Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━ 'ሴትን አላምንም' ክፍል | ሀበሻን Text Meme

​​​​​​​​━━━━━━━━━━━━━━━━




"ሴትን አላምንም"

ክፍል 8

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ

……አህላምዬ ዛሬ አልመጣችም ማንን ልጠይቅ ለማን አቤት ልበል? አህላም ከሌለች መንገዱስ የት አለ? እረ እግሬስ እንዴት እሺ ብሎ ይራመድልኛል? … ስልኬን ስላልያዝኩኝ ያለኝ አማራጭ በፍጥነት እቤት ደርሼ መደወል ነው።

ጥያት መሄዱ ቢያስከፋኝም አማራጭ አልነበረኝም። በአቅራብያዬ ባለ ታክሲ ገብቼ ተሰፋርኩኝ ታክሲው ሲንቀሳቀስ ቅር ፣ ቅር ይለኝ ጀመር። ከት/ቤት እየራቅኩኝ ስመጣ በመስኮት ዞሬ ተመለከትኩኝ ለብዙ ደቂቃዎች ስፈልጋት የነበረችው አህላምዬ በር ላይ ቆማ ማያት መሰለኝ…… የለችም ባር ባር አለኝ ሳላየት ላድር ነው ላለፉት ቀናቶች አስለምዳኝ የሄደችውን ጨዋታና ሳቅ ዛሬ የለም መንገዱ ላይ ያሉ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ ፣ የንዴት እና የብስጭት ፊት የሚታይባቸው ሰዎች መንገዱ ላይ ቁመዋል ለምን ተቆጡ እነሱም አህላምዬን ስላላዩ ይሆን?

ታክሲ ውስጥ የተከፈተው ለስለስ ያለው ሙዚቃ ከሃሳቤ አባነነኝ… የአህላምዬ ፈገግታ ፊቴ ድቅን እያለ ያስቸግረኛል ምን አለ ሰዎች "የሳቅን ስልት" ከሷ ቢማሩ ሰው ለስልኩ ጥሪ ከሚቀያይር እያደር አዲስ ሚሆነውን የአህላምዬን ፈገግታ አንዴ ጥሪ ቢያደርግስ? ታክሲው ጉዞውን ቀጥሎአል። እኔም ሙዚቃውን እየሰማሁኝ በሃሳቤ ገስግሻለው… ለእኔ ከአህላምዬ ጋር ያሳለፍኳቸው አጭር ቀናቶች የራሳቸው ገፅ አላቸው ዛሬ ግን አህላም የለችም። ትዝታዋ ግን አለ የረዥም ጊዜ ሳይሆን ሰሞኑ የሆነ ዛሬ ላይ ግን ትዝታ የሆነ እኔ በትዝታ ወደ ሁዋላ ተመልሻለው ፤ ታክሲው ግን ወደፊት ይገሰግሳል።

አህላምዬ ከመጀመርያው እለት ጀምሮ በተፈቀደላት መሠረት ልቤ ውስጥ ገብታ ፤ እግሮቿን አኮራምታ ቁጢጥ አለች ፣ ውላ ስታድር ተንፈራጣ ተቀመጠች ፣ በቆይታዋ ደግሞ በጀርባዋ ጋደም አለች ስትከርም ጭራሹን ጓዟን ጠቅልላ ይሄ መከረኛው ልቤ ላይ ተኛችበት።

እቤት ስገባ እናቴ የተለመደውን ፈገግታዋን አሳየችኝ ሳያት ድካሜ ይጠፋል የመኖር ፍላጐቴ ያይላል ፣ አንድ ልጇ ነኝ ለእኔ ብዙ ሁናለች። ከት/ቤት ስመጣ ውጊያ ሂጄ እንጂ ተምሬ የመጣሁኝ አይመስላትም ራበህ? ደከመህ? ምን አዲስ ነገር አለ? የዘወትር ጥያቄዎቿ ናቸው ማሚ ዛሬ እነዚህን ጥያቄዎችን ለማስተናገድ ፍቃደኛ አይደለሁም በልቤ አልኩኝ። ዛሬ ፀሀይ መች ወጣች ፣ ዛሬ ከተማው ላይስ መች ሴት ነበር ፣ ዛሬ ከተማው ላይ ማን የሳቀ አለ? ሴትም ፣ ሳቅም ፣ ፀሀይ አልነበሩም ስለዚህ ስለየትኛው ልንገራት ስልኬ ጋር ለመድረስ ጓግቼ ማሚን በቅጡም ሰላም ሳልላት ወደ ክፍሌ ገባሁኝ ምን ያረጋል አህላምዬ አልደወለችም። ጨካኝ ደህና ነኝ ፤ በሰላም ነው ያልመጣሁት አትልም? ይጨነቃል ያስባል ብላ አታስብም? ደህና ባትሆንስ? የሆነ ነገር አጋጥሟት ቢሆንስ? "የመኝታ ቤቴ በር ተከፈተ እናቴ ናት ማሚ የድሮ አራዳ ነች ቀለል ሲላት ከትዝታዎቿ ማህደር ታገራኛለች ዛሬ ግን አንድ የፈለገችው ነገር እንዳለ ያስታውቅባታል።

ሰኢዲዬ ስትጨርስ ሳሎን ና እየበላን ማወራህ ነገር አለህ አለችኝ እሺ ብዬ ወደ ስልኬ ተመልሼ አህላም ጋር ደውልኩኝ ስልኳ አይነሳም ከአንድም ሶስቴ ደውዬ አታነሳውም። ድንገት አንድ ነገር ትዝ አለኝ ወንድሟ ቀጣይ ለሶስት ሳምንት ከሄደበት በያዝነው ሳምንት ይመጣል ብላኝ ነበር ቁርጥ ቀነኑን ባትነግረኝም። ወንድሟ መጥቶ ይሆናል ብዬ እኔም ተረጋጋሁኝ ልብሴን ቀይሬ ሳሎን ገባሁኝ።

ማሚ ሳሎን ላይ ባለው መጅሊስ እንደ ልእልት ተቀምጣለች፤ ዝምታዋን ለመስበር ማሚ" አንዳንዴ ትኩር ብዬ አይሽና ምን ያህል እድለኛ ብሆን ነዉ
አንቺን እናቴ አርጐ የሰጠኝ ብዬ አስባለሁ " ብዬ ግንባሯን ሳምኳት። እናቴ ምንም ከመናገሯ በፊት ከጥያቄ ነው ምትነሳው ትምህርት እንዴት ነው? እና ተያያዥ ጥያቄዎች ? በተርታ ከመለስኩኝ በሗላ ። ሁሌም ስለ አባቴ ስታነሳ እንደምትሆነው አንገቷን አቅርቅራ።

ሰኢዲዬ?
ወዬ ማማ ጠጋ ብዬ ታፋዋ ላይ ተኛው እሷም ፤ ባባ ከሞተ በሗላ የስራው ሁኔታ መስመር ለማስያዝ ሞክርያለው አሁን እየደከመኝ ነው። ሃላፊነቱን እንድትረከበኝ እፈልጋለው ይህ የሚሆነው አሁን ሳይሆን የዚህን አመት ትምህርትን ስታጠናቅቅ ነው ፤ የኮሌጅ ትምህርቱንም በማታው ክፍለ ጊዜ ትቀጥላለህ ለዚህም እስከ ክረምቱ ረዥም የማሰብያ ጊዜ አለህ እስከዛው ድረስ ግን ቅዳሜና እሁድ አብረን እንወጣለን አለችኝ። ባባ ጠንካራ ነጋዴ ነበር 9ኛ ክፍል እያለሁኝ ነበር ድንገት በተከሰተበት የልብ ህመም ነው ያረፈው ። ባባ ተቆፍሮ የማይደርስበት ጥልቅ የሃሳብ ሃብት ፣ከሰማይ የራቀ ምልከታ የነበረው ነበር። አላህ የጀነት ይበለውና ሁሌም ምክሩ እናትህን አደራ ነበር አደራዬን ማስቀየም አልፈልግም ዩንቨርስቲ ገብቼ መማር ብፈልግም የእርሷ ፍላጐት ከሆነ ከእሷ የሚበልጥ ነገር የለምና ሃሳቧን እንደምቀበል ነገረኳትና ግንባሯ ስሜ ወደ ክፍሌ አመራው።

ፀሀይ ጠልቃለች ቢሆንም አሁንም አህላም ስልክ አታነሳም ልቤ ፍርሃት ፍርሃት አለው፣ ውጣና ብረር እቤታቸው ሂድ ሂድ አለኝ። የወጣችልኝ የህይወት ፀሃይ በደንብ ሳላያት የጠለቀችብኝ መሰለኝ ፤ ነገ ጠዋት የመጀመርያ ስራዬ ሰፈሯ ሂዶ መውጫዋ ጋር መከታተል ነው ቢያንስ ደህንነቷን አረጋግጬ እመለሳለው ብዬ ጋደም አልኩኝ በዛችው ቅፅበት ኬት መጣ የማይባል እንቅልፍ ጭልጥ አርጐኝ ይዞኝ ሄደ አይነጋ የለ ነጋ የመጀመርያ ስራዬ ወደ አህላም ስልክ መደወል ነበር።

ስልኳ ጥሪ አይቀበልም ፍርሃቴ ይበልጡኑ ጨመረ፣ ማታ አይነሳም አሁን ደግሞ ዝግ ነው ምን ሆና ይሆን? የዚህን ጥያቄ መልሱ ያለው እቤቷ ደጃፍ ስደርስ ነው። ደህንነቷን አረጋግጬ ወደ ክላስ እገባለው ብዬ 1፡00 ከቤት ወጥቼ ላዳ ይዜ ወደ ሰፈራቸው አቀናው። ወደ መንደራቸው መግቢያ ጋር የመኪና መጨናነቅ አለ እዛ ስደርሰወ 2:00 ሰዓት ሆኖዋል በዚህ ሰአት የመኪናው ግርግር ስላልገባኝ ባለላዳውን እዚህ ጋር አቁመውና እኔ ደርሼ ልምጣ ብዬው ወደ ሰፈራቸው ገባሁኝ። …… ድንኳን እግሬ ተንቀጠቀጠ ፣ ትንፋሽ አጠረኝ ፣ እይታዬ ተጋረደብኝ። ጥቁር ዩኒፎርም የለበሱ ሴት ተማሪዎች ከሩቅ ይታዩኛል አዎ ድንኳኑ እነ አህላም በር ላይ ነው ዙሪያውን ደግሞ የትምህርት ቤታችን ዩኒፎርም የለበሱ ተማሪዎች አሉ እየፈራሁኝ ወደ ድንኳኑ ተራመድኩኝ……



ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል………

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን