Get Mystery Box with random crypto!

ሀበሻን Text Meme

የቴሌግራም ቻናል አርማ textememe — ሀበሻን Text Meme
የቴሌግራም ቻናል አርማ textememe — ሀበሻን Text Meme
የሰርጥ አድራሻ: @textememe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.28K
የሰርጥ መግለጫ

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╔╦═╦╦═╗
║ እንኳን ወደ ሀበሻን Text Meme ቻናል
በደና መጡ 👫 ║
║ ║
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╩
#እየተጫወትን - እንማማራለን🌎🙌👌
Don't forget to subscribe

ለ አስተያየት
@sanchozil10 & @eyoc7
For spam @bre1122_bOT

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 23:17:39 ​​እሱም እናቱ ለተስማማችበት ነገር ፍቃደኛ መሆኑን ተናግሮ ግን አንተን ማየት እንዳለበት ጠይቆ ዛሬ አንተ ባታውቅም ሱቅ መጥቶ አይቶህ ነው የሄደው ፤ ምላሹንም ለአጐትህ አሳውቆታል ከአጐትህ ጋር በዝርዝር እንዳወሩ እና በተግባቡት መሰረት የዛሬ ሳምንት ሽማግሌ እንዲላክ ቀን ተቆርጧል …… አህላምዬ አሁን ደንገጥ አለች ፈገግታ የተቀላቀልበት ዕንባዋን አፍስሳ ማሚን አቀፈቻት የእስካሁኑን ሰምታ የሽማግሌውን ቀን መቆረጡን ግን አላወቅችም ነበር… አዎ ወንድ ነኝ ዛሬ ግን ተሸነፍኩኝ ዕንባዬ ቀድሞኝ ወረደ አዎ ዕንባ " 99% ስሜት ሲሆን 1% ነው ውሃ" ስሜቴ ገንፍሎ ወጣ ማሚን አቅፍኳት ሕይወቴን አቀለለችልኝ ፣ የመከራውን ክምር የናደቸው መስሎ ታየኝ አህላምና እኔ ልንጋባ ሰርግ ብቻ ቀረ… ሽልማቴን አገኝሁኝ ምኞቴን በእጄ አስገባሁኝ ፤ የመጀመርያ ልጇን የምትድረው ማሚ ደስታዋ ወደር አጣ የደስታ ስካር እና ዕንባ ተፈራረቀባት ፤ ሶስታችንም ያለአንዳች አስካሪ መጠጥ በደስታ ብቻ ሰከርን ……… የካቲት 3 / 2004 ዓ/ል ሽማግሌ ተላከ እኔም የቤት ዕቃዎችን ከአህላምዬ ጋር ሟሟላት ጀመርን ፤ የሽምግልና ሂደቱ ብዙም አድካሚ አልነበርም በሁለታችንም ቤተሰብ መሀል ሽማግሌ ሁነው የተገኙት የሚተዋወቁ እና በብዙ ማህበራዊ ጉዳይ የሚገናኙ ሰዎች እንዲሁም ባባን የሚያውቁት ሰዎች ነበሩ የሰርግ ቀጠሮ ተያዘ…………...


ክፍል አስራ ሶስት ይቀጥላል


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
118 viewsEyoba, 20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:17:39 ​​​​​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━


"ሴት አላምንም"

ክፍል 12

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ

……… የራስምታቱ መንስዔ የድካም ስሜት እና ፀሐዩ እንደሆነ ስለገባኝ ፊቴን ታጥቤ ወደ መኝታዬ አመራሁኝ…ምሽቱ በንጋት ተተካ ህይወትም እንዲህ ናት የጨለመበት ጊዜውን ጠብቆ ወገግ ይልለታል ፣ ሳቁን ያጣ በቀኑ ይስቃል አየህ ለዚህ ነው አንተ አይደለህም የምትስቀው ጊዜህ ነው የሚስቀው የሚባለው…… ብቻ ነግቷል የዛሬው ማለዳ ይለያል ከአህላምዬ ጋር የፍቅራችን ጥንስስ የጀመርንበት ነው…… ማታ አህላምዬ ቴክስት ልካ ነበር " ባየሁህ ጊዜ የእኔ እንደሆንክ አንድ ነገር ነግሮኛል ልቤ ስለአንተ ጠየቀኝ እናም ቀስ በቀስ ልቤን ሞላህው ከጅዬህ ነበር በመጨረሻ አገኘሁህ አፈቅርሃለው" …… ልዩ የሆነ የፍቅርና የደስታ ስሜት ተሰማኝ እኔም… የዓለም ሴቶች ሁሉ እፊቴ እንደ ዝናብ ጠብ ጠብ እያሉ ቢመጡ አይኔ ባንቺ እንጂ በማንም አትሞላም የአይኔ ማረፊያ አፈቅርሻለው" ብዬ ከአልጋዬ ተነሳሁኝ ማሚ ቀድማኝ ተነስታ ስለ ነበር ሳሎን ስገባ ቁርስ ተዘጋጅቶ የእኔን መምጣት ነበር የሚጠበቀው……ከማሚ ጋር እየበላን በመሀል ስለእኔና አህላም ሁልንም ነገርኳት በህይወት ዘመኔ ያንን ፈገግታና ደስታዋን አይቼ አላውቅም … በሰሚራ ጉዳይ የነበረውን ጥርጣሬ በፊቷ ምላሽ ተወገደልኝ…… ያንን ከውብ አንደበቶቿ የሚወጣውን ምክሯን ማዥጐድጐድ ጀመረች።

የኔ ልጅ! ከአባትህ ሞት በሗላ አንድ ቀረኝ የምለው አንተ እና የአንተን ስኬት ነበር ፤ በአባትህ የቀረኝን ፍቅር በአንተ እሞላዋለው ብዬ አስብ ነበር ፤ አግብተህ እና ወልደህ ማየት ከምንም በላይ ለእኔ ስኬት እና እርካታ ነው። ተማሪ ነህ ብዬ ስለማስብ የማግቢያህ ጊዜ ይርቅብኛል… ግን በቂ ሃብትና ንብረት አለህ ባል ለመሆን እድሜ ሳይሆን አስተሳሰብ በላጭ ነው ፤ እድሜያቸው አርባ ሁነው ግን ጭንቅላታቸው የ 10 ዓመት እንዳለ ሁሉ ፣ እድሜው 20 ሁኖ አስተሳሰቡም የበሰለም አለ። ልጄ ማስጨነቅ እንዳይሆንብኝ ብዬ እንጂ ከሰሚራ ጋር ብታጋቡልኝ ብዬ አስብ ነበር ዛሬ ግን የራስህን ሰው አምጥተሃል ፤ ምርጫህን ልጋፋህ የምፈልግ ሰው አይደለሁም የመረጥካትን ልጅ ባላውቅም አንተን ልጄን ግን አውቅሀለው… ለልጆችህ እናት የምትሆንዋን እንደመረጥክ አምናለው… ልጄ ውበት እና መልክ አስፈላጊ ነው ግን የትዳር መሰረቱ እርሱ አይደለም እስኪ ልጠይቅህ? ለምንድን ነው ያፈቀርካት? የማሚ ጥያቄ ነበር መልካም እና ውብ ሴት ስለሆነች ፍቅርን ሰጥታ መቀበል የምትችል ንፁህ ሴት ስለሆነች ነው ማሚ……… ዕይታህ መልካም እና ጥሩ ነው ፤ ስለ ፍቅር ስታወራኝ ስለትዳር የነገርኩህ ለሁሉም ጥያቄዎች ብዙ ምላሾች ሊኖራቸው ይችላል ፤ ነገር ግን የመዋደድ እና የፍቅር ምላሹ ደግሞ ኒካህ ብቻ ነው። አንተም እርሷም ተማሪ ናችሁ ታድያ የእናንተ ልብ ፈቀደ እንጂ የቤተሰቦቻችሁ ፍቃድ ገና አልተወሰነም… ልጄ አትደንግጥ እኔ በአንተ ሙሉ እምነት አለኝ የምትሆንህን መርጠህ ካመጣህ እቀበልሃለው ሁሉም ቤተሰብ ግን እንደኛ ላይሆን ይችላል… የሁልም ልጅ ለቤተሰቡ ውድ እና እንቁ ነው ስለዚህ የቤተሰቧን ምላሽ አጣራ… ፈገግ ብላ ለአንተ ሌላ ሽማግሌ አያስፈልገውም እኔ ሽማግሌ እሆንልሃለው አለችኝ…… ቀጠል አድርጋ ልጄ? በቂ ሀብትና ንብረት አለን ከዚህ በሗላ ሱቁም መኪናው የአንተ ናቸው ፤ ደስተኛ ሁነህ እንድትኖርልኝ እፈልጋለው ከቻልክ ልጅቷን አምጥተህ አስተዋውቀኝ አለችኝ…… ልቤ በደሰታ ጮቤ ረገጠ ሁሉም እናቶች እንደ እኔ እናት ቢሆኑ ብዬ ተመኝሁኝ ግና የእናት መጥፎ የለውም… … የእኔና የአህላም ፍቅር የዘመናት ውጥን ሳይሆን የቀናቶች ድምር ውጤት ነበር ፤ ከእርሷ ጋር ባሰለፍነው ጊዜ የተገነዘብኩት ከእርሷ ውጭ መኖር እንዳማልችል ነው፡፡

የ 12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አለቀ ፣ ክረምቱም በነፃነት እና በፍቅር አሳለፍን ውብ ክረምት ፤ ክረምት አሁን ነው የጀመረው ወይስ ድሮም ነበር። ድሮም ከነበረ የአሁኑ ይለያል ካልነበረ ግን ክረምት ማለት እኔና አህላምነን ማለት ነው…… ማሚን ከአህላም ጋር አስተዋውቅያት እኔን ባይተወር አድርጋኛለች ፤ የየትኛውም እናት እንደ ባህላችን ከጋብቻ በፊት ከልጁ ሚስት ጋር የዚህን ያህል ቅርርብ እንዲኖር አትሻም ፤ የእኔ ማሚ ግን የሴት ልጅ ምኞት አልያም ደግሞ በልጇ ሚስት የመሸነፍ ጉጉት ባላውቅም ወሬያቸው ልዩ ሁኖዋል ሲያሻቸው እኔን ባዳ አድርገው ይጫወታሉ…… …እኔም ስራ ውዬ መግባት ከጀመርኩኝ ሰነባብቻለው ፤ አህላምም የኮሌጅ ትምህርቷን ቀጥላለች ፤ ማሚም የስራ ድርሻዋን እኔ ስለተረከብኩት አህላም እረፍት ስትሆን ገበያ እየወጡ ይመለሳሉ………… ምን ዓይነት ድንቅ እና ውብ እናት ነች ፤ እኔ እና አህላም እንደ ቀልድ ሁለት ዓመት ሞላን ማሚና አህላም ግን ግንኙታቸው የወራቶች ሳይሆን የዘመናት ነበር የሚመስለው… … ነፍሴ ሀሴት አደረገች በምድር ላይ ሁለት ውብ እና ውድ ነገሮች አሉኝ እናቴ እና አህላምዬ …… ዛሬ አዲስ ቀን ነው ማማ ሁለታችንንም በአንድ ጉዳይ ልታናግረን እንደምትፈልግና ሱቅ ቶሎ ዘግቼ እንድመጣ ጥብቅ ማሳሰብያ ሰጥታኛለች …… የማሚን ቃል አክብሬ በጊዜ መጥቻለው ማሚና አህላም አብረው ቁጭ ብለው እየተጫወቱ ነው…… ዛሬ ቁም ነገር የያዙ ይመስላል… ሰላም ብያቸው ልብስ ልቀይር ክፍሌ ስገባ የሚያምር አበባ እና ወረቀት ተቀምጦልኟል……" ከመተነፍስ እና አንተን ከመውደድ መካከል ለመምረጥ ብገደድ ሁቢ .... የመጨረሻውን እስትንፋሴን ተጠቅሜ አንተን መውደዴን እገልፅልሀለው" አፈቅርሃለው የወደፊት ባሌ ከሚስትህ አህላም የሚል ነበር። ፈገግ አልኩኝ እናቴ ሁሌም ቢሆን ዱዓዋ ወግ የሚገባት ሚስት ይስጠህ ነበር… ወግም ፍቅርም የሚገባትን ልጅ አድሎኛል…… የጓደኛዬ ወግ ትዝ ብሎኝ ሳቄን ለቀቅኩት ሰዒድ " እንደምንም ብለህ ፍቅር የምታውቅ እና የከተማ ልጅ አግባ ፤ የገጠር ልጅ አግብተህ ማታ ስትመጣ በር ላይ ጋቢ ለብሳ ነው የምትጠብቅህ ሲያሻትም ያንን ሁለት ዓይነት ካልሲ ለብሳ ፣ "romantic" ነገር አታውቅም ስለዚህ ተጣጥረህም ቢሆን የከተማ ልጅ አግባ አንተን ባታከብርህ የተጋባቹበትን ቀን ታከብርልሃለች ይልና ድክም ብሎ ይስቃል ፤ ሳቁ ታወሰኝ እና እንደሱ ፈገግ አልኩኝ……… ሳሎን ገብቼ እነ ማሚ ጋር ተቀላቅዬ አንድ ሁለት ጨዋታዎች ጣል አድርጌ ለማሚ መድረኩን ለቀቅኩላት…… ማሚ አንቺ እና ልጅሽ አህላም እኔን እንደ ጐረቤት ልጅ አድርጋችሁኝ ምን አድርግ ብላችሁ ነው የጠራችሁኝ "ኪራይ" በወቅቱ አልከፈልኩም ብዬ ፈገግ አልኩኝ በውስጤ ለአህላምዬ ለዛሬ ስጦታዋ ምላሽ ምን መስጠት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ ነበር…… ማሚም ቁጭ በል እስኪ ብላ …… ዛሬ የፈለግኳቹ የሁለታቹንም ግንኙነት ወደ ትዳር የመቀየር ሃሳብን ይዤ ነው…… ሰዒዲዬ አህላምን በደንብ አውርቻታለው በጨዋታ ጨዋታም የእርሷ ቤተሰብ ከአጐትህ ጋር ቅርርብ አላቸው… አንተ ሳታውቅ አህላም ለእናቷ እንድትነግራት እና ሃሳቧን እንድታሳውቀኝ በነገርኳት መሰረት…… መልካምን ምላሽ ይዛ መጥታለች …… አጐትህም አውቆ ደስ ብሎታል አሁን የቀረው ወንድሟ ነበር ለወንድሟ ደግሞ አህላምና እናቷ እንዲነግሩት ተነጋግረን ነበር… በእናቷ ሃሳብ አጐትህ እንዲጨመር አድርጌ ትላንት ማታ አናግረውት ነበር።
112 viewsEyoba, 20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:23:58 ​​​​​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━



ሴትን አላምንም

ክፍል 11

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ



ውበቷ ገደብ ጥሶ ተሸነፍኩኝ……የውቦች ተወካይ መሆኗ ፍንትው ብሎ ተገለጠልኝ ፤ የቆንጀዎች መሪ ደረቴ ላይ መኖሯ አቅም አሳጣኝ… ጥቂት የማይባሉ ፀጥታ የሰፈነባቸው ሰከንዶች ውቢቷ ደረቴ ላይ ተለጥፋ አለፉ ፡፡

ነፍሴ እንደ ጠዋት ፀሀይ እንደ ጠዋት ወገግታ አህላምዬን ናፍቋል ፣ ድንቅ ገጣሚያን ፣ ውብ ሙዚቀኞች ፣ ታዋቂ ጋዜጠኞች ፣ ከያኒያን ፣ ሰዓሊያን በዙሪያችን ስለእኛ ለመዘገብ የቆሙ መስሎ ታየኝ። …… ሁለታችንም በፍቅር ዓለም ውስጥ ሰጥመናል ፤ የሰውነታችን ሙቀት ከትክክለኛው የሰው ልጅ የሙቀት መጠን ያለፈ መሰለኝ። ድንቅ የመፈላለግ ስሜት…… አጠገቤ ያለችው ፀሀይ ወይስ ጨረቃ የማልጠራጠረው ከሁለት አንዱ አጠገቤ እንዳለ ነው……እምቡጥ ፅጌረዳ የመሰለው ከንፈሯ ውብነቱን ሳይለቅ እየተንቀጠቀጠ ተከፈተ ፤ አይኗን ጨፈን አድርጋ ከአንገቷ ቀና ብላ ወደእኔ ጠጋ አለች ሳናዛቸው ከንፈሮቻችን ተጋጠሙ… አንዱ እጄ  አንገቷን ሌላኛው እጄ ወገቧን ይዞ በፍቅር ዓለም ውስጥ ሰከርን ከልካይ የሌለበት ምሽት ይሄን ውብ ሰዓት ማንስ መጥቶ ይከለክለዋል ፣ የትኛውስ ማዕቀብ ያስቆመዋል፣ የከንፈሬን ማህተም ከንፈሯ ላይ አኖርኩኝ አዲስ ህይወት ሁለታችንም ወደ ማናውቀው ዓለም…  የፍቅር ዘማሪዎች ከያሉበት ወጥተው ውብ ዝማሬያቸውን አዜሙልን … … የዘላለም ይሁን ብለው መልካም ምኞታቸውን ተመኙልን ፣ ትንፏሻ ፍጥነት አለው የፍራቻ ትንፋሽ የማይሰማ የድንጋጤ ጩኸት ግን ደግሞ ደስታ የምን ሀዘን ማን ነው የሞተው የምትል ትመስላለች…… እውነትስ ማን ነው የሞተው?

እነዛ ትናንሽ ከዋክብቶች ስለእኛ ውብ እና ደማቅ ብርሀናቸውን ወደ ምድር ላይ አወረዱት …የማትጠገብ ሴትና የምድራችኝ ብቸኛዋ ባለ ውብ ከንፈር ፣ የክፍለ ዘመናችን ልዩ ሴት ከንፈሬ ላይ የዘላለም አሻራዋን  አኖረች ፤ ልለቃት አልፈለግኩም እሷም መሄድን አትሻም…የምናየው ነገር ሁሉ የሚያምር የምንሰማው ነገር ሁሉ ጥዑም ዜማ የተላበሰ መሰለ።

ከብዙ መሳሳም  ቡሀላ ተላቀቅን ህልሜ ዕውን ሆነ ለትንፋሽ ሳይሆን ለፍቅር ስሜት ከንፈሬን ከከንፈሯ ጋር አላተምኩኝ… … የመኖር ጉጉቴ ጨምረ የእርሷም እንዲሁ ፤ ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብዬ "አፈቅርሻለው" የማለዳ ሀሣቤ አንቺ ነሽ ብዬ አንሾኳሸኩ.. ምንም ማሰብ በማይኖርብኝ ግዜ እንኳን አስብሻለሁ...አንቺን ማፍቀር መከተል የህይወቴ አንዱ ምሣሌ አድርጌዋለሁ አፈቅርሻለሁ..ደጋግሜም አፈቅርሻለው..ባንቺ ማፍቀር ውስጥ ቀኔን ጀመርኩ ምሽቴን ውብ አደረግኩኝ  ....ሽልማቴ ነሽ የእኔ ፍቅር ብዬ ዓይኗን ተመለከትኩኝ  በፍቅር ዕንባ የተሞሉ ዓይኖቿ ውስጥ አንዳች የፍቅር ደሴት ይታየኛል…  ወደ ጆሮዬ ተጠግታ በሹክሹክታ "አፈቅርሃለው" ብላ ከንፈሬ ስማ ሳታየኝ ዞራ በፍጥነት ሄደች… በዚች ቀን የፍቅራችን መሰረት ተጣለ፣ የዛኑ ቀን ግንባታው ተጀመረ በጠንካራ የመፈላለግ መሰረት። 

ሄደች የሰላም እርግብ ከአጠገቤ ርቃለች ፤ ከደቂቃዎች በፊት ሁሉ ነገር እጄ ላይ ነበር ውበት፣ስብዕና፣ፍቅር አሁን ግን ሄዳለች… ህልም ወይስ አሁናዊ ሁኔታ?   በፍጥነት መኪናዬን አስነስቼ ጉዞ ወደ ቤት ………  ዛሬ የፍጥረት ውሃ ልክ የእኔ ሁናለች… ጭር ያለ ምሽት  ጭር ያለ መንገድ ላይ በፍጥነት እየነዳሁኝ ነው። ቀስ ብዬ የምነዳው ማሚ አጠገቤ ስትሆን ብቻ ነው መኪና  ስነዳ ያየኝ ሰው እና በህይወት እንቅስቃሴ የሚያቀኝ ሰው ሁለት ገፀ ባህሪያቶችን ይዤ የምጫወት ነው የሚመስለው። "ምን አልባት የአህላምዬን ፎቶ  30 ላይ አድርጌ" 30 የሆነው በምክንያት ነው ካላልኩኝ በስተቀር ይህን ባህሪዬን መቀየር አልቻልኩም … ……

ቃል ገባው በሰው ፊት
ይኸው በአደባባይ
ከአንቺ ሌላ ላላይ
የሱ ፍቃድ ሆኖ
አንቺን አግኝቻለው
ምን እፈልጋለው……

ይህ ውብ ሙዚቃ የዘፈን ምርጫ በሚሰኘው የሬዲዬ ፕሮግራም ላይ የተጋበዘው ዘፈን ነበር።እኔም ቃል ገብቻለው በአደባባይ ብቻ አይደለም በጨረቃ ፊት እስከመጨረሻው እስትፋንሴ ድረስ ከአህላምዬ ላልለይ ………… ቀን ማማን አላየሗትም ናፍቃኛለች ፤ ስለ ህይወት ስታወራና ስትመክረኝ ነገሮችን ቀላል ታደረግልኛለች… በ ባባ መሞት ልቤ ተጐድቶ ተስፋ በቆረጥኩበት ሰዓት የእድሜ ልክ ምክር የሚመስለው ንግግሯን እንዲ በማለት ነበር የነገረችኝ……… ሰዒደዬ እባክህ አትዘን !ሀዘን እኮ "ንፁህ ውሃ ስታይ መርዝ ፣ ፅጌሬዳ አበባ ስትመለከት ቁልቋል ፣ ማራኪ የአትክልት ቦታ ስታይ የተቃጠለ ምድረ በዳ ፣ በሰፊ ምድር ላይ ጠባብ እስር ቤት እንድታስብ ያደርግሀል።

በአደጋ የተነሳ ስታዝን ሌላ አደጋ ፣ በድህነትህ ምክንያት ስታዝን ድህነትን ትጨምራለህ ፣ ሀዘንህን ትተህ መልካምን ነገር አድርግ ለባባ የሚጠመቀውን አድርግለት አባትህ መልካም ሰው ነበር ስለ መስጠት ሰብኮ እና ሰጥቶ ነው ያለፈው ። ………ውዷ ባለቤቴ አንቺ የምትሰጪያት ጠብታ ከልብሽ ከሆነ በእጥፍ ይሰጥሻል። በምትሰፍሪው መስፈርያ ይሰፈረልሻል በሰጠሽው ልክ ይሰጥሻል ስለዚህ "አመድ አፋሽ ሆንኩ" ከማለትሽ በፊት አመድ ሰተሽ ከሆነስ? መስጠትን ብቻ ሳይሆን አሰጣጥሽ ወሳኝነት አለው አንድ አንዴ ከመንጠቅ የማይተናነስ መስጠትም አለ ይልና ግንባሬን ይስመኛል።

የኔ ባል? እለዋለው

ወዬ የአይኔ ማረፍያ የዘውትር መልሱ ነበር።

ንግግሮችህ ሁሉ ይማርኩኛል ስለው "መፅሀፉን ስለምትፈሪው እኮ ነው ግለጪው ያልኩሽን ሁሉ እርሱ ላይ ታገኚዋለሽ ይለኝና ይስቃል" እኔም አኩራፊዋ እናትህ ያኮረፍኩኝ መስዬ ወደ መኝታ ክፍል እገባለው እሱም ተከትሎኝ ይመጣል።

ሳታስበው እንባዋ ይቀድማታል ስለሱ ስታወራ… … ትዝታዬን እየቃየኝሁ መኪና ከፊት መኖሩንም እንኳን አላየሁም ነበር መኪናው አልፎኝ ስሄድ ነው የባንንኩት "አልሃምዱሊላህ" ተረፍኩኝ ዛሬ ለማሚ ሁሉንም ነገር መንገር አለብኝ ስለ አህላምዬ "እንደምትወዳት" ተስፋ አደርጋለው ማሚ ደስታዬ ደስታዋ ነው።  የመኪናውን በር አልፌ እንደገባሁኝ ማሚ ከሁለት ሴቶች ጋር ቁማለች ማምሸቴ ገባኝ ቢሆንም ስለ አህላምዬ ስነግራት እንደምትረጋጋ አሰብኩኝ…  "ሰሚራ" አልኩኝ ድንገት ልቤ እየደነገጠ ማሚ ስለዚች ልጅ ሁሌ ታወራኛለች ከቤታችን ሁለት ግቢ ቀጥሎ ነው መኖርያቸው።

እናቷ የማሚ ጓደኛ ነች ልጇም እርሷም ጥሩ ሰዎች ናቸው። ለእርሷ ነው ምድርህ ብላ አንድ ቀን ማሚ የቀለደችው ቀልድ ትዝ አለኝ እና ደነገጥኩኝ ፤ በህይወቴ የመጣች ስንክሳር መስላ ታየችኝ በማታውቀው ነገር እየሰደብኳት እንደሆነ ቢገባኝም  ግን  በዚህ ሰዓት ከአህላምዬ ውጪ ማንንም ማየትም ስለ ማንም ማሰብ አልፈልግም……ማሚ ና እንጂ ሰው ሰላም በል "ሰሚራ" ጐረቤት ሁናቹ እስካሁን እንዴት አትግባቡም ፤ ይሄኔ የሌላ ሰፈር ወንድ ልጅ ስልክ ከስልክሽ እኮ አየጠፋም አለች እናቷ… የሰሚራ እናት አራዳ ነች የእኔ ማሚ ደግሞ "የአራዳዎች አለቃ" ሰላምታ ተለዋውጥን ወደ ቤት ገባሁኝ ድንገት ራስ ምታት ጀመረኝ ጐንበስ ስል ከአፍንጫዬ ደም እየፈሰሰ ነው ኻዲማችን ደሜን ስታይ ጩኻ ስለ ነበር እነ ማሚም እየሮጡ መጡ።

ክፍል አስራ ሁለት ይቀጥላል ...

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
172 viewsEyoba, 12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:23:19 ​​​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━


ሴትን አላምንም

ክፍል 10

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ


መኪናውን ወደዳር አቁሜ ስመለከት ቴክስቱ የአህላምዬ ነው። ተጣድፌ ከፈትኩት

ሰኢዲዬ?
 … የሳቅ ረሀብተኛ ዘወትር አልቃሽ ሴት ሁኜ ነበር የተገናኝነው ፤ ያሳለፍኩት ህይወት ጨላልሞብኝ የህይወት ለዛው ጠፍቶብኝ ስባክን እና ስብከነከን ቆሜ እንዳልራመድ አቅም ያጣው ሆኜ ሳለው ነው መጥተህ የህይወትን ቀጣይ አቅጣጫ ያሳየህኝ እህቴ ለኔ ከምንም በላይ ነበረች። ከእርሷ ውጪ ህይወት ሞት መስሎ በሚታየኝ ሰአት ድንገት የህይወትን ብርሃን አብርተህ አሳየኝህኝ "ሁሉም ሰልፈኛ ነው ተራውን ጠባቂ "ያልከኝ ምክር እህቴን አስታወሰኝ አህላምዬ "ሰው ታመመ ብለሽ ብዙ አትጨነቂ ሁሉም ሰው ዛሬ ባይታመም ነገ ፣ ዛሬ ባይሞት ነገ ይሞታል የተራ ጉዳይ ነው ስለዚህ ለሚመጣው የህይወት ፈተና እራስሽን አዘጋጂ" ትለኝ ነበር።

 እርሷም ተራዋን ጠብቃ ሄደች ፤ ግን አንተን ተክታልኝ የሄደች መስሎ እንዲሰማኝ አደረግከኝ። እውነት በጠፋበት ዘመን የእውነት ሰው ሆነህ አሳይተህኛል ፤ በእጆችህ የነካሃቸው እግሮቼ ፣ ከጉድጓድ ውስጥ በእቅፍህ ያወጣህበት የትህትና ጥግ ፣ ወንድሜን ተክተህ  ከቤት ወደ ት/ቤት ያመላለስክበት ስብእናህ ከልቤ የሚጠፋ አይደለም ፤ ዛሬ ደግሞ ከመራራው ሀዘን መለስ ብዬ እንዳስብ ረድተህኛል ለዚህም ከልቤ አመሰግናለው ከትምህርት ቤት የቀርሁባት ያቺ ቀን እህቴ በጠና ታማ ስለ ነበር ነው።

ነግቶ እስከማይህ ናፍቆቴ ብዙ ነበር ጥላዬ መስለህ ትታየኛለህ አደራ ከጐኔ ሁነህ አበርታኝ………። ከአህላም የተላከው መልእክት ነበር

 " እውነተኛ ሳቅ እና ደስታ ውስጤ ሲፀርስ ተሰማኝ…  እሷን የእኔ አድርጌ አሰብኳት መላ አካለቴ ጆሮ ሆኖ ስለእርሷ ማዳመጥ ፈለገ ፣ ሁለመናዬ የእርምጃዎቿን ኮቴ ማዳመጥ ጀመሩ።

ተስፋ ጭንቅት እንዲሁም ፍቅር አንድ ላይ ተዋህደው ነፍሴን በፍቅር ውቅያኖስ ውስጥ ሲከቷት ታየኝ… አህላምን ሊወስዳት የመጣው ችግር  ሲወረፍ ታየኝ… … ምን ያህል በፍቅሯ እውር እንደሆንኩኝ ባየች ብዬ አስብ ነበር ፤ ዛሬ ግን የፍቅርን ጭላጭ ሳትጐነጨ አልቀረችም ቴክስቷ ለኔ ከምንም በላይ ዋጋ ነበረው… … የአንድ አንድ ሰው ኖሮም ሞቶም ጠቃሚነቱ ጉልህ ነው።

የአህላምዬ እህት ሞታ የሚወዋዳዱ ሰዎችን ህይወት ግን አስቀጠለች ፤  ህልሜን በእውኑ አለም ውስጥ ያገኝሗት መስሎ ታየኝ።  ማለዳ የወፎችን ድምፅ በእቅፌ ውስጥ ገብታ ስታዳምጥ…  በፍቅር ስንወዳደስ ፣ በፍቅር ስንጐራረስ ፣ በአንድ የህይወት ጣራ ውስጥ ህይወትን አብረን ስንቃኝ ታየኝ እና ፈገግ አልኩኝ።

ስልኬን አውጥቼ መልእክቴን አኖርኩላት……

አህላምዬ ከልብ አመሰግናለው እውነታው ይህ ነው………​ልቤ በአንቺነትሽ ሀሴት ተሞልታለች አንቺ በህይወቴ ምዕራፍ ከመጣሽ ጊዜ ጀምሮ አዲስ ተስፋ እና አዲስ ሃይል አግኝቻለው … አይኖቼም በድካም አይፈዙም ራስ ምታትም ሆነ ነስር ከዛች ልዩ ቀን በሗላ ተመልሶ አያውቅም ሀኪሜ ሁነሽ አዳንሽኝ ፈዋሼ ሁነሽ የመኖር ህልሜን በእጥፍ ጨመርሽው።

አህላምዬ?

ልቤ ዘወትር ስላንቺ ያስባል ፣ አይኖቼ አንቺን ብቻ ለማየት ያማትራሉ ፣ ጉልበቶቼ ወደ አንቺ
ለመጓዝ ይበረታሉ ፣ በልቤ ዙፋን ነግሰሽ ተሞሽረሻል  ………… ። መልእክቴ ተቋጨ "አፈቅርሻለው" ብዬ ላፍረጥርጠው? አዎ አፍቅርያታለው እሷን ወደ ህይወቴ ካመጣሁኝ ቡሗላ አይበርደኝም ፣ አይጠማኝም ከምግብ የበለጠ የሚያጠግበኝ፣ ከመጠጥም ይልቅ የሚያረካኝ፣ ፍቅሯ በውስጤ አለ። "እነዚህ ቃላቶች ሁሉ የኔ ቢሆኑም ፍቅሬን አይገልፁልኝም " ግን አሁን አፈቅርሻለው አልላትም"። ለሁሉም ጊዜ አለው።


የመኪናዬ በር ተንኳኳ …… አንዲት ላይዋ ደምቆ ውስጣ ግን አንዳች የመሸነፍ ስሜት የተላበሰች ሴት ነበረች "ሴተኛ አዳሪ"። "ማልወደው ቃል"

መስኮቱን ዝቅ ሳረገው ሳልናገር ፈጥና ወንድሜ ቦታውን ልቀቀው እንጂ የስራ ቦታ ነው ከፈለግክ አንዳችንን ይዘህን ሂድ ካልሆነ ተንቀሳቀስ አለች ቆጣ ብላ።

እሺ ብዬ መኪናዬን አስነስቼ ሄድኩኝ አሳዘነችኝ ግን ደግሞ ምን ታድርገው ። የረከሱ ወንዶች የገንዘባቸው መለኪያ የስሜታቸው ማርኪያ አድርገዋቸዋል ሴትን ልጅ እንዴት ለርካሽ ነገር ይጠቀሟታል?

 ሴትን ልጅ "ከእንብርቷ በታች ላለው አካሏ ሳይሆን ከአንገቷ በላይ ስላለው ጭንቅላቷ ብሎ የሚቀርብ ወንድ ከተማው ላይ የለም እንዴ"? የሴትነትን ዋጋ ያላወቁ ወንዶች ከስሜታቸው ቀድሞ ለህሊናቸው ቢያስቡ ምን አለ? አንዲትን ሴት ወደ መልካም ህይወት መምራት ከመከራ ህይወት ማውጣት የህሊና እረፍት እንጂ ሌላ ምንን ይሰጣል ?

እነዚህ ስጋ ነጋዴዎች! ሴትን አረከሷት አልኩኝ አንድ የግጥም ስንኝ ትዝ እያለኝ

የሌሊት ስጋ ቤት
ይሄ ስጋ መሸጥ ያተርፋል እያሉ
 ያዋጣል እያሉ
የቀን ሳያንሳቸው
እራፊ አሻርጠው ማታም ይወጣሉ
ስጋ እየተስማማው ስጋ እያጣፈጡ በላተኛው ሁሉ
ቀን የበሬ ገዝተው
 ባዋዜ አዋህደው ፤
 ሲቆርጡ እየዋሉ
 ሲጠብሱ እየዋሉ
ማታም እየጠጡ
 ነፍሳቸውን ስተው
 የሰው ስጋ ገዝተው
ዝሙት ይሰራሉ ፤
የበሬን ጥብስ ጥጋብ
 ፀሀይ እንደገባች በሰው ያበርዳሉ፡፡ አልኩኝ ።

በተደጋጋሚ እነ አህላምዬ ጋር በለቅሶው ሰበብ መሄድ አብዝቻለው ፤ አንዳች የመቀራረብ ስሜት ሁለታችንም ላይ ይታያል…… መመላለሴን ያዩና ስወጣ ከአህላምዬ ጋር የሚመለከቱኝ እየታዘቡኝ መስሎ ታየኝ "በፍቅሯ ሽባ ልፍልፍልስና ጠውላጋ ነው ብለው ያሙኝ እየመሰለኝ ፈራ ተባውን ተያይዤዋለው።

ይበሉዋ ደግሞ ምን ገዶኝ ልክ አይደሉ እንዴ ? በማላዘው አይኔ እየናፈቀችኝ ፣ በከደንኩት አይኔ ደግሞ እያየሗት አይደል? ቃል ባጣው ምላሴ አልሰብኳትም ፣ በድን አካለቴ እሷን አላለም ? የእርሷ ምርኮኛ ነው ቢሉ ምን ተሳሳቱ? ………… ዛሬ ከሌላው ጊዜ የበለጠ አምሽቻለው አህላምዬ መኪና ድረስ ልሸኝህ ብላ  አብራኝ ወጥታለች… ፈገግታዋ እየተመለሰ ፍንድቅድቅ ሁና እያተየችኝ ነው "አልሃምዱሊላህ" የሁለት ሰው ደስታ ተመለሰ የእኔም ፣ የእርሷም "በኔ ውስጥ እሷ አለቻ"………… አስፓልቱ ዳር ቆመን  ስለ ቤተሰብ እያወራን እርሷም መበርታት እንዳለባት እያወራን  አንድ መኪና ከላይ  እየተመዝገዘገ መጣ…………እጇን ስቤ ወደ ደረቴ አስጠጓሇት መኪናው አለፈ ፤ እኔና እሷ............

ክፍል አስራ አንድ ይቀጥላል……

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
209 viewsEyoba, 11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:22:29 ​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━


ሴትን አላምንም

ክፍል 9

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ

እልፍ አእላፍ ሰዎች በድንኳኑ ዙሪያ ላይ ቁመዋል በሀዘን ልባቸው የተሰበረ ፣ ለእንባቸው ገደብ አላበጅ ያሉ ሴቶች ይታዩኛል። የማየው ነገር ህልም እንጂ እውን አይመስልም "እኔን ልጄ" የሚሉ የሲቃ ድምፆች ከትላልቅ እናቶች  ይሰማል። ውሃ ሆንኩኝ ፤ እየተርበተበትኩኝም ቢሆን ወደ ድንኳን ውስጥ ገባሁኝ ክፍት ወንበር ስቤ ተቀመጥኩኝ ማንን ልጠይቅ? አህላም የት ሄደች? ማንስ ነው የሞተው? መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎቼ የኔን የነገን ተስፋ በጉልህ የሚያሳዩ ወሳኝ ነጥቦች። ………" ልጇ ደህና ነው ሙቀት ክፍል ገብቷል ሚስኪን በወጣትነቷ ተቀጨች እስከ መቼ ድረስ ነው ግን በወሊድ ምክንያት የሚከሰት ሞት የሚያበቃው"የሚል ድምፅ ከወደ ጆሮዬ ዘልቆ ገባ … ልሳቅ ፣ ወይስ እልል ብዬ ድንኳኑን የሰርግ አዳራሽ ላስመስለው? የጐመዘዝው ህይወቴ ወደ ጣፋጭነት ሲቀየር ታየኝ ፣ የጠፋው ብርሃኔ ደምቆ ሲበራ ታየኝ። አህላም አልሞተችም እነሱ ጋር ግን የሆነ ሰው ሞትዋል ፤ ሞት ደሞ ለማንም አይቀርም መቅረት ያለበት ደግሞ ለአህላም ብቻ ነው አህላም አልሞተችም።


ልቤ ተረጋጋ ፤ ሰው እንዴት ለቅሶ ላይ ሟችን ያማርጣል የዚህች ልጅ መሞት ህልሙን የሚያጨልምበት ስንት ሰው አለ ? ጨካኝ! አልኩት እራሴን… ለራሴ ደስታ ስል በሰዎች ሞት ላይ ምሳለቅ ፍቅር ወይስ እራስ ወዳድነት ብቻ አላውቅም የማውቀው አህላም አለመሞቷን ነው። …… ድንኳኑን ለቅቄ ስወጣ በአይን የማውቀው የግቢያችንን ተማሪ አየሁት ጠጋ ብዬ ሰላም እንዴት ነህ? የሚለው ጥያቄዬ አስቀደምኩኝ እሱም ሞቅ ያለ ሰላምታውን ከሰጠኝ በሗላ ማን ሞቶ ነው? አልኩት የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ የክላሳችን ተማሪ እህት ነች ድንገት በወሊድ ምክንያት ነው የሞተችው አለኝ። oh የአህላም እህት አላህ "የጀነት" ይበላት አመሰግናለው ሰላም ሁን ብዬው አልፍኩኝ ማታ ደግሜ ስለመምጣ  ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ነበረብኝ ላዳው ውስጥ ገብቼ ወደ ትምህርት ቤት አቀናሁኝ ፤ አነዛን አስጠሊታ እና አስቀያሚ ምሽቶችን አልፌ ዛሬን ደርሻለው።  አይ ፍቅር እስረኛ አድርጐኛል ያውም በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ የሚያሳዝነው ያሰረችኝ መታሰሬን ፣ በእስሩ ውስጥ የሚደርስብኝን ስቃይ ምንም አታውቅም እሷም  ዛሬ የሀዘን እስር ቤት ላይ ነች። እኔም ጋር ድንኳን አልተደኮነም እንጂ የምወዳትን ልጅ ሳላይ 2 ቀን ሞልቶኛል ታድያ ከዚ በላይ ለእኔ ምን ዱብዳ አለ።

 ምሽቱን እነ አህላምዬ ጋር ላሳልፍ ብዬ ከትምህርት ቤት መልስ መኪና አስፈቅጄ ለቅሶ ቤት ሄድኩኝ። ከቀኑ ቀለል ያለ ሰው ቢኖርም አሁንም ሰዎች ይታያሉ አህላምን ማግኝት አለብኝ ግን እንዴት? የቤተሰቡ አባል የሚመስል ሰው ውሃ ይዞልኝ መጣ እኔም "ይቅርታ" ወንድም አህላምን  ማግኝት እችላለው?  ከተረጋጋች አልኩት? ትኩር ብሎ አይቶኝ ይቻላል ማን ብዬ ልንገራት? ማን ይበላት?

በመከራ ውስጥ ሆኖ ስለ አንቺ የሚያስበው  ፣ ጦርነትም ውስጥ ሆነ ስለ አንቺ ሰላም በብዙ የሚጨነቀው ፣ በመሞት ውስጥ ሆኖ ስለ አንቺ  በህይወት መኖር የሚያሳስበው፣ ወንጀለኛ ሆኖ ስለ አንቺ ፅድቅ ከእራሱ በላይ የሚያስጨንቀው  ሰኢድ ይበላት? ሰኢድ... ሰኢድ በላት አልኩት ከሃሳቤ መለስ ብዬ። …… ብዙ ሳይቆይ አህላምን ይዟት መጣ… ልጁንም  የመልካም ሰው መገለጫ አድርጌ አሰብኩት ፣ የፈረሰውን የፍቅር ድልድይ ገንቢ መሃንዲስ ነው ብዬ መሰከርኩለት ፣ የፍቅር ጥም ቆራጭ መልካም ሰው ከቶ ከሱ ውጪ እንዴት ይኖራል?


አህላምዬ አዝናለች ቢሆንም ግን በመምጣቴ ደስ ሳትሰኝ አልቀረችም ያንን ከውሃ እና ከምግብ በላይ አስፈላጊ መስሎ የሚታየኝ ፈገግታዋን ቸረችኝ። ወደ መንገዱ እየተራመድን

አህላምዬ?
አቤት…
እንዴት ነሽ በረታሽ?
አልሃምዱሊላህ ምን ማድረግ ይቻላል አላህ ያመጣውን አምኖ መቀበል ግድ ይላል።

"አብሽሪ አላህ ሶብር ይስጣቹ ከህይወት አስቀያሚ ነገር  ውስጥ የሚወዱትን ሰው ማጣት ነው። ሀዘንሽ ከልብ ይገባኛል ግን ሁሉም ወደ ማይቀረው ሀገር ተጓዥ ነው ፤ ሁሉም እንደ ታክሲ ሰልፍ በሞት መስመር ላይ ተሰልፎ ተራውን እየተጠባበቀ ነው ህይወቱን እየገፋ ያለው ፣ ተረኛ ሟችም በሰልፉ መስመር እስከቆመ ድረስ ጊዜው ሲደርስ መሞቱ አይቀርም። ዋናው ቁም ነገሩ መሞት አይደለም ከሞት በሗላ ያለ ህይወት ነው ሞትማ ለማን ይቀራል? ለዚህ አይደል የነገ ሟች የዛሬን ሟች ይሸኛል የሚባለው።  በርታ በይ ፤ በርትትሽ ቤተሰቦችሽን አበርቺ " ሰው ከሰው ሲለያይ አይደለም ወረቀትም ከወረቀት ላይ ሲቀደድ የስቃይ ድምፅ አለው" ሀዘንሽን እረዳለው እኔም አባቴን አጥቼ  በብዙ ተሰቃይቻለው። ግን መመለስ በማይቻል ነገር ላይ ቆዝሞ ማሳለፍ ትርፉ ሌላ ህመም ነው ትእግስት ፍሬዋ ጣፋጭ ነው ታገሺ።………

የገፋትን ሃይል ባላቅም እንባ እየተናነቃት እቅፌ ውስጥ ገባች  …… ከልብ አመሰግናለው  አውቃለው ለህይወትህ ትርጉም የነበረውን ሰው ካጣህ በኃላ የህይወትን
ጠአም ማግኘት ከባድ ነው ። ግን ዛሬ አንተን በማወቄ እድለኛ እንደሆንኩኝ ተሰምቶኛል ፤ ብዙ ሰው ያቃተው በደስታህ ጊዜ አብሮ መኖርና ማሳለፍ ሳይሆን በችግርና በመከራ ጊዜ ከወዳጁ ጎን ሆኖ ሀዘኑንና ስቃዩን አብሮ መካፈል ነው ዋናዉ ይህ ነዉ ሰኢዲዬ በሀዘኔ በህመሜ ሰዐት ከጎኔ በመሆን እና ብርታትና  ጥንካሬ እንዳገኝ ስለመከርከኝ የዛሬዋን ምክር አልረሳም ብላኝ አይንዋ ላይ የቀረውን እንባ አፈሰሰችው። እኔ እንባ የለኝም ትላንት ማታ ስለ እርሷ እያሰብኩኝ እያለው አንዲት የእንባ ዘለላ ቁልቁል በጉንጮቼ ኮለል ብላ ወረዳለች። እኔም "ወዴት ነው የምትሄጂው?"  በማለት ስጠይቃት በአይንህ ውስጥ የምትወዳት ሴት አለች "ለእኔ የሚሆን ቦታ አላገኘውም"  ብላኝ ከሄደች ቆይታለች ታድያ አይኔ ውስጥ አህላም ገብታ ለቅሶዬ ኬት ይምጣ።… … አህላምዬ እራስሽን ጠብቂ ነገ እመጣለው ብዬ ተሰናብቻት ሄድኩኝ ፤ ባትሄድ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ሰምቼ ቆምኩ ሰውነቴ አንዳች የፍቅር እና የመፈለግ ስሜት ወረረኝ እኮ አህላም እኔን እንዲ አለችኝ?  ፊቴን አዙሬ…  ልመለሳ? አልኳት…  አይ መሽቷል ቤት ማሚ ትጠብቅሃለች ስገባ ደውልልኝ አለችኝ።

ልቤ ፈነደቀ አህላምን ያገኝሗት መሰለኝ።  መኪና ወዳቆምኩበት ስፍራ እየተራመድኩኝ አንዳች ስሜት ዙር አለኝ ፊቴን አዙሬ ስመለከት አህላም ቁማለች  ደነገጥኩኝ…  ቀድማኝ እጇን አንስታ ቻው አለችኝ እኔም ቻው ብዬ በእጄ እንድትገባ ምልክት ሰጠዋት።  በፍጥነት መኪናዋን አስነስቼ ወደ ቤት ገሰገስኩኝ ልቤ ሀሴት አርድጓል አዲስ እድል አዲስ ቀን አዲስ ህይወት … ድንገት አንድ ነገር ታወሰኝ እና ፈገግ አልኩኝ ማሚ ሁሌም አንድ የሚያስቃት ግጥም አለ እሱን ትልና ትስቃለች።

ሚስቴና ሰበቧ
·
·
ለስጋዋ ስትኖር ነፍሴን አሞኝታ
አገኘኋትና ወንድ ጋር ተኝታ
ምነው ምን በደልኩኝ? ብዬ ስጠይቃት
እግሯ ስር ወድቄ በእንባ ስማፀናት
እንደለመደችው ሰበብ አዘጋጅታ
አንተ መስለኸኝ ነው አለችኝ ተነስታ።።

ስልኬ ጮኸ የቴክስት ድምፅ ነው መኪናውን ዳር አቁሜ ሳየው አህላም ነች።


ክፍል አስር ይቀጥላል….......


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
191 viewsEyoba, 11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:02:02 ​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━




"ሴትን አላምንም"

ክፍል 8

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ

……አህላምዬ ዛሬ አልመጣችም ማንን ልጠይቅ ለማን አቤት ልበል? አህላም ከሌለች መንገዱስ የት አለ? እረ እግሬስ እንዴት እሺ ብሎ ይራመድልኛል? … ስልኬን ስላልያዝኩኝ ያለኝ አማራጭ በፍጥነት እቤት ደርሼ መደወል ነው።

ጥያት መሄዱ ቢያስከፋኝም አማራጭ አልነበረኝም። በአቅራብያዬ ባለ ታክሲ ገብቼ ተሰፋርኩኝ ታክሲው ሲንቀሳቀስ ቅር ፣ ቅር ይለኝ ጀመር። ከት/ቤት እየራቅኩኝ ስመጣ በመስኮት ዞሬ ተመለከትኩኝ ለብዙ ደቂቃዎች ስፈልጋት የነበረችው አህላምዬ በር ላይ ቆማ ማያት መሰለኝ…… የለችም ባር ባር አለኝ ሳላየት ላድር ነው ላለፉት ቀናቶች አስለምዳኝ የሄደችውን ጨዋታና ሳቅ ዛሬ የለም መንገዱ ላይ ያሉ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ ፣ የንዴት እና የብስጭት ፊት የሚታይባቸው ሰዎች መንገዱ ላይ ቁመዋል ለምን ተቆጡ እነሱም አህላምዬን ስላላዩ ይሆን?

ታክሲ ውስጥ የተከፈተው ለስለስ ያለው ሙዚቃ ከሃሳቤ አባነነኝ… የአህላምዬ ፈገግታ ፊቴ ድቅን እያለ ያስቸግረኛል ምን አለ ሰዎች "የሳቅን ስልት" ከሷ ቢማሩ ሰው ለስልኩ ጥሪ ከሚቀያይር እያደር አዲስ ሚሆነውን የአህላምዬን ፈገግታ አንዴ ጥሪ ቢያደርግስ? ታክሲው ጉዞውን ቀጥሎአል። እኔም ሙዚቃውን እየሰማሁኝ በሃሳቤ ገስግሻለው… ለእኔ ከአህላምዬ ጋር ያሳለፍኳቸው አጭር ቀናቶች የራሳቸው ገፅ አላቸው ዛሬ ግን አህላም የለችም። ትዝታዋ ግን አለ የረዥም ጊዜ ሳይሆን ሰሞኑ የሆነ ዛሬ ላይ ግን ትዝታ የሆነ እኔ በትዝታ ወደ ሁዋላ ተመልሻለው ፤ ታክሲው ግን ወደፊት ይገሰግሳል።

አህላምዬ ከመጀመርያው እለት ጀምሮ በተፈቀደላት መሠረት ልቤ ውስጥ ገብታ ፤ እግሮቿን አኮራምታ ቁጢጥ አለች ፣ ውላ ስታድር ተንፈራጣ ተቀመጠች ፣ በቆይታዋ ደግሞ በጀርባዋ ጋደም አለች ስትከርም ጭራሹን ጓዟን ጠቅልላ ይሄ መከረኛው ልቤ ላይ ተኛችበት።

እቤት ስገባ እናቴ የተለመደውን ፈገግታዋን አሳየችኝ ሳያት ድካሜ ይጠፋል የመኖር ፍላጐቴ ያይላል ፣ አንድ ልጇ ነኝ ለእኔ ብዙ ሁናለች። ከት/ቤት ስመጣ ውጊያ ሂጄ እንጂ ተምሬ የመጣሁኝ አይመስላትም ራበህ? ደከመህ? ምን አዲስ ነገር አለ? የዘወትር ጥያቄዎቿ ናቸው ማሚ ዛሬ እነዚህን ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ፍቃደኛ አይደለሁም በልቤ አልኩኝ። ዛሬ ፀሀይ መች ወጣች ፣ ዛሬ ከተማው ላይስ መች ሴት ነበር ፣ ዛሬ ከተማው ላይ ማን የሳቀ አለ? ሴትም ፣ ሳቅም ፣ ፀሀይ አልነበሩም ስለዚህ ስለየትኛው ልንገራት ስልኬ ጋር ለመድረስ ጓግቼ ማሚን በቅጡም ሰላም ሳልላት ወደ ክፍሌ ገባሁኝ ምን ያረጋል አህላምዬ አልደወለችም። ጨካኝ ደህና ነኝ ፤ በሰላም ነው ያልመጣሁት አትልም? ይጨነቃል ያስባል ብላ አታስብም? ደህና ባትሆንስ? የሆነ ነገር አጋጥሟት ቢሆንስ? "የመኝታ ቤቴ በር ተከፈተ እናቴ ናት ማሚ የድሮ አራዳ ነች ቀለል ሲላት ከትዝታዎቿ ማህደር ታገራኛለች ዛሬ ግን አንድ የፈለገችው ነገር እንዳለ ያስታውቅባታል።

ሰኢዲዬ ስትጨርስ ሳሎን ና እየበላን ማወራህ ነገር አለህ አለችኝ እሺ ብዬ ወደ ስልኬ ተመልሼ አህላም ጋር ደውልኩኝ ስልኳ አይነሳም ከአንድም ሶስቴ ደውዬ አታነሳውም። ድንገት አንድ ነገር ትዝ አለኝ ወንድሟ ቀጣይ ለሶስት ሳምንት ከሄደበት በያዝነው ሳምንት ይመጣል ብላኝ ነበር ቁርጥ ቀነኑን ባትነግረኝም። ወንድሟ መጥቶ ይሆናል ብዬ እኔም ተረጋጋሁኝ ልብሴን ቀይሬ ሳሎን ገባሁኝ።

ማሚ ሳሎን ላይ ባለው መጅሊስ እንደ ልእልት ተቀምጣለች፤ ዝምታዋን ለመስበር ማሚ" አንዳንዴ ትኩር ብዬ አይሽና ምን ያህል እድለኛ ብሆን ነዉ
አንቺን እናቴ አርጐ የሰጠኝ ብዬ አስባለሁ " ብዬ ግንባሯን ሳምኳት። እናቴ ምንም ከመናገሯ በፊት ከጥያቄ ነው ምትነሳው ትምህርት እንዴት ነው? እና ተያያዥ ጥያቄዎች ? በተርታ ከመለስኩኝ በሗላ ። ሁሌም ስለ አባቴ ስታነሳ እንደምትሆነው አንገቷን አቅርቅራ።

ሰኢዲዬ?
ወዬ ማማ ጠጋ ብዬ ታፋዋ ላይ ተኛው እሷም ፤ ባባ ከሞተ በሗላ የስራው ሁኔታ መስመር ለማስያዝ ሞክርያለው አሁን እየደከመኝ ነው። ሃላፊነቱን እንድትረከበኝ እፈልጋለው ይህ የሚሆነው አሁን ሳይሆን የዚህን አመት ትምህርትን ስታጠናቅቅ ነው ፤ የኮሌጅ ትምህርቱንም በማታው ክፍለ ጊዜ ትቀጥላለህ ለዚህም እስከ ክረምቱ ረዥም የማሰብያ ጊዜ አለህ እስከዛው ድረስ ግን ቅዳሜና እሁድ አብረን እንወጣለን አለችኝ። ባባ ጠንካራ ነጋዴ ነበር 9ኛ ክፍል እያለሁኝ ነበር ድንገት በተከሰተበት የልብ ህመም ነው ያረፈው ። ባባ ተቆፍሮ የማይደርስበት ጥልቅ የሃሳብ ሃብት ፣ከሰማይ የራቀ ምልከታ የነበረው ነበር። አላህ የጀነት ይበለውና ሁሌም ምክሩ እናትህን አደራ ነበር አደራዬን ማስቀየም አልፈልግም ዩንቨርስቲ ገብቼ መማር ብፈልግም የእርሷ ፍላጐት ከሆነ ከእሷ የሚበልጥ ነገር የለምና ሃሳቧን እንደምቀበል ነገረኳትና ግንባሯ ስሜ ወደ ክፍሌ አመራው።

ፀሀይ ጠልቃለች ቢሆንም አሁንም አህላም ስልክ አታነሳም ልቤ ፍርሃት ፍርሃት አለው፣ ውጣና ብረር እቤታቸው ሂድ ሂድ አለኝ። የወጣችልኝ የህይወት ፀሃይ በደንብ ሳላያት የጠለቀችብኝ መሰለኝ ፤ ነገ ጠዋት የመጀመርያ ስራዬ ሰፈሯ ሂዶ መውጫዋ ጋር መከታተል ነው ቢያንስ ደህንነቷን አረጋግጬ እመለሳለው ብዬ ጋደም አልኩኝ በዛችው ቅፅበት ኬት መጣ የማይባል እንቅልፍ ጭልጥ አርጐኝ ይዞኝ ሄደ አይነጋ የለ ነጋ የመጀመርያ ስራዬ ወደ አህላም ስልክ መደወል ነበር።

ስልኳ ጥሪ አይቀበልም ፍርሃቴ ይበልጡኑ ጨመረ፣ ማታ አይነሳም አሁን ደግሞ ዝግ ነው ምን ሆና ይሆን? የዚህን ጥያቄ መልሱ ያለው እቤቷ ደጃፍ ስደርስ ነው። ደህንነቷን አረጋግጬ ወደ ክላስ እገባለው ብዬ 1፡00 ከቤት ወጥቼ ላዳ ይዜ ወደ ሰፈራቸው አቀናው። ወደ መንደራቸው መግቢያ ጋር የመኪና መጨናነቅ አለ እዛ ስደርሰወ 2:00 ሰዓት ሆኖዋል በዚህ ሰአት የመኪናው ግርግር ስላልገባኝ ባለላዳውን እዚህ ጋር አቁመውና እኔ ደርሼ ልምጣ ብዬው ወደ ሰፈራቸው ገባሁኝ። …… ድንኳን እግሬ ተንቀጠቀጠ ፣ ትንፋሽ አጠረኝ ፣ እይታዬ ተጋረደብኝ። ጥቁር ዩኒፎርም የለበሱ ሴት ተማሪዎች ከሩቅ ይታዩኛል አዎ ድንኳኑ እነ አህላም በር ላይ ነው ዙሪያውን ደግሞ የትምህርት ቤታችን ዩኒፎርም የለበሱ ተማሪዎች አሉ እየፈራሁኝ ወደ ድንኳኑ ተራመድኩኝ……



ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል………

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
175 viewsEyoba, 11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:09:49 ​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━


"ሴትን አላምንም"

ክፍል 7

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ


እሁዱን በጠዋት ነበር የተነሳሁት ፤ እናቴ ከሰራተኛችን (ከኻዲማችን) የለመደችውን ጭቅጭቅ ይዛላች እናቴ ለእኔ የስኬቴ ምንጭ የደስታዬ ፋና ወጊ ናት።

እናቴ የማያልቅ ዘላለማዊ ፍቅርን በስስት የምትለግሰኝ የፍቅር ምንነት መግለጫዬ ናት በህይወቴ ከፍቷት ማየትን አልወድም በእሷ ውስጥ መልካምን ነገር አያለው እሷ ለኔ ከምንም በላይ ነች። እሷነቷ የታላላቅ ስኬቷ ጀንበር ሆኖ የምትፈነጥቅለት ነገር ግን ከእርሱ ልቆ ምታየው የመድመቂያው ጮራ መፍለቂያዋ እኔ ነኝ ለሷ።
እሁድ ቀን አርፍዶ የመነሳት ባህላችን የተመቸው ለኔ ብቻ ይሆን አላቅም እናቴ ሁሌም ንቁ እንድሆን ስለምትፈልግ በጠዋት መታ በር ታንኳኳለች ተነስ ያደለው "ሪከርድ ይሰብራል ፤ አንተ አልጋ ስበር" ብላ በነገር ወጋ አርጋኝ ትሄዳለች። ድምፇን ስሰማ ደስ ይለኛል አይደለም የፍቅር ቃሏ ስድቧን በጠዋት መስማት ለእኔ የቀኔ ማማር መሰረት ነው።

እናቴ ስትታመም ቤቱ ይጨልማል ፣ ፀሀይዋ ላለመውጣት ቃል የገባች ትመስለኛች ለዚህም በጠዋት የሷን ድምፅ በምንም መልኩ መስማት ለእኔ ደስታ ነው ፤ የዛሬው እሁድ ግን ይለያል ይህ ፍቅር የሚሉት የደስታ ይሆን ሀዘን ልቤ ላይ ገብቶ ያናውጠኛል። ከአልጋ ላይ ቁጭ ብዬ ከአህላምዬ ጋር ማሰልፈውን የፍቅር ማእበል መቃኝቱን ተያይዜ ከአልጋዬ ላይ መነሳት ከብዶኛል። ሩቅ ሃሳብ " ቀዝቃዘው ንፋስ እየነፈሰ… የሰው ጫጫታ በማይሰማበት ምሽት በጨረቃ ብርሃን ፍንትው ብሎ በሚታዩ መንገዶች በዛፍ ጥላ በተከበቡ ውብ መንደሮች ውስጥ እኔና አህላም እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንራመድ… በአካባቢው ውብ አበቦች መሀል ፀጥታውን አልፎ የሚገባው የንፋሱ ጩኸት ፣ የዛፎቹ እንቅስቃሴ ተዳቅሎ ልባችን ላይ ያለውን የፍቅር ስሜት ሲግል። ወደጆሮዋ ተጠግቼ ብርዱን አሰረስቼ የጨረቃውን ውበት በዚህ ቃል ሳደምቅላት" አፈቅርሻለው" አህላምዬ ብዬ የፍቅርን ቅኝት ስቀኝ። ላጣሽ አልፈልግም ሁሌም ከጐንሽ ነኝ አይዞሽ እንዳትፈሪ ቀሪው ህይወቴ ያንቺ ነው! ብዬ ሙሉ ተስፋን ስቸራት በምናብ የፍቅራችን ጊዜ ስቃኝ ፤ ሳላስበው በንፋስ ኃይል የተከፈትው የመኝታ ክፍሌ በር አስደነገጠኝ። ምቀኛ በር! በእኔና በአህላም የማይመቀኝ የለም እንዴ? ያ ክፉ አስተማሪ ፣ ጉድጓዱ ፣ ጓደኛዬ መሀመድ፣ ይህው ዛሬ ደሞ የመኝታ ክፍሌ በር ከአህላምዬ ሃሳብ አባነነኝ። የሄድኩበት የፍቅር ጉዞ ሳስብ ስቄ ዝም አልኩኝ… የማይረሳ የእብደት ጊዜ ያሳለፍኩበት እሁድ።

አይመሽ የለ መሽቶ ነጋ ዛሬ አዲስ ቀን ነው። ይህን የኔን ቀን ሰዓሊ ቀለምን አጣምሮ አይስለውም ፣ ፀሀፊ በየትኛውም አገላለፅ አይገልፀውም ፣ ዘፋኝም በየትኛውም ውብ ድምፅ አያዜመውም፣ እውቅ አዋቂዎችን ዝንት ዓለም ቢመራመሩም አይደርሱበትም። ምክንያቱም ዛሬ እንቅልፌን የወሰደችውን ፣ እኔነቴን የተቆጣጠረችውን ፣ ባይተዋር ያደረገችኝን ሴት ላገኝ ነው፤ ሁለቱን ቀን እንዴት እንዳሰለፍኩት ሰዓሊውም ፣ ዘፋኙም ፣አዝማሪውም ይሁን ገጣሚው አያውቀቱም። ታድያ ለእኔ ሰኞ ምን መሆኑን እነሱ በምን ያውቁታል?

ዛሬ ደግሞ ተማሪው ምን ሆነ ነው ያረፈደው ይህው ት/ቤት በር ላይ የደረስኩት 12:45 ነው በዚ ሰአት ተማሪ እንዴት አይመጣም እላለው። ሌላ ጊዜ ት/ቤት ከምደርስበት ሰአት 1:30 ያህል ቀድምያለው አህላምን ቀድሜ ለማየት አስቤ ነው በጠዋት ከቤት የወጣሁት ይሄኔ እሷ ከእንቅልፏ አልተነሳች ይሆናል? እኔም የግቢውን በር አልፌ ስገባ ሰኞ ፣ እሮብ ፣ አርብ ኳስ የሚጫወተቱትን የግቢያችንን ተማሪዎች ተመልክቼ የሰልፍ ሰዓት እስኪደርስ እነሱን ለማየት ወደ ሜዳው አቀናው ። የሰልፍ ሰዓት ደርሶ ክላስ እስክንገባ አህላምን አላየሗትም ፤ ምን አልባት አሟት ይሆን የቀረችው ብዬ እየደበረኝም ወደ ክላስ ገባሁኝ ትምህርቶቹም፣አስተማሪዎችም እየተቀየሩ ቢያስተምሩንም ምንም የሰማሁት ነገር የለም።
የመጨረሻ ደውል ላይ ከሃሳቤ ባነንኩኝ ቦርሳዬን ይዤ ተማሪዎችን ቀድሜ ወጣሁኝ እነ አህላምዬ ፎቅ ላይ ስደርስ በዝግታ ደረጃውን እየወረደች አየሗት አህላም? ብዬ ስጠራት ቀና ብላ ተመልክታኝ ያንን ውብ ፈገግታዋን ቸረችኝ ከአርቡ የቀጠለ ፈገግታ ፊቷ ላይ ግን ደስ የሚል ነገር አይነበብም ሰላምታ ከተለዋወጥን በሓላ ፤ ምን ሆነሽ ነው? አልኳት " ወንድሜ ለስራ ጉዳይ ከሀገር ወጥቷል ጠዋትም በታክሲ መጥቼ ረፈደብኝ አለችኝ። "ቢንጐ" አልኩኝ በውስጤ ደስ ቢለኝም እሷ እንድታውቅብኝ አልፈለግኩም ታድያ ከእኔ ጋር እንሄዳለና ወንድምሽ እስኪመጣ አልኳት! እናቴ አንደላቃ ነው ያሳደገችኝ በቂ ብር ከበቂ የአጠቃቀመ ዘዴ ጋ አስተምራ። ወንድሟ እስኪመጣ በላዳ አብረን ልንሄድ ፤ አልያም ደሞ ማሚን እንደምንም ለምኜ መኪናውን እንድትሰጠኝ ማድረግ። ማሚ መኪና መንዳት አትወድም መኪና ግን አስፈላጊ ነው ብላ ታምናለች ጉዳይ ሲኖራት ከእኔ ጋ ትሄዳለች ብዙም አትወጣም ከወጣችም ከክላስ ስመጣ እኔ እየነዳሁኝ አብራኝ መሄድ ነው የሚያስደስታት። ት/ቤት ይዤ ልሂድ ብዬ ጠይቅያት አላቅም ዛሬ ግን ልጠይቃት ወሰንኩኝ፤ አህላምም አብረን እንሂድ የሚለው ሀሳብ ምቾት ባይሰጣትም እራሷን አሳምና በሚመስል የፊት ስሜት ከግቢ አብረን ወጣን። አርብ ለት ያሳፈረን ባለ ላዳ ከግቢ ትንሽ ራቅ ብሎ አየሁት ወደሱ አመራን የእግሯን ደህንነት እየጠየቅኳት ፤ ሁለቱ ቀን እንዴት እንዳለፉ እያወጋን መኪናው ጋር ደረስን የሗላኛውን በር ከፍቼ አስገባሗት ከዛ በሗላ ለተከታታይ ቀናቶች አብረን እየሄድን ግንኙነታችን እየጠነከረ ሄደ ግጥም እንደምትወድ ሰለነገረችኝ አንድ አንድ ግጥም በየቀኑ እየላኩኝ እንድታነብ አድርጋለው በቴክስት ማውራት በደንብ ጀምረናል። የእኔ አላማ እሷን የኔ ማድረግ ፤ እሷስ ስለኔ ምን ታስባለች? በቴክስት ምታወራኝ ምን አልባት ወንድሟ ስሌለ ቢሆንስ? የፈጠነው ቅርርባችን ሳያሰጋት የቀረ አይመስለኝም። ቀናቶች አለፉ ዛሬ ግን አንድ ለየት ያለ ነገር ተፈጠረ ተደውሎ ወደነ አህላም ፎቅ ብሄድም……… አህላም


ይቀጥላል ክፍል ስምንት…………

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
217 viewsEyoba, 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 22:07:04 ​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━


"ሴትን አላምንም"

ክፍል 6

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ


ዛሬ ቀኑ ተለወጠብኝ እንደዚ አይነት ቀን ገጥሞኝ አያውቅም ጠዋት ት/ቤት ከገባውበት ሰአት አንስቶ ብዙ አዲስ ነገሮችን ተከሰቱ ፤ በአንድ ቀን እንደዚ ሰው መቅረቤን እያሰብኩ ገረመኝ፡፡ ብዙ ሀሳብ በውስጤ እየተመላለሰ ከአህላምዬ ጋር መሄዴን ቀጠልኩ . . .አህላምዬ ገላ ላይ ያለው ያልደረቀው ቁስል አስቀናኝ ፤ ሰው እንዴት በቁስል ይቀናል? የኔን ቦታ የሚጋፋ አንድ ጎረምሳ ጉልበቷ ላይ የተኛ ያህል ተሰማኝ። የላዳውን ሹፌር እየተመለከትኩኝ በምድር ላይ ውቧን ሴት ማሳፈሩን ቢያውቅ "የደስታ ጮቤ" ይረግጥ ነበር አልኩኝ በልቤ። መንገዱ በዝናብ ምክንያ የተጨናነቅ የመኪና ፍሰት ይታያል። ቢሆንም እኛን ማስቀደም አለባቸው መኪናው ውስጥ ከአምቡላንስ በላይ ለቤተሰቦቿ አስፈላጊ፣እንደ ኦክስጂን የሚቆጡሯትን ልጃቸውን አዘግይተንባቸዋል የመኪናው ፍስት ብዙም ቦርጭ ባለወጣ ትራፊክ ተቃለል። ቦርጫም ትራፊኮች መሀል መንገድ ላይ ሲቆሙ ሌላ መጨናነቅ ይፈጥራሉ የዚህ ከሲታ ትራፊክ መኖር በፈጣን ትራፊካዊ አመራር መንገዱ አቀለለልን።


እስካሁን ትካሻዬ ላይ ተኝታለች? ማነች? እንዴት ትከሻዬ ላይ እስካሁን? ብቻ አላውቅም ወድጃታለው ትከሻ ላይ መተኛት የማመን ስሜት አይደል? ብዙ አመት ካወቅኳቸው ሰዎች በተለየ ሙሉ ለሙሉ ተማምኜብሃለው ነው? በዚህ ሃሳብ ውስጤ ሁኜ ቤታቸው በር ላይ በአህላምዬ አመላካችነት ደረስን። ከመኪና ወርዳ ልባዊ ምስጋናዋን ከፈገግታዋ ጋር ቸረችኝ እኔም በፈገግታ ተቀብያት መሄዷ ባያስደስተኝም የመጨረሻ ቃል ይመስል ሰላም መሆንሽን በምን አቃለው ሁለት ቀን ሙሉ አንገናኝም ስልክሽን ስጪኝ ብዬ በሙሉ ልብ ጠየቅኳት። ለመወሰን ጊዜ አልወሰደባትም የት/ት ቤታችን ህግ በትምህርት ሰዓት ስልክ መያዝ ስለማይቻል በወረቀት ፅፋ ሰጠችኝ ፤የነበረኝን ደስታ ላየ ስልኳን ሳይሆን ህይወቴን ሊቀይር የሚችል ቼክ ነበር ሚመስለው።

ቤቷ እስክገባ በዓይኔ ሸኝሗት ቤቷ በር ላይ ስትደርስ ወደኛ ዙራ በእጇ ሰላምታን ሰጠችን። ደህና ሁን ምትለኝ መሰለኝ ፣ ከአሁን በኋላ አንገናኝም ቸር ሰንብት ይመስላል። አህላም ገባች ድንገት ጨለመብኝ ፀሀይ ጠለቀች አጠላለቋ ደሞ አስፈሪ ነው አሁን ደምቃ በርታ እልም ብላ እንደ ጠፋች ፀሀይ መፍዘዜን ያወቅኩት ባለ ላዳው እንሂድ አለቃ ሲለኝ ነው።


እሷን ከሸኝሁኝ በሗላ ለቀጣይ ሁለት ቀናት እንደማላገኛት ሳስብ ልቤ ተረበሸ ፤ ትምህርት ሊጀመር የቀረው ሁለት ቀን ወይስ ሁለት አመት? ቀኑ አልመሽ አለኝ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ የግድግዳውን ሰአት ደጋግሜ እመለከለታው ቀኖቹ ረዘሙብኝ እንኳን ሊመሽ የምሳ ሰዓት አልደርስ ብሎኛል "የተረገመ ቀን" ምንም የምቀይረው ነገር እንደሌለ ቢገባኝም አልጋዬ ላይ በጭንቀት እገላበጣለው። አንዳንድ መፅሀፍትን ለማንበብ እየገለጥኩኝ መልሼ አስቀምጣለው የማደርገው ግራ ገባኝ አህላምዬ ናፈቃኛለች። በአንድ ቀን እንዲ ያደረገኝ" ፍቅር" ወይስ ስሜት? አላቅም ብቻ ሰኞ ምላትን ማሰብ ጀምርያለው ደፋር ከሆንኩኝ።

የፍቅር ማዕረግን ባንቺ ለብሽያለሁ..በምድር ላይ የማቱሳላ እድሜን ያክል ብኖር ወይም ደግሞ የቀረኝ እድሜ ዛሬን ብቻ ቢሆን ላንቺ ያለኝን ፍቅር ይጨምረዋል እንጂ አይቀንሰውም ልበላት ወይስ?

" ደስታሽን ደስታዬ ላደርግ፤ መጥፎ የሚባል ሁኔታ ውስጥ ብትገቢም እንኳ ሁሌም ከጎንሽ ነኝ ብዬ ቃል ልግባና ተንበርክኬ አብረሺኝ ሁኚ ልበል? የሰው ልጅ በቃሉ እንጂ በእንብርክኩ መቆም አላቃተውም ብትለኝስ።"ይህማ አይሆንም ምንም ስሜቷን ላላወቅኩት ሴት ተንበርክኬ ብዋረድስ? በቃ እንዲ ልበላት።

(ጁምአ) አርብ እለት ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሽ ውስጤ ለዘመናት ሲፈልግሽ የነበርሽው ሃዋዬ አንቺ ነሽ ብዬ ለራሴ ነገርኩት አዳምሽ ልሁን ልበላት? አቅሙን ካገኝሁኝ ሁሉንም እላታለው።
ቅዳሜ ማታ ስልኳን ብቀበልም መደወል አልፈልግኩም ፤ ወንድሜ አለ ስላለች ስደወልላት አይቶ ቢናገራትስ መደወሉን ትቼ አጭር ቴክስት ላኩኝ። "እንዴት ነሽ አህላም ሰኢድ ነኝ ተሻለሸ? ያልደወልኩት እቤት ከሰው ጋ ከሆንሽ ብዬ ነው አሁን እንዴት ነሽ?"

ከደቂቃዎች በኋላ ወደ ስልኬ መልእክት ገባ ተጣድፌ ስክፈተው ያየሁት ነገር አላስደሰተኝም ጓደኛዬ መሀመድ ነው "የት ነህ"? የሚል ቴክስት የላከልኝ ። ማሜን ድንገት ጠላሁት አህላምዬን የተጋፋኝ መስሎ ታየኝ እቤት ነኝ አንተ "የት ነህ" ብዬ ከመፃፌ የአህላምዬ ቴክስት ገባ " ደህና ነኝ በጣም ቁስሌም ደርቋል ግን ለወንድሜ አንድ የትምህርት ቤት ልጅ ገፍቶ ነው የጣለኝ ብዬ ልነግረው አስብያለው" እንዳልነግረው ከፈለክ እኔን በደንብ ይቅርታ መጠየቅ አለብህ ብላ ይህን( ) አክላ ላከችልኝ። የቴክስቷ መልስ ፈገግ አስባለኝ ፈታ ያለችና ለመግባባት ምትመች ልጅ ሁና ታየችኝ እኔም " ምን ልቀጣ "? ግጥም እችላለው ልጋብዝሽ ብዬ አልኳት? ደስ ይለኛል ብላ መለሰች ፤ እድሉን አግኝቻለው በግጥም ስሜቴን መግለፅ አለብኝ ።

" እኔ ምን አጥፍቼ"

እኔ ምን አጥፍቼ ጥፋቱስ የአባትሽ
አንቺን መሳይ ልእልት
ያለምንም ረዳት አምነው መላካቸው
......
እኔን የሚገርሙኝ ወላጆችሽ ናቸው
አንቺን መሳይ ልዕልት
ያለማንም ረዳት እዚህ መላካቸው
በመንገድ ስትሄጂ....
ስንቱን ጎበዝ ጀግና
ባይንሽ ማርበድበድሽ ማን በነገራቸው ...............
...................
አህላምዬ አብረን ስንሳፈር አንቺን እያየሁኝ
ምናለ ላንድ ቀን አባትሽ በሆንኩኝ
ብዬ ተመኘሁኝ
ከስምሽ ቀጥሎ ስሜን ባስጠራሽኝ
እኔ አባትሽ ብሆን....
እንደ ዶሮ ዕንቁላል ታቅፌ ባኖርኩሽ
በስስት በፍቅር ነይ የኔ ልጅ ባልኩሽ
እኔ አባትሽ ብሆን.....
እንዳሁኑ ያንቺ አባት
በጠራራ ፀሐይ ያለምንም ረዳት
መች እልክሽ ነበር?
..... ...........................
እኔ አባትሽ ብሆን....
ይሄ ሁሉ ጀግና
ባንቺ ልዩ ውበት ውስጡ ባልታወቀ
ደፋሩ ባልፈራ አገር ባላለቀ ...............
.................
ተመልሼ ደሞ ነገሩን ሳስበው
እንኳንም አባትሽን ያንቺ አባት አረገው
እንኳንም የላከሽ ብቻሽን ያለሰው
እንዲያ ባይሆንማ....
እኔም ባልተመኘሁ እኔም ባልተቀኘሁ
ባንቺ ባልተገረምኩ ላገር ባልነገርኩኝ
ብዕሬን አንስቼ ግጥምም ባልፃፍኩኝ
እንዲሀ ተደስቼ አንቺን ባላገኝሁኝ።

ለረዥም ደቂቃ ቴክስት ሳትመለስ በመቆየቷ ልቤን ፍርሃት አራደው። ፍርሃቴ ብዙ ሳይቆይ በአንዲት የ text ድምፅ ተወገደ። ዘለግ ያሉ ኢሞጆችን ላከች ከልብ አመሰግናለው አንድም ሰው እንደዚ ብሎኝ አያውቅም የምር ልቤን ደስ አሰኝተሃዋል አመስግናለው ስላወኩ ደስ ብሎኛል መልካም እረፍት ፣ ሰኞን ናፍቅያለው "ግጥም ታነብልኛለህ" አለችኝ የትኛውን ሰኞ? የዛሬ አመቱ ወይስ የዛሬ ሁለት አመቱን? ሰኞ ስንት አመት ቀረው? የዚን ያህል እንዴት ቀርባ አወራችኝ? ሴት አይደለች ሴት እኮ እስክትግባባ ትቆያለች የሷ ግን ፈጠነ ምን አይነት ልዩ ባህሪ ነው ያላት? ሰኞም ትከሻዬ ላይ ትተኛ ይሆን?


ክፍል ሰባት ይቀጥላል ………

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
265 viewsEyoba, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 21:55:31 ​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━


"ሴትን አላምንም"

ክፍል 5

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ

ረጋ ካለው ሰላምታችን በኋላ… የት/ቤቱን ግርግር አልፈን እንውጣ አልኳት። ምላሿን ሳላገኝ ከፊቷ ተቀድሜ የተማሪዎቹን ትርምስ አልፌ ውጪ ጠበቅኳት ትንሽ ቆይታ እሷም ግርግሩን አልፋ መጣች "የበራልኝን ብርሃን ዛሬ ማጨለም አልፈለኩም" ሳሪስ ከሆነች ሳሪስ ፣ ቦሌ ከሆነች ቦሌ ፣ ካዛንቺስ ከሆነች ካዛንቺስ ብቻ አብርያት መሄዴ የማይቀር ነው ዛሬ እሷ የምትሄድበት ነው መኖርያዬ። "ወዴት ነሽ"? አልኳት……ወደ "ኮልፌ ነኝ" ብቻሽን ነው የምትሄጂው? የማያቋርጠው የእኔ ጥያቄ "ዛሬ አዎ" ሌላ ጊዜ ግን ወንድሜ ነበር ሚወሰድኝ አርብ ቀን ስራ ይበዛበታል ስለዚህ ያመሻል አለችኝ… ልሸኝሽ ልበላት እንዴ? እኔና አንተ ልንጣጣም ማንችል ነን ብትለኝስ? ከአንተ ጋ በእግር ከመሄድ ወንድሜን ጠብቄ በሚደላ መኪና ሙዚቃ እያዳመጥኩኝ መሄድ ይሻለኛል ብትለኝስ? ከአንተ ጋ ስሄድ ፀሀይ ያጠቁረኛል ፣ ዝናብ ያበሰብሰኛል ብላ ያልጠበቅኩትን መልስ ብትመልስልኝስ? …… ከሃሳቤ ባንኜ ስምሽን ማን ልበል አልኳት እሷም "አህላም" እባላለው አለችኝ ይህን ስም ወይም የዚህን ስም የቃል ትርጓሜ በደንብ አውቀዋለው አዎ አስታወስኩኝ አንድ የታሪክ መፅሀፍ ላይ።

አህላም ማለት "ምኞቴ" ማለት ነው አዋቂ መስሎ ለመታየት ይሁን ትርጉሙ ስለገባኝ oh በጣም አሪፍ ስም ነው አልኳት። የማን ምኞት ነሽ ምን አልባት ቤተሰቦችሽ ከመጀመሪያውም ቆንጆና የታላቅ ስብእና ባለቤት እንደምትሆኚ ታይቷቸው ይሆን ይሄን ስም ያወጡልሽ? …… ስላት ፈገግ አለች ስትስቅ ጉንጮቿ ወደ ውስጥ ይገባል ፈገግታዋ ንፁህ ነው ሸፍጥ ተንኮል ፣ የሌለበት… ከልብ የመነጨ ፈገግታ ነው። ፍቃደኛ ከሆንሽ ልሸኝሽ ለውለታሽ ቢያንስ "ሻይ ልጋብዝሽ" ብዬ ፍቃዷን ጠየቅኩኝ ። ፍቃደኝነቷን አንገቷን በመነቅነቅ አሳየችኝ ልቤ በሀሴት ተሞላ ጉዞዋችንን ቀጠልን እንዳይመሽ በልቤ ፈጣሪዬን እየተማፀንኩኝ መንገድ ጀመረን። " ጉድጓድ ሚል ድምፅ " ከሗላችን ተሰማ ግን መዳን አልቻልንም አህላምዬ ለመንገድ መስርያ ተብሎ በተቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ወደቀች። " ልቤ ከዳኝ ፣ እጄ ተንቀጠቀጠ ፣ እሷን ከውስጥ ለማውጣት አቅም አነሰኝ ፣ ዐይኖቼ በአንዴ ደም መሰሉ ሰማይ ምድሩ ጨለመብኝ። ቢሆንም አህላምዬ ተርፋለች ፣ ከጉድ ሰውሮኛል ፣ ጉድጓዱ ጥልቀት የለውም ቀኝ እግሯ ተንሸራቶ ስለገባ ድንጋይ መቷታል። … ትንሻፌን ሰብስቤ ደገፍ አድርግያት መንገዱ ጫፍ ላይ አስቀምጭያት ውሃ ላመጣ ሄድኩኝ። ትንሽ ስለደማባት"ደሟን በሶፍት ጠራርጌ" ትንሽ አረፍ እንበል ብዬ ተደላድላ እንድትቀመጥ አመቻቸሁላት ስትወድቅ ያዩ አላፊ አግዳሚዎች ብዙ ተጐዳች? አላህ ያሽርሽ ፣ ማሪያም አወጣችሽ? "መንገዱን ቆፋፍረውት እኮ ሰው ማለቁ ነው" ይላል አንድ አንድ የመንገዱ መበላሸት ብሶት ያማረረው ግለሰብ። አጠገቧ ተቀምጬ ላየኝ ትውውቃችን የአንድ ቀን ሳይሆን የዘመናት ይመስል ነበር አህላምዬ? አልኳት ደንግጬ ስለ ነበር ማቆላመጤን ረስቼዋለው…… ሰው ታሞም ያምርበታል ? ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ውብ መስላ ታየችኝ ፊቷ በህመም ይሁን በድንጋጤ ፍም መሰሎ ደሟ ሲዘዋወር ይታያል ህመም እና ድንጋጤ በተሞላበት ድምፇ "ወዬ" ብላ አንገቷን ትካሻዬ ላይ ጣል አድረገችው። …… የማረገው ጠፋኝ ታላቅ የኒሻን ሽልማት ትከሻዬ ላይ ያረፈ መሰለኝ እንኳንም ወደቀች ባትወደቅ መቼ ትከሻዬ ላይ አንገቷን ትጥል ነበር? ጠረኗ እንዴት ከደም ስሬ ቅርብ ሆኖ ያውደኝ ነበር?

