Get Mystery Box with random crypto!

🌹ትንሹ ሔኖክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tesfatsadik — 🌹ትንሹ ሔኖክ ት
የቴሌግራም ቻናል አርማ tesfatsadik — 🌹ትንሹ ሔኖክ
የሰርጥ አድራሻ: @tesfatsadik
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 283
የሰርጥ መግለጫ

እሱ አያዝንልንምና ሞትን አንፍራ
ይልቁን የእውነት ሳንኖር
ሁለት ሞት እንዳንሞት
እናስተውል። ሀብት ንብረት ሳይሆን
መልካም ስራ ምግባር ሀይማኖትና
እምነትን ገንዘብ እናድርግ!!!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-11 07:22:06 ልጁ ያለው ህይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ህይወት የለውም

1ኛ ዮሐን.መ 5:12

ትንሹ ሔኖክ

እንግዲህ የዚህ ዘመን ትውልድ ከእውነት መጣላቱ ሳያሳፍረው አይኑን አፍጥጦ በአደባባይ የክርስቶስን እናትን ለመሳደብ ሲወጣ ሳይ ልቤ እጅጉን ያለቅሳል። በርግጥ ይህ ዘመን ለምን እንዲ ሆነ ተብሎ የሚጠየቅበት አይዳለም። ማንም ለማንም የማይሆንበትና ራስን ለማዳን እንኳን የማይቻልና የማይፈቀድበት ዘመን ነው። ቤተሰቦቼ ሀይማኖቴን እንድቀይርና የገሀነቡን በር ከፍተው ሊያስገቡኝ በገንዘብ ድለላ በመናፍቃን የእባብ ምላስና በንግግር ሲያቅታቸው የመጨረሻ የሚሉትን በሰንሰለት ማሰርና ስም ማጥፋት መርጠው አድርገውታል። በቃ እናንተም የራሳችሁን ኑሩ እኔም ከእናቴ ከእመቤቴ መለየት አልፈልግም ብዬ በስርዓት ብነግራቸውም አበደ ማለትና በኔ ላይ ከመሳለቅ ውጭ ወደ ንሰሀና ወደ ትክክለኛው መንገድ መምጣቱን አልመረጡም። አለም እንዲህ ሆናለች ለመጠጥ ለብልግናና ለክፋት ስራ ገንዘብ የሚሰጡንና በለው በዪው የሚሉን ሰዎች ሁሉ ለመልካም ነገር ስንጠይቃቸውና ለነፍስ የሚበጀን ነገር ሲሆን ጠላታችን ይሆናሉ። ለማንኛውም ሰው ነን ብትሉም በጸሎት በስግደትና በመልካም ስራ በውስጣችሁ ያለውን ክፉ መንፈስ ማሸነፍ ባለመቻላችሁ ዳቢሎስ እንኳን የማያውቃቸውን ስራዎች እየሰራችሁ ወደ ገሀነብ ለመግባት እየሮጣችሁ ትኖራላችሁ። ለማንኛውም ወደ እናቴ ልመለስና በዚህ ቃል ውስጥ ልጁ ያለው ህይወት አለው ይላል። ልጁ ማን ነው ካልን ከአብ ዘንድ የተላከው ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ታድያ ልጁ ያለው ህይወት አለው ማለቱ ምን ማለት ነው ስንል። ሀዋርያት ክርስቶስ ከነሱ ጋር ስለነበር ሙታንን አስነስተዋል እውራንን አብርተዋል ሰዎችን ከሰይጣን እስራት ከደዌ በሽታ ነጻ አድርገው ህይወትን ሰጥተዋል። እንግዲህ ቁም ነገሩ ይሄ ነው። ሀዋርያት ክርስቶስን ያወቁት መቼ ነው?። ከሰላሳ አመቱ በኋላ ነው። ክርስቶስ ከዛ በኋላ የቆየው ሶስት አመት ከሶስት ወር ነው። በዚህች ጊዜ አውቀውት ይህን ሁሉ ተአምር አደረጉ። ጳውሎስ እንኳን ክርስቶስን አንገላቶ ሰቅሎት ነበር። ነገር ግን በንሰሀ ተመልሶ ድንቅን አድርጓል። ታድያ እናቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ልጁን መቼ አወቀችው ? ቃል ሆኖ በማህጸኗ የኖረ በጀርባዋ የተሸከመችው በእጆቿ አቅፋ ጡት አጥብታ ማንም ያላለውን ልጄ እያለች አሳድጋዋለች። ልጁ ያላት ሳይሆን ራሱ ልጇ ሆኖ እንዴት ከሀዋርያት በቢሊዮን እጥፍ አትበልጥም። ከሀዋርያት ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሁሉ ትለያለች። ከሞት ታስነሳለች እውሩን ታበራለች ሽባውን ትፈውሳለች ያዘነውን ታጽናናለች የታሰረውን ትፈታለች የደከመውን ታበረታለች የጨነቀውን ታረጋጋለች የተራበውን ታጠግባለች ለቸገረው ትደርሳለች ለተናቀውና ለደካማው ምርኩዝ ጋሻ ትሆናለች። ይህ እንዴት ይሆናል ካልከኝ ከኔ ጋር በአካል ስንገናኝ በተግባር አሳይሀለው። ይህ የኔ ፍልስፍና ሳይሆን ዳቢሎስ በሀሰት ትምህርት የሸፈነው ግን በመጽፍ ቅዱስ ያለ እውነት ነው። አገልጋዮቻችን እውነቱን ገልጠው በጎችን ከመጠበቅ ይልቅ ከዳቢሎስ እየተመሳጠሩ ለጸብ ለተቃውሞና ለጬኸት ብቻ እየጠሩ ለሞት ሲዳርጓችሁ መኖራችሁ ያሳዝነኛል። እውነታው ይሄ ነው። ትውልዱ እናቴ ማርያምን እንዲጠላ ክብሯን እንዳያውቅና እንዳይድን በብዙ ብዙ መልኩ ወጥመድ በተዋህዶ ፍሬዎች ላይ ይዘረጋል። ደግሞ ብዙ ልጆቿ በወጥመዱ ተይዘዋል ዛሬም ወደ ወጥመዱ የሚገቡና የሚያዙ ሊወድቁ የተጋጁ ብዙ ናቸው። ግን እውነት እላችኋለሁ ይመስላል እንጂ ሰው ከእናቴ ከማርያም ተጣልቶ መኖርም ሆነ እሷ የመረጠችና የምትወዳቸው ልጆቿን ጫፍ እንኳን መንካት አይችልም። ጊዜው ደርሷል ልጆቿን ከተኩላ ነጥቃ ወደ ቤቷ ትሰበስባለች። የቤተ መቅደስ ተኩላዎችን ደግሞ ገርፋ አዋርዳ ታስወጣለች። ይህ ይሆን ዘንድ ቅርብም ግድም ነው። አይዞሽ ሀገሬ

