Get Mystery Box with random crypto!

✥መ/ር ምህረተአብ አሰፋ ፔጅ✣

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahido_ortho — ✥መ/ር ምህረተአብ አሰፋ ፔጅ✣
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahido_ortho — ✥መ/ር ምህረተአብ አሰፋ ፔጅ✣
የሰርጥ አድራሻ: @tewahido_ortho
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.32K
የሰርጥ መግለጫ

ውድ የቻይናላችን ተከታዮች በሙሉ የምለቀቀውን ሸር እያደረጋችሁ ለወዳጅ በማድረስ የድርሻውን ይወጡ #የማንቂያ_ደውል በቴሌግራም እስኪ ጀምር።
#እግዚአብሔር_እንድ_ይላል
በመንገደ ላይ ቁሙ ተመልከቱም
#የቀደመችውንም_መንገድ_ጠይቁ
#መልካምቱ_መንገድ_ወዴት_እንደ_ሆነች_እወቁ
ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ
#እነርሱ_ግን_አንሄድባትም_አሉ።
✥ት/ኤር 6፤16
⏩በየ እለቱ ሙሉ ትምህርት ያገኙበታል

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-21 07:57:27 ​​​​​​በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸ ሥርዓቶች

1, ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።


@tewahido_ortho
https://telegram.me/tewahido_ortho
2.4K views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 01:29:49 :++ ንጉሥ #በአህያ ላይ ++
(ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ)

"አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት። የዚህች በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው። በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣ ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት።
ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት።

ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ።

ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።

"የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት?

ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም።

እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል። መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም ሥልጣኑ እያላቸው በትሕትና "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን።





መምህር ምህረተአብ ፔጅ
#በድጋም የተለቀቀ



https://telegram.me/Tewahido_ortho
2.1K views22:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 07:49:53 ተወዳጆቼ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን የአብይ ፆም ሰባተኛው ሳምንት
"ኒቆዲሞስ" ይባላል።
#ኒቆዲሞሲ

@tewahido_ortho

ኒቆዲሞስ ማለት :- በቤተክርስቲያን ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል።

ትርጓሜው የአይሁድ መምህር ወይም ደሞ የጌታችን ደቀ መዝሙር የሌሊቱ ተማሪ ማለት
ነው።

ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው።ዮሐ 3:1
ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው።ዮሐ 3: 1
ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው።ዮሐ 3:10
ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው።የሐ 7:51

ኒቆዲሞስ በኢየሩስ አሌም በሀብት በእውቀት ዝና በስልጣን የታወቀ ነው።ኒቆዲሞስ ስለ ሶስት ነገር ሌሊት ሌሊት እየሄደ ከጌታ እግር ስር ይማር ነበር።

1 አይሁድ ፈርቶ:- በዛን ሰአት በአይሁድ ህግ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር የሆነ ሀብት ንብረቱ ስለ ሚቀማ ከነሱ ለመሸሽ ሌሊትን መረጠ።
2,ውዳሴ ከንቱን ሽቶ:-በወቅቱ የነበረ እውቅ ሊቅ ነበርና
እንዴት ከመምህር ስር ይማራል እንዳይሉት።
3 ልቡናው እንዲሰበሰብ:-ከቀን ይልቅ ሌሊት የአይምሮ
እረፍ ስላላት እሱን ሽቶ ነው።

ኒቆዲሞስ ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብሎ ስለ ምስጢረ ጥምቀትና ዳግመኛ ልጅነት የፅድቅ ስራ በሰፊው ተምሮአል።
ዮሐ ም 3፡ 1-12

ወስብሐት ለ እግዚአብሔር


ለወዳጅ ያጋሩ ወድ የተዋህዶ ልጆች


@tewahido_ortho
2.5K viewsedited  04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 07:07:51 #ደብረ_ዘይት የአብይ ጻም 5ኛ ሳምንት። እግዚአብሔርስ ገሀደ ይመጽእ ወይአምላክነሂ እያረምም። እሳት ይነድድ ቅድሜሁ። #እግዚአብሔር_ግልፅ_ሁኖ_ይመጣል
መዝ 49፤1_5 #በደብሬ_ዘይት ዕለት ይህ የመንግስት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል።
ማቴ 24፤14
የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ምፅሀት ወይም የዓለም ፍጻሜ
መምጫ እንደ ሆነ ታሳብ እንድሆን እያደረገች በቤተክርስቲያንአችን ታስተምራለች ። እኛም የእነሱ ፈለግ ነንና እንዲው እናስተምራለን።እንኳን አደረሳችሁ ተወዳጆቸ

