Get Mystery Box with random crypto!

የመድሀኒት እናት ትንሹ ሔኖክ እኔ ሰው ነች ብዬ ፈጽሞ አልስትም እሷ ሰው ከሆነች እኔ ሰው አ | 🌹ትንሹ ሔኖክ

የመድሀኒት እናት

ትንሹ ሔኖክ

እኔ ሰው ነች ብዬ ፈጽሞ አልስትም
እሷ ሰው ከሆነች እኔ ሰው አልሆንም
የመለኮት እናት የብርሀን መገኛ
ድንግል እናቴ ናት የፍጥረት መዳኛ
እንደ ጸሀይ በርታ ደምቃ የተገኘች
ንጽሂተ ንጹሀን ቅድስት እሷ ነች
የሰው ልጅ ስለሷ የሚወዛገበው
ከዝምታ ውጪ ምንን ተናግራ ነው
ቢወዱ ቢጠሏት ምላሽ የማትሰጥ
የእናትነት ፍቅሯ ፍጹም ማይቋረጥ
የመድሀኒት እናት ድንግል መድሀኒት ነች

ውይይይይ የኔ እናት ማርያም ውድድድድድድድ ነውኮ የማደርግሽ ይኸው ስምሽን ሀያ አራት ሰዓት እየጠራሁ ልረካ አልቻልኩም ምን ትዪኛለሽ? ኧረ እናቴ እንዳንቺ ያለ የሚወደድ የሚፈቀር የሚጣፍጥ ልብን የሚገዛ ምን አለ በምድር። እኔ ካንቺ ውጭ የሚበልጥብኝ አንዲት ነገር በምድር የለም ሊኖርም ፈጽሞ አይችልም። እናቴ ፍቅርርርቅር አደርግሻለሁ ብዙዎቻችሁ እናቴ ለምን ትላለህ ብላችሁ ልታርሙኝ ትሞክራላችሁ። ቆይ እኔ ስለናንተ ውሎና ስራ ምን አውቃለሁ። እኔ የማውቀው ስለራሴ ነው። እኔ ደግሞ ጠዋትና ማታ ከስሯ አልተለየሁም ስለዚህ እናታችን ብዬ አላሽቃብጥም የማውቀው ስለራሴ ነው። ደግሞ ማርያም እናቴ የፍጥረት ሁሉ እንደሆነች እንኳን እናንተ ዳቢሎስም ጠንቅቆ ያውቃል። ዋናው ማወቁ ሳይሆን እንደኔ መጠቀሙ ላይ ነው። ይኸው እርርርር በሉ እናቴ የኔ የብቻዬ ማርያም ውድድድድ አደርግሻለሁ

ውድድድድድድ የምታደርጊኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