Get Mystery Box with random crypto!

TMS

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahdo_media1 — TMS T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahdo_media1 — TMS
የሰርጥ አድራሻ: @tewahdo_media1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.00K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-30 11:45:27 በካናዳ ቶሮንቶ የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ታላቅ ጉባኤ ተጀመረ

አብዛኛው ሕብረተሰብ የእግዚአብሔርን የማዳን ነገር ዋጋ ሳይሰጡና በበጎነት ሳይመለከቱ፤ የራሳቸውን ምክንያት በመደርደር፤ ሰው ላይ የሚታየውን ችግር ፋይዳ ቢስ አድርገው፤ ባዶነታቸውን ሳይመለከቱ እንደ ነፍሳቸው ምኞት ይናገራሉ፡፡ “እንዲሁም ክፋትን ይጎነጉናሉ” ብዙው ሰው ረጅሙን ዕድሜ ያሳለፈው በምስጋና፣ በፀሎትና በአምልኮት ሳይሆን፤ በጥላቻ፣ በመለያየት፣ በመሰሪነትና አንዱን አንዱ ጥሎ በማለፍ ስለሆነ፤ በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ሆኖ ኃጢአያትን በመለማመድ፤ ደፋር፣ ኩሩ፣ ቀማኛና ነጣቂ በመሆን፤ ክፋትና ጥፋትን ለማቆየት እየሠራ ይገኛል፡፡
እኛም ታዲያ የምናስበው፣ የምናቅደውና አመለካከታችን ከክፋት ጋር የተያያዘ በመሆኑ፤ የብዙውን ትውልድ ዕድል አጥፍተን፤ ብዙ ከሃዲዎችን ማፍራታችን አንዱ የግፍ ሥራችን ምልክት ነው፡፡ በጎና ቅን ሆነን በመንፈስ ቅዱስ ተዋጅተን ወደ ሰው የምንሄድበት ሕሊና ስላጣን፤ ነገር እየጎነጎንን መሰሪ እቅድ ኑሯችን ውሰጥ ተክለን፤ ከጀርባችን ብዙ ክፋቶችን አዝለን እንኖራለን፡፡

ከእነሱ ሁሉ የተሻለው እንደ አሜኬላ ነው” ያለው የነብዩ ቃል፤ አሜኬላ ተደብቆ የሚወጋ ከታች ስትረግጠው ከላይ የሚቧጥጥ፣ ጫማ አልፎ የሚያቆስል፣ የሚያደማ፣ የማያስሮጥ፣ ቁስል የሚሆን፣ እግርን የሚቆጠቁጥ፣ የሚያም፣ የሚያስጨንቅ፣ አረማመድን የሚገታ፣ የወደፊት ተስፋን የሚያመክን እና ቁልቁል የሚያሽከረክር ነው፡፡ ዛሬም የተሻለ የተባለው ሰው ሁሉ ልክ እንደ እሾህ የሚዋጋ ሆኖ በሥልጣን፣ በማዕረግ፣ በከፍታ ለሌላው ሰው እንደ አሜኬላ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ከሁሉ ቅን የሆነውም፤ እንደ ኩርንችት ነው፡፡ ኩርንችት ደግሞ እንደ ደበኛ አድፋጭ፣ ተንኮለኛ፣ ምቀኛና ነገረኛ ምሳሌ በመሆን፤ በተፈጥሮ ሂደትም በምትረግጥበት ስፍራ ላይ እግርህንና ኮቴህን ተደብቆ የሚወጋ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ኩርንችትና አሜኬላ በሁሉም አቅጣጫ በኑሮችን ውስጥ የተለመደ አድርገን፤ በክፋትና በግፍ አሠራር የሌሎችን ሕይወት በግልጽና በስውር ስንጎዳ ይታያል፡፡
464 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 16:05:53 "ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ። እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው።"

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም መግለጫ ሰጡ።

ሐዋ. ፳፫፥፭ "በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር" የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መነሻ በማድረግ መግለጫውን የጀመሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ ላይ በጥራዝ ነጠቅነት የተሳሳተ መረጃ መስጠት ትክክል አለመሆኑን በመጥቀስ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ። እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው። በዚህም ቤተ ክርስቲያን ታዝናለች" ብለዋል።