#ኑ_እናንቴ_የአባቴ_ብሩካን
ማት((25፤31))
የሰዉ ልጅ በጌትነቱ ቅዱሣን መላእክትን ሁሉ አስከትሎ በምመጣበት ጊዜ
ያን ጊዜ በዙፋኑ ይቀመጣል
አሕዛብ ሁሉ በፍቱ ይሠበሰባሉ
እሬኛም በጎች ከ ፍየሎች
እንደምለይ እየራሳቸዉ
ይለያቸዋል።
በጎችን በቀኙ
ፍየሎችን በግራዉ ያቆማቸዋል።

ያን ጊዜ በቀኙ ያሉትን እንድህ ይላቸዋል አናንቴ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችዉን መንግስት ትወርሱ ዘንድ ኑ ።

ጌታችን መዳንታችን ይህን ሰናገር ራሱን ዝቅ አድርጎ የሰዉ ልጅ አለ
ግን አስቡት እርሱ ፈጣር ነዉ
ነገር ግን
የተወለደዉ በከብች ግርግም
የቴሰቀለዉ በእርጥብ መስቀል

ራሱን ዝቅ አድርጎ ሥመጣ አንዳንዶች ዝቅ አድርገዉ ወሰዱትደ።

ይህን ቃል አስተዉሉት!!!!


ፍልጵዮስ((2፤8 --10
እግዝአብሔር ሁኖ ሳለ
የባርያዎቹን መልክ ይዞ መጣ
ስሙም ከሁሉ በላይ የሆነ
በሰማይም ካሉት
በምድርም ካሉት
ጉልበት ሁሉ ለእየሱስ ክርስቶስ
ሥም ይበርከክ።


በስማይ ሥል መላእክትንነዉ
ይሕ ማለት መላእክት ጅማት እግር እጅ አላቸዉ ማለት አይደለም ለአምላካቸዉ አንደ ምሰግዱ ሥለ ፍፁም ክብሩ ለማሥረገጥ ነዉ።
በምድር ሥል እኛ ባርያዎችን የሰዉ ልጆችን ነዉ።


በዛሬ ቀን ከመላእክት ወገን አንዱ እንደ ምሰበስበን እንደ ምቁምልን እናያለን እርሱም
ቅዱስ ሚካኤል ነው

ት/ዳንኤል((12፤1))
በእዝያን ዘመን ሥለ ሕዝብህ ልጆች ሁሉ የምቆመዉ ታላቁ አለቃ
#ሚካኤል_ይነሳል
ሕዝቡም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዝያ ዘመን ድረስ
እንደ እርሱ ያለ ያልሆኔ
የመከራ ዘመን ይሆናል
በእዝም ዘመን በመፃሐፍ ተጽፎ የተገኘዉ ሕዝብህ ሁሉ እየአንዳንዱ ይድናል ።
ከምድር ካሉትም ብዙሆች ከአንቀላፉት ይነቃሉ።

አሁን የምንተኛ ጊዜ አይደለም
የምንነቃበት ጊዜ ነው

#መናፍቃንንም_ብትሆኑም_እግዚአብሔር_ኑ_ይላችዋል_ጠፍታችው_እንደ_በግ_እንድትቅበዘበዙ_አይፈልግም_ኑ_የአባቴ_ብሩካን_ይላችዋልና_ኑ

ጌታችን ቅድም አንዳየነዉ ቅዱሳንን ሰብሰቡለት ያለዉ
እዝጋ ተፈፅሞ አየነዉ

2ኛጰጢ((3፤7) በእዝያን ዘመን ሰማያት ይቀልጣሉ ልዩ ልዩ ሥፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል።

በአይናቹ የምታዪት ነዉ
ምድር ተናዉጣለች ሰዉ ሁሉ የሞት ደብዳበ በትከሻዉ ተሸክሞ ነዉ ያለዉ መቼ አንደ ምመጣ ስለማናዉቅነፅተን ፤በንስሐ እንጠብቀው፤ንስሐ እንግባ ።



((ኢሳ((53፤8"))
#ከትዉልድ_ሁሉ_ማን_አሰተዋለ ባየነዉ ጊዜ ደምግባት የለዉም አንደ ተቀሰፈ ቆጠርነዉ።


ፍቱ በደም ቸሸፍኖ
ጀርባዉ በጅራፍ ቆስሎ
ገለጋይ በለለበት ተዉ ብለዉ የምያሥቆም በለለበት
እኛን ለማዳን የመስቀል ፍርድ ፈፀሜ።

((ቆላስያስ((2፤14 ))
የእዳ ደብዳበያችን ተቀደደ
የጥሉም ግርግዳ ፈረሠ ።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ያለውም ለዝ ነው
እዳ በአባታችን በአዳም ነበረው ጥልን በመስቀል ጠርቆ ገደለው።

የሐ((10፤31))
እኔንም አያችዉ አታዉቁኝም
አባተንም አያችዉ አታዉቁትም
#እኔና_አብ_አንድ_ኔን።

እርሱ እግዚአብሔር ነው
በአንድነት እና በሦስትነት አለም የፈጠረው ግን ስለ እኛ ያሳየው ፍቅር ፍፁም ፍቅር ነው።ማንም ልያደርግልን የማይቻለውን አምላካችን ግን በደሙ አነጻን።

የሐ/ራዕ((1፤6--8))
#የወጉት_ሁሉ_ያዪታል
መቸ ክርስቶስ ስመጣ።

አዎ ጌታ ግልፅ ሁኖ ይመጣል
የወጉትም ሁሉ ያዩታል

ሙታንም ሕያዋን ይሆናሉ
ኢሳ 19፤26


የሐ((3፤13))ከሰማይም ከወረደዉ በቀር ወደ ሠማይ የተመለሰ የለም።


የሐ:/ሥራ((((1፤።9))
እናት ወደ ሰማይ ትኩር ብላችዉ
ትመለከታላችዉ???
ይህ ከእናንቴ ወደ ሰማይ የወጣዉ እየሱስ አንድዉ ይመጣል።

የሐ/ራዕ((12፤12))
እንሆ በቶሎ አመጣለዉ ለዬ አንዳዱም አንደ ስራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋ ከኔ ጋር አለ
አልፋና ኦመጋ እኔ ነኝ ።

ውድ ወንድምና እህቶቸ በዛሬ ቀን
እግዚአብሔር ግልፅ ሁኖ ይመጣል የተባለው ቃል ይፈፀም ዘንድ ግድ ነውና። ማስተዋልን እግዚአብሔር ያድላችው።
በክርስቶስ ቀኝ ለመቆም ያብቃችው
ከቅዱሳኑ ጋር ይብረትን ያድላችው
ለሰማዩ አምላክ ቀኝ ፍት ሁላችንንም ይሰበስበን። አሜን


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
አሜን #ሸር_ያድርጉት_ብያንስ_ለ5_ወዳጅ_ይድረስ
ወደ ማታ
ጌታችን መዳንታችን በመጋቢት 27የምታሰብበት ሥለህኔ
#ትምህርት_ይቀጥላል


Groupjoinshare

@Enem_tiwulidnegn


ለአስታየቶት
@Asitayet



#ቻይናልይቀላቀላሉ


https://telegram.me/timhirte_tewahido
2.5K views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 11:34:24 አሕዛብ ለምን ያጉረመርማሉ መዝ 2፤1
አሕዛብ ለምን ያጉረመርማሉ
መዝ ❷፤1
የሙስልሞችን እየአንዷዷን ጥያቀ እያብጠረጠርን
እናያለን #ቻይናል_እንሆ_ብለናል_እንደ_ምትወዱት_ተስፋ_እናደርጋለን።
❶ኛ መጻሕፍቅዱስ እውነት ይጋጫልን
❷ኛ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ አይደለምን
➌ኛ ቁርኣን ከፈጣር የመጣ ቃል ነውን
❹ቁርኣን ስለ ኢየሱስ አይመሰክርምን
❺ማንኛውንም ጥያቀ እንመልሳለን
የተዋህዶ ልጆች አለን እናተ አላችው
ሸር ያድርጉት
https://t.me/tiyakenaMels
2.8K views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 15:26:56 ✥መ/ር ምህረተአብ አሰፋ ፔጅ✣
ውድ የቻይናላችን ተከታዮች በሙሉ የምለቀቀውን ሸር እያደረጋችሁ ለወዳጅ በማድረስ የድርሻውን ይወጡ #የማንቂያ_ደውል በቴሌግራም እስኪ ጀምር።


#እግዚአብሔር_እንድ_ይላል
በመንገደ ላይ ቁሙ ተመልከቱም
#የቀደመችውንም_መንገድ_ጠይቁ
#መልካምቱ_መንገድ_ወዴት_እንደ_ሆነች_እወቁ
ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ
#እነርሱ_ግን_አንሄድባትም_አሉ።
✥ት/ኤር 6፤16
በየ እለቱ ሙሉ ትምህርት ያገኙበታል
https://t.me/tewahido_ortho
2.3K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-14 14:47:57
መስቀል አደባባይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ርስት ናት እንጂ የማንም መወንጨፍያ ቦዶ መዳ አይደለችም



@tewahido_ortho



መምህር ምህረተአብ አሰፋ
3.8K viewsedited  11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 08:16:55
ተንቀናል!!


በመጨረሻም መስቀል አደባባይ ላይ እንዲህ ጨፈሩበት በጣም ያሳዝናል


ኢትዮጵያ ላይ ምን እየተደረገ ያለ አይታወቅም

@tewahido_ortho
5.3K viewsedited  05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 08:08:47
Video


ቦታችን ይከበር



@tewahido_ortho
4.4K viewsedited  05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 08:04:19
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መብት መጠበቅ አለበት

ለምመለከተው አካል ሸር ያድርጉ


@tewahido_ortho
5.0K viewsedited  05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