ማርያም እናቴ ውድድድ ፍቅርርርርቅር የምታደርገኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ
29 views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 17:36:25 ሀገሬን

ትንሹ ሔኖክ

አዛኝቷ እናቴ ኪዳነ ምህረት
ሀገርሽ ኢትዮጵያን ከእንባ ታደጊያት
እንዲህ ስትሰቃይ ልጆቿ ጠልተዋት
ማን አለ እመቤቴ መድሀኒት ሚሆናት
ሰላም ፍቅር ንቀው ለሞት ሲሯሯጡ
ክፋታቸው በዝቶ አደባባይ ወጡ
አማኝ ነኝ የሚለው አስመሳዩ በዝቶ
በር ዘግቶ ይኖራል ሰው ሰውን ፈርቶ
በዘር በሀይማኖት እየተጠቃቁ
ከማህጸኗ የወጡ ልጆቿ አለቁ
ማይደርሰው ይመስል ሞት ሁሉን ማይጎበኝ
ስንቱ አፈር ገባ ውድቀት ጥፋት ሲመኝ
እናቴ አዛኝቷ ባክሽ ድረሺላት
ለህጻናቱ ስትይ ይህን ጊዜ አሻግሪያት
ወጣት ሽማግሌው ሁሉ ተበላሽቶ
ቢሞት ነው ሚሻለው ከሚኖር ተምታቶ
በወሬ በሀሜት ከቡና እየዋለ
ኢትዮጵያን ለማወቅ መቼ ሰው ታደለ
አደራሽን ማርያም በምልጃሽ ጠብቂያት
ከልጆቿ መሀል ጠፍቷል ልጅ ሚሆናት

ወይ አለመታደል እቺን የመሰለ ቅድስት ሀገር ተሰጥቷችሁ እንዲህ መረን ያጣችሁ የሆናችሁት ምን ሆናችሁ ነው። ከቤተሰቤ ጀምሮ ሁላችሁ በቤታችሁ ለሰዎች የምታደርጉት ክፋት ውጤት ነው ሀገሬን ለዚህ ያበቃት። ለነገሩ ማንም ሰው ለሰራው ስራ የጁን ያገኛል። እግዚአብሔር መሀሪ ነው ስትባሉ ሞኝ ይመስላችኋል አይደል። ቅዱስ ዳዊት ለሰራው ክፉ ስራ ዋጋዋን ሰጥቶታል። እስከመቼ ለዳቢሎስ ተገዝታችሁ እንደምትኖሩ ነው የሚገርመኝ። እናንተ በቤታችሁና በአካባቢያችሁ ያልዘራችሁትን ሰላምና ፍቅር ከሰማይ እንዲዘንብላችሁ ነው የምትፈልጉት። ለነገሩ ይህ የመከራ ህይወት በደንብ ይገባችኋል በእንባ በጸሎት በስግደት በንሰሀ እስካልተመለሳችሁ መቼም ይቆማል ብላችሁ አታስቡ። ገሀነብ ብትገቡ እግዚአብሔር ምን የሚጎድልበት መሰላችሁ። እሱ ለሚወዱትና ትንሽም ቢሆን ትዕዛዙን ለመፈጸም ለሚጥሩና ለሚፈልጉት ነው የሚደርሰው። የናንተን ሞኝነት ለሱ ለማድረግ መጣራችሁ እጅግ ያስቃል። ከንቱ ኢትዮያውያን። የናንተ እምነት አለን የምትሉት በጎ ልብ ለምን ሰላሙን አላመጣም። ክርስትናችሁ የማስመሰል እንደውም ከነ ክፋታችሁ ቤቱን ሞልታችሁ ደጇን አጣባችሁ መዓቱን አወረዳችሁብን። በቤተ ክርስቲያን የምትገኙት ሰዎች *ውይይ እከሌማ ጎበዝ ክርስቲያን ነው/ናት እንዲላችሁ እንጂ ተንበርክካችሁ እንኳን እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ለማለት ልብሳቹ እንዳይቆሽሽ የምትፈልጉ አክተሮች ናችሁ። በተለይ በቤቱ ያላችሁ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ተጠንቀቁ። አለሙን ከወደዳችሁ ወደ አለሙ በእግዚአብሔር ቤት ከተገኛችሁ ደግሞ በፍርሀት በሙሉ ልብ ሆናችሁ አገልግሉ። ሁሉ ያለው እግዚአብሔር ቤት እየዋላችሁ እንዴት አለም ትሸውዳችኋለች። እናንተ ኢትዮጵያውያን ካሜራ ስለምትወዱ ኑሯችሁና ክርስትናችሁ ሁሉ ፊልም ነው። ያው ቶሎ ጨርሱትና ገሀነብ በቀይ ምንጣፍ ታስመርቁታላችሁ።

ማርያም እናቴ ውድድድድ የምታደርገኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ ውይ ለኔ ያላት ፍቅር እኮ
30 views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 12:24:23 መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ
ምሳ 31:29