ፍቅር ጨካኝ አደረገኝ በሷ መውደቅ ውስጥ ደስታዬን ያገኝሁኝ መሰለኝ ? ምን አለ " ትንፋሽ ቢያጥራት " ከኔ ውጪ ማን ትንፋሽ ይሰጣት ነበር። ወይዬ ብላኝ ከሃሳቤ ክምር ከማፅናኛዬ ቃል ውስጥ ያለውን ሁሉ ናደችብኝ። ወድጄሻለው ልበላት? በእጅጉ እንደምወዳት ልገልፅላት ፈልጌ ነበር ግን ቋንቋ አልነበረኝም ፣ ለእሷ ያለኝን ፍቅር መግለጫ አልነበረኝም። በአንድ ቀን ግንኙነት እንዴት ወዶኛል ብላ ታስባላች ሴት እኮ ነች ሴት ልጅ ደሞ ብልህምም ብልጥም ነች ለማፍቀርም ለመውደድ ምክንያት ትፈልጋለች። እኔን ለመውደድ ምን ምክንያት አላት? ለረዥም ደቂቃ የፈሰሰው ደሜ ወይስ አሁን በእግሯ አስኳትኛት የመውደቋ ሰበብ መሆኔ? ብቻ ያንን የብዙዎች ምኞት የሆነውን አንገት ትከሻዬ ላይ ነው ያለው ግን ምን ያረጋል ብዙም መቆየት አልቻልንም።


ዝናቡ ለመጣል ከሚነፍሰው ንፋስ ጋር ትግል ይዟል ፣ ቀና ብለን ስንመለከት የጨፈገገው ደመና ከበድ ብሏል በእሷ መውደቅ እና መታመመ ሀዘን ሰማይዋ ምታለቅስ መስላ ታየችኝ ። መንገደኛው የያዘውን እቃ ለማስቀመጥ በጥድፍያ ላይ ይገኛል ሰው የዝናቡን ከባድነት በመገመት ይሯሯጣል ይህ ሁሉ ትእይንት ደንታ ያልሰጠኝ እኔ ነበርኩኝ ጥላ ከለላዬን ትከሻዬ ላይ አርጌ ተቀመጭያለው። ዝናቡ ከመጣ ሊያበሰብሰን በመሆኑ ከፊታችን የቆመውን ላዳ አናግሬ መምጣት ሰለነበረብኝ አንገቷን ቀስ ብዬ ከትከሻዬ አንስቼ ላዳውን ላናግረው ሄድኩኝ ዓለሜን ከትከሻዬ ላይ በማውረዴ ቢከፋኝም በዋጋ ስለተስማማን አህላምዬን ቀስ አድርጌ ወደ መኪናው ይዣት ገባሁኝ።

አሁን ቀለል ያላት ትመስላለች ቁስሏም ማቃጠሉ በተወሰነ መልኩ በርዶላታል ሌላ ቦታዋ ስላልነተካ ደስ ብሎኛል መንገዳችን ጀመርን ከዚህ በሗላ አንገቷ ሌላ ትከሻ ላይ ማረፍ የለብትም ፣ የእግሯን ቁስል ሆነ ህመሟን ከኔ ውጪ ማንም እንዲያየው መፈቀድ የለብኝም። ግን እንዴት?


ክፍል 6 ይቀጥላል …………━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
406 viewsEyoba, edited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:49:09 ​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━



ሴትን አላምንም

ክፍል 4

"ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ"

ለሁለት ደቂቃ ያክል ሚናገር ጠፍቶ ዝም አልን።
ያቺን ሁለት ደቂቃ ያሳለፍኩት " በውበቷ በመደነቅ ፈዝዤ ነው"። " ትንሽ አረፍ በልበት እኔ ወደ ክፍል ልግባ" ስትል በንፁህ ልቦና ሃሳቧን አቀረበች። እኔ ግን ልለቃት አልፈለግኩም ቁጭ ብላ ስታወራኝ አምሽታ ፣ ብታነጋ ምነኛ ደስተኛ በሆንኩ…"በዚች ደቂቃ ውስጥ የማላውቀው አዲስና ልዩ የሆነ የፍቅር ስሜት ውስጤ እየተጫረ እንደሆነ ተሰማኝ። "በህይወቴ ከተደሰትኩበት ቀን የመጀመሪያዋን ደረጃ የዛሬዋ ቀን ሳትይዝ አትቀርም"። የውበት ንግስት፣ተዋድጅ ፍጡር ፣ የቆንጆዎች ቁንጮ ከአጠገቤ ልትርቅ መሆኑ ሳስብ አለምን ያጣሁ ያጣሁ ያኽል ተሰማኝ። ይሄ ሁሉ ዓለም ግንባታው ደፋ ቀናው ውብ ነገር ላይ ለመኖር አይደል ይህው ውብ አለም እዚ ሳትበረዝ አለች አይደል። የመኪና ቀለም ፣ የህንፃዎች ውበት ፣ የሁሉ ነገር ሳምፕል ለምን ከእሷ አይወሱዱም ማይሰለች ውበት ከእሷ ይቀዳል።

የለበሰችው ዩኒፎርም አይመስልም ቬሎ እላይዋ ላይ የተጣለ እስኪመስል ዩኒፎርሙን አሳምራዋለች። ብቻዋን ደስ ምትል ንፋስ ፣ ግር ግር የሌለባት አለም ፣ ንፁህ አየር የሆነች ሴት ከአጠገቤ ራቀች እሷ ስትሄድ ቦታው የመኪና ግርግር …… ጫጫታ የተተካበት መሰለኝ። ለምን ሰላም በታጣበት ክልል የሷን ምስል መንግስት በትልቅ ባነር ከፍ አርጐ አይለጥፍም ለሰላም እና መረጋጋት መፍትሄው የሷ ምስል እንጂ "መከላከያ ሰራዊት" አይመስለኝም። ይሄን በውስጤ እያብሰለሰልኩኝ ከአጠገቤ መራቋን ልብ አላልኩም … የሄደችው ደሜ ስለቆመ አይደል? "ደሜ ምን ያደረጋል ባይቆምስ" እሷ ትሄድ ነበር? ቢከፋኝ በአይኔ ሸኝሗት መማሪያ ክፍሏን ለማየት ቋመጥኩኝ ቢደክምኝም ድምፇ ሀይል ሁኖኝ ፣ ውበቷ ጉልበት ሁኖኝ በፈጣን እርምጃ ከሗላ በቅርብ ርቀት ተከታተልኳት።

የመማሪያ ክፍሏን አየሁት 11ኛ ክፍል እኛ ካልንበት ህንፃ በስተጀርባ ነው ይሄም አንድ ተስፋ ነው። ቀኑ ጁምአ (አርብ) ነው ነገ ዩኒፎርም ይታጠባል ሸሚዜ ከታጠበ "ያንን በምድር ላይ "በውድ ዋጋ ማይገኝውን የእሷን… ጠረን ከኮሌታዬ ላይ ሊፋቅ ነው! ለዚህ ደሞ ፍቃደኛ አይደለሁም ክፍሌ ማስቀመጥ አለብኝ ማንም እንዲያጥበው አልፈልግም። አሁን ወደ ክፍል ገብቼ ሳምሪ፣ ሜሪን ፣ ሀናን ልመለከት ነው? እረ ግፍ ነው ፈጣሪዬ ሆይ! በምን በደላቸው ነው ይሄን ፊት የቸርካቸው እላለው። አንዱ ልቤ ቀበል አርጐ "ተው በፈጣሪ ስራ አይገባም ይለኛል" ምን ዓይነት ልዩነት ነው ያላቸው? ሜሪ ደፍጣጣ አፍንጫ ያላት የክፍላችን ሳይሆን የምድራችን መልከ ጥፉ መስላ ታየችኝ ሀናን ደሞ የገጠጠው ጥርሷ ከንፈሯን አልፎ ከመታየቱም በላይ ረዥም ጅል መስላ ታየችኝ። ወደ ክፍል ገብቼ የመማሩን ሂደት ቀጥያለው "አካሌ እንጂ ልቤ መታጠበያ ቦታ ላይ የተመለከታት እንስት ጋር ነው"።

ተደውሎ እስክንወጣ ጨንቆኛል ቢያንስ ለውለታሽ ሻይ ልጋብዝሽ ልላት አስብያለው። ሰአት አልሄድ አለኝ የገባው አስተማሪ አስጠላኝ "እራስን ስለማጥፋት ሚያወራ መሰለኝ "ተደምሮ ስለሚመጣ ውጤት መንገር ትልቅ ስራ አርጐታል ተደምሮ ፣ ተስልቶ የተቀመጠ ህይወት ውጪ እየጠበቀኝ እሱ ይዘባርቃል ስለ ሰፈር ያወራኛል… የፍቅር ደሴት ላይ ለመንፈላሰስ ደውል እየጠበቅኩኝ። አይደል ተደወለ ከፓርላማ ስብሰባ የወጣሁ መሰለኝ ፣ ከህይወት ጭንቅ መከራ የታለቀቅኩ መስሎ ታየኝ ደውል ደዋዩ የዘላለም ባለ እዳው ነኝ ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁኝ። ከአምስተኛ ፎቅ መሬት ላይ ወርጃለው "እንዴት በምን ፍጥነት እንደሆነ ግን አላቅም" ብቻ ደርሻለው መሬት ብቻ ሳይሆን የዛች ውብ ልጅ መማሪያ ህንፃ መውጫ ጋር ቆምያለው ብዙ አልቆየችም ደረጃውን በእርጋት ስትወርድ አየሗት ሰው እንዴት በሰአታት ውስጥ ውበቱ ይጨምራል ከቅድሙ በላይ ተውባ ታየችኝ።

መንገዴን ተክትላ ብትመጣም አንገቷን ደፍታ ስለምትራመድ አላየችኝም። ከየት ያመጣሁት ዓይን አውጣነት እንደሆነ ባላቅም ትከሻዋን ነካ አድርጌ ሰላም አልኳት ከአንገቷ ቀና ስትል እኔ መሆኔን ለማወቅ ጊዜ አልወሰደባትም ረጋ ባለ አንደበት "እንዴት ነህ" ተሻለህ አለችኝ? በአጋጣሚ እንደተገናኝን እንጂ ተከታትዬ እንደጠበቅኳት አልተረዳችም።

"ተሻለህ" ላለችኝ ጥያቄ ምን ብዬ ልመልስላት አዎ ደሜ ቆሞዋል ህመሜም ድኖዋል ብዬ ልመልስ? ወይስ ሌላ ህመም ደረብሽብኝ ብዬ ልንገራት? በዛች አጭር ግንኙነት በፍቅርሽ ተሸንፍያለው ፣ ለአንቺ ተገዢ ሆኛለው፣ ከራሴ ቁጥጥር ውጪ ሆኛለው ብዬ ልንገራት። "ቅሉን አንድ ልብ ነበረኝ እሱም ዛሬ ለአንቺ ሰጥቼሻለው" ታድያ ዛሬ አንቺ ሁለት ልብ እኔ ምንም የለኝም እና ልቤን ጠብቂልኝ ልበላት? ወይስ ሌላ ህመም ሰጥተሽኝ ሄድሽ ልበላት። ፍቅር ህመም ሳይሆን ያለ ውጊያ መማረክ ፣ እጅ መስጠት ፣ ወዶ መግባት ፣ ከራስ መነጠል ፣ መጥፋት በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ነው ትለኝ ይሆናል።

ለጊዜውም ቢሆን ደህና ነኝ ብያታለው ግን ደህና ነኝ?


ክፍል አራት ይቀጥላል……

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

@eyoc7
446 viewsEyoba, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