በሀገር ውስጥና በውጭ ላለችው ቤተ ክርስቲያን አባት የሆኑ አባትን በዚህ መንገድ መናገር ሉዓላዊ የሆነች የኢ/ኦ/ቤ/ክንን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናንን መድፈር ነው ያሉት ብፁዕነታቸው
ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል ትርፍ ማግኘት አይቻልም ሲሉ አብራርተዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናትን በውጪ ሀገር መትከል ከጀመረች ጀምሮ ጽላት በአሠራሯ መሠረት ትልካለች።
የታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት እና ልጆቿ በረሃብ እየተገረፉ የጠበቁትን ሁኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ታሸሻለች ብሎ ማሰብ ንስሐ ያስገባል።
ይህ የቅዱስነታቸውን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ክብር መንካት ነው ብለዋል።

መንግሥት ለምን ብሎ መጠየቅ እና መመርመሩ ተገቢ ነው። ነገር ግን ቅርጽና ቅርስ መለየት ያስፈልጋል። በቀጣይም በጉዳዮ ላይ ግልፅነት ለመፍጠር ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር በቀጣይ እንወያያለን በማለት በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
ምንጨ:- ማህበረ ቅዱሳን
@tewahdo_media1
587 viewsedited  13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 16:05:19
555 views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 19:51:31
በቅዱስ ፓትርያርኩ ጉዞ ላይ በቦሌ ኤርፖርት ከተፈፀመው አሳዛኝ ድርጊት ጋር ተያይዞ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነገው ዕለት መግለጫ እንደሚሰጡ ተገልጿል።

ተዋህዶ ሚድያ ማእከል ማምሻውን እንዳለው "ብፁዕነታቸው ስለተፈፀመው ድርጊት መረጃውን እንደሰሙትና እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ወጡ የተባሉት ጽላትና ንዋያተ ቅድሳት በሕጋዊ መንገድ መውጣታቸውንና ለዚህም ሕጋዊ ፍቃድ መያዛቸውን ተናግረዋል።"

አክሎም "ብፁዕነታቸው ይህ ለአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትም ሆነ ድርብ ለሚፈልጉ አብያተ ክርስቲያናት በሀገረ ስብከታቸው ጥያቄ መሰረት በመንበረ ፓትርያርክ ፍቃድ የሚሰጥ አስቀድሞ የነበረ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አሠራር ነው።"

በሌላ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ ብፁዕነታቸው ነገ 8:30 ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በጉዳዩ ላይ መግለጫ እንደሚሰጡ ዘግቧል።
Credit: Tewahdo Media Center
@tewahdo_media1
720 viewsedited  16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 18:04:03 ሁለት ፅላቶች፣ መስቀሎች፣ መፅሀፍ ቅዱስ እና ቅብዓ ሜሮን "በህገወጥ ሊወጡ ሲሉ ተያዙ" ተብሎ መረጃ ሲሰራጭ ነበር፣ እውነታው ግን በሎስ አንጀለስ ከተማ ለሚገኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉ ናቸው።

እውነታውን ተዋህዶ ሚድያ ማዕከል እንዲህ አቅርቦታል።

"ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለሕክምና ወደ ሰሜን አሜሪካ እንደሚሄዱ መገለፁን ተከትሎ ትናንት ምሽት ቅዱስነታቸው የአሜሪካ ጉዟቸውን መጀመራቸው ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው ለሕክምና የሚሄዱ ቢሆንም በአዲስ አበባ ኤርፖርት በተገኙበት ወቅት ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ተፈቅደው በአድራሻ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የተጻፈ ሕጋዊ ደብዳቤ እያለ እና ሂደቱ ትክክለኛ ሆኖ ሳለ አንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎች "ከቅዱስነታቸው ጋር ሕገ ወጥ ቅርስ ከሀገር ሊሸሽ ሲል ተያዘ" እያሉ የሚነዙት አሉባልታ መሠረተ ቢስ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ተ.ሚ.ማ ያነጋገራቸው እማኞች ስለሂደቱ ሕጋዊነት በመግለፅ የሰነድ ማስረጃም ጭምር እንዳለ ነው የገለፁት።

