አንድ የሚያስቃት ግጥም አለ እሱን ትልና ትስቃለች።

ሚስቴና ሰበቧ
·
·
ለስጋዋ ስትኖር ነፍሴን አሞኝታ
አገኘኋትና ወንድ ጋር ተኝታ
ምነው ምን በደልኩኝ? ብዬ ስጠይቃት
እግሯ ስር ወድቄ በእንባ ስማፀናት
እንደለመደችው ሰበብ አዘጋጅታ
አንተ መስለኸኝ ነው አለችኝ ተነስታ።።

ስልኬ ጮኸ የቴክስት ድምፅ ነው መኪናውን ዳር አቁሜ ሳየው አህላም ነች።


ክፍል አስር ይቀጥላል….......


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን