Get Mystery Box with random crypto!

'፮ኛ ኮርስ 'የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት' #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አም | የተዋህዶ ቤተሰቦች✝ ኮርስ መስጫ

"፮ኛ ኮርስ "የቤተ ስርስቲያን ሥርዓትና ምጢራት"

#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
፫.፭, #ምሥጢረ_ንስሐ
፫.፭.፩, #የንስሐ_ትርጉም
ንስሐ ሥርው ቃሉ "ነስሐ" የሚለው የግዕዝ ግሥ ሲሆን ትርጓሜውም ተጸጸተ፣ ተቆረቆረ ማለት ነው።

ንስሐ ሊሠራት ስለማይገባ ሥር ወይም ስለ ኃጢአት ማዘን፤ ምነው ባልሠራሁት፣ ምነው ባላደረግሁት፣ ምን ቀን ጣለኝ ብሎ መቆጨት ነው።

የንስሐ ልብ ያለው፣ ንስሐ በመግባት ፍሬ ማፍራት የሚችለው በሥነ ፍጥረት የሰው ልጅ ብቻ ነው። ሌሎች ፍጥረታት የመጸጸት ፍጥረት የላቸውም።

፫.፭.፪, #የንስሐ_ምንነት
ክርስቲያን በጥምቀት ከዓለም ክፉ ሥራዎች ሁሉ የተለየና የሞተ ነው። ሕይወቱ በሙሉ ለክርስቶስ የተሰጠ ነውና። "እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ።" (ሮሜ 12፥1-2) ተብሎ እንደተጻፈ የክርስቲያን አካሉ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያም ነው ተብሏል። (1ኛ ቆሮ 6፥19)

ይሁን እንጂ የሰው ልጅ ስሑት/የሚሳሳት በመሆኑ ከኃጢአት የተነሣ ንጽሐ ሥጋውና ንጽሐ ነፍሱን ያሳድፋታል። በኃጢአት ወድቆ ፈጣሪውን ይበድላል።

ከዚህም የተነሣ የክርስቲያኖች ጉዞ ፈተና የበዛበት እየወደቁ እየተነሡ የሚጓዙት እንጂ ኃጢአት ሳይሠሩ እንደመላእክት በንጽሕና አልያም ወድቀው ለዘላለም እሳት እንደተጠበቁት አጋንንት ተስፋ የሚቆርጥበት ሕይወት አይደለም።

አበው "ቅዱሳንን ቅዱሳን ያስባላቸው ኃጢአትን ሠርተው ባለመውደቃቸው ሳይሆን ወድቀው በንስሐ መነሣት መቻላቸው ነው።" ማለታቸው የክርስትናን ኑሮ ይልቁንም የንስሐን ምንነት ፍንትው አድርጎ የሚያስረዳን ነው።

ከላይ በትርጓሜው እንደተመለከትነው ንስሐ ኃጢአተኞች ተጸጽተው ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቁበት ደገኛ ሥርዓት ነው። የተባለውም ለዚህ ነው።

ምሥጢር ያስባለውም ለካሕናት በተሰጣቸው በዓይን የማይታየው ሥልጣን አማካይነት በንስሐ ተመላሾች የሚያገኙት የኃጢአት ሥርየት ስላለ ነው። "ንስሐ መግባት" ማለትም በተሠራው ኃጢአት መጽናናትና ዳግመኛ ያንን ኃጢአት መልሶ ላለመሥራት መወሰን ነው።
◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄◄

@Tewahdo_Haymanotie
#ቀጣይ_ትምህርታችን-->የንስሐ አመሠራረት፦
#ወስብሀት_ለእግዚአብሔር_ወለወላዲቱ_ድንግል_ወለመስቀሉ_ክቡር_ይቆየን!!

ገፅ ➒❼