ቅዱስነታቸው ሁለት ጽላቶችን ፣ 3 የብር የእጅ መስቀሎችን (የግል ንብረታቸውንና ስማቸው የተፃፈባቸውን) ፣ 5 አዲስ እትም የግእዝ መጽሐፍ ቅዱስ እና አንድ ሊትር ቅብዓ ሜሮን ይዘው ለመሄድ ለቦሌ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ ጥያቄ መቅረቡንም ተ.ሚ.ማ አረጋግጧል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ከታማኝ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት በተለያዩ ማኅበራዊ ድኅረ ገጾች በሰበር ዜና እየተላለፈ የሚገኘው "በአባቶች ሻንጣ ውስጥ ተደብቀው የነበሩ ቅርሶች ተያዙ" የሚሉ መረጃዎች መሰረተ ቢስ መሆናቸውንና ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአገልግሎት ይዘዋቸው የሚጓዙ ንዋያተ ቅድሳት መሆናቸውንና ህጋዊ ሰነዶች የተዘጋጁላቸው መሆናቸውም ተገልጿል ፤ መላው ኦርቶዶክሳውያን ካልተረጋገጠ መረጃ እና ፍፁም ሀሰት ከሆነ ማናቸውም የመረጃ ሂደቶች ራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክታችን ነው።"

@tewahdo_media1
1.2K viewsedited  15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 18:03:37
647 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 18:03:30
633 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 11:25:38
መጣልን ገብርኤል ከእኛ መሃል ቆሟል
የእሳቱንም ኃይል በመስቀል ገስጿል።
____
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለሊቀ መላኩ ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአል አደረሳችሁ!!

"ቁሉቢ" ማለት በኦሮምኛ ቋንቋ ሽንኩርት ማለት ነው። በቦታው ላይ በብዛት ሽንኩርት፣ ድንችና ሌሎች አትክልቶች የሚመረትበትና የሚሸጥበት ስለ ነበር “ቁሉቢ” የሚለውን ስያሜ አግኝቷል።

ስዕለት ሰሚው ደብረ ኃይል ቁሉቢ ቅ/ገብርኤል ገዳም ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ይገኛል ::

ሀያሉ መላክ ሦስቱን ሕጻናት ከእሳት እንዳወጣ እኛንም ሀገራችንንም ካለንበት ፈተና እና መከራ ያውጣን።

ለእመቤታችን የምስራች ያበሰረከው ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ለሀገራችን ለኢትዮጲያ መከራው በቃ ብለህ አሳልፈን።አሜን!

@tewahdo_media1
857 viewsedited  08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 11:22:03
ሆነ ተብሎ የሚደረገውን እዩት

ህዝብን የመናቅ ጥግ !

የዚህ ኮንሰርት አዘጋጆች ሌላ ቀን ጥፍቶ ነው ወይ በዚህ ዕለት ኮንሰርት ?

ድምፃዊያኑስ ምነው ለአንድ ቀን የማይረባ ገንዘብ ህዝቡን ናቃችሁ ?

በዚሁ ከቀጠላችሁበት ውጤቱን አብረን እናያለን!

እስፖንሰሩ ደግሞ ጊዮርጊስ ቢራ
የጉድ ሃገር

ጠጭው ደግሞ ኦርቶዶክስ ነኝ የሚለው ያሳዝናል

ኧረ የተዋህዶ ልጆች እንንቃ!

@tewahdo_media1
931 viewsedited  08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 10:48:27
ገብርኤል ኃያል መልአከ ሰላም መልአከ ብሥራት
የምታወጣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከሚነድ እሳት
ፍቅርህ ተስሏል በልባችን
ፊትህ ቆመናል ባርከን ብለን

አዝ፡-------------------
የጽናታቸው ዝናው ሲሰማ
ከዛ ባቢሎን ከሞት ከተማ
ህፃናት ሳሉ በራ እምነታቸው
ቆመህ ተገኘህ መሐከላቸው

አዝ፡--------------------
ውኃው ሲዘል ቢያስደነገጥም
በጋኖቹ ውስጥ ቢነዋወጥም
ፀንተው ዘመሩ ልጅና እናቱ
አንተ ስትደርስ ከዚያ ከእሳቱ

አዝ፡---------------------
ቂርቆስም ፀና ሞተን ሳይፈራ
አንተ ስላለህ ከነርሱ ጋራ
አትፍሪ አላት ስለምን ትፍራ
አምነው ድል ነሱት ያንን ተራራ

አዝ፡---------------------
እኔም አምናለሁ አድነኝ ብዬ
ፈጥነህ አማልደኝ ከቸር ጌታዬ
ክፉውን ዘመን የማልፍበት
ፅናቱን ስጠኝ ድል ልንሳበት

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
859 views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