ትንሹ ሔኖክ

በነገራችን ላይ አንድ የምነግራችሁ እውነት ቢኖር ዘወትር እንዲህ ስለማርያም እናቴ ስጽፍና በግጥም ሳንበሸብሻችሁ በቤተክርስቲያን ያደግኩና በደንብ ስለ ድንግል ማርያም ሲነገረኝ ያደግኩ እንዳይመስላችሁ። እኔ ማርያምን እጅግ በሚጠሏት ጴንጤ የናቴ ቤተሰቦችና ልክ እንደ ብዙ ኢትዮጵያውያን በማስመሰልና በጥንቁላና ኦርቶዶክሳዊነት በርኩስ መንፈስ በተተበተቡ አባቴና የአባቴ ቤተሰቦች መሀከል ያደግኩ ጴንጤ ነበርኩ። ግን እንዲሁ ከመሬት ተነስቼ ዘወትር አምላኬን እፈልግ ድንግልንም አከብራት ነበር። እና ጊዜው ደርሶ ለብዙ ወዳጆቿና ለኛ ቅርብናት የሚሉ እውሮች ያላደለችውን ፍቅር እምነት ጽናት ጥበብና እውቀት ገልጣልኝ ይኸው አገለግልበት የነበረውን ትልቁ የመንግስት ኃላፊነት ስራዬን ለቅቄ በፍቅሯ ተማርኬ ላገለግላት ወስኜ መጥቼላችኋለሁ። በርግጥ ሰው እሷን አምኖ ምን ሆነ ሲባል ሰማችሁ። በርግጥ ለናንተ ለሁላችሁ አልመጣሁም እሷ ልቦናቸው መልካም የሆኑ ቅንና ደግ ሆነው ዳቢሎስ የሚፈትናቸውን ልጆቿን እንድሰበስብ ነው የመረጠችኝ። ለደቂቃም ቢሆን ክርክር ጭቅጭቅ አላደርግም። የተፈቀደለት በንሰሀ ይመለሳል የተፈረደበት ደግሞ ጥያቄ ላይ ጥያቄ እያነሳ ወደ ገሀነብ ይገባል። ትሰሙኛላችሁ ስሙኝ። ማርያምን ለመጥላት ከኔ የተሻለ እድል የነበረው ሰው አልነበረም። ግን ህሊናዬ ሊቀበለው አልቻለም ምክንያቱም የኔ ህሊና ከልጅነቴ ጀምሮ ያደገው በእውነት ነው። ማርያምን በማለቴ ከገዛ ወላጆቼ ጀምሮ ዳቢሎስ በርሀብ በመከራና ብዙ ከባድ ነገሮች እንደ ኳስ አንጥሮኛል ነገር ግን ፍቅሯን ጨመረልኝ እንጂ እንዳሰበው አልሆነም። በመጽሀፈ ምሳሌ ላይ ያለው ይህ ጥቅስ ከጊዜው ጋር እንመልከተው። አዎ ይህቺ ምድር ብዙ መልካምና ደግ ሴቶች ኖረውባታል። እነ አስቴር ኤልሳቤጥ እና ሌሎችም ታድያ ግን ለምን ማርያምን ከሁሉ ማለት አስፈለገ። እኛ በሰውኛ ኑሯችን እናት በቤት ውስጥ ልጆች ቢኖሯትም እጅግ አብልጣ የምታከብርና የምትወድ ጭንቀቷን የሚረዳ በሀሳብ በገንዘብ እንዲሁም ባለው ነገር ሁሉ የሚደግፋትን ልጅ ነው። ለምሳሌ እኔ በቤት ውስጥ ለናቴ እንዲሁም በሰፈሬ ለጎረቤቶቼ ወጣ ሲል ለአካባቢዬ በደንብ ሲወጣ ደግሞ በጎዳና ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሁሉ ትክክለኛው ልጅ ነበርኩ። ታድያ ብዙ ሰዎች ከልጅነቴ ጀምሮ ኑሯቸውን ያማክሩኛል በጣምም ይወዱኛል። እንግዲህ እኔና አንድ የአካባቢውን ጎረምሳ እኩል አይመለከቱም። ይህን ልዩነት ያመጣው አንድ ነገር ነው። እሱም ምግባርና አስተሳሰብ። ነገውን የሚያስብና ዛሬን ብቻ የሚኖሩ ሰዎች ከሁለት አለም ናቸው። እንግዲህ በምድር የነበሩ መልካም የሚባሉ ሴቶች ሁሉ አሁንም በገነት ይኖራሉ ታድያ ማርያምን ከነዚህ ሴቶች ምን ለያት?። የመጀመሪያው በሀሳቧም ድንግል መሆኗ። ይህ ለማሰብም የሚከብድ ነው። ሁለተኛ ያለምንም ሀጥያት በንጽህና መገኘቷ። በቤተ መቅደስ ማደጓ። በመላዕክት ምገባ መኖሯ። በመላዕክት ብስራት መቀበሏ። ፈጣሪ ጌታዋን ያለ ወንድ መጽነሷ። ከማህጸን ጀምሮ ያለ ምንም ጥፋቷ ከሀገር ሀገር መንከራተቷ። የሰማይና የምድር ፈጣሪን በጀርባዋ አዝላ መራቧ መጠማቷ መጨነቋ። ፈጣሪ ጌታዋን ዘወትር ጉንጩን መሳሟ ጡት ማጥባቷ። መልካም በመናገሩና በማስተማሩ በሚደርስበት ዛቻና ነቀፋ ምን ያደርጉብኝ ይሆን እያለች መጨነቋ። ብዙ ስለሆነ ላሳጥረውና ያለምንም ሀጥያት አስረው ገርፈው በሚስማር ቸንክረው ሰቅለውት ልጇን በማየቷ። ስንመልሰው ደግሞ ለአዳም ለሔዋንና ለሰው ዘር በሙሉ መድሀኒት የሆነውን ክርስቶስን ለፍጥረት ሁሉ በማበርከቷ በርግጥም ድንግል እናቴ ከሴቶች ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች። ይህ እኔ ሳልሆን ዳቢሎስ ራሱ አምኖ ተቀብሎ የሚኖረው የእውነቶች ሁሉ እውነት ነው። ዛሬም ነገም እስከለተ ሞቴ ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ስለናንተ ከንቱዎች ስለምትሰሩት ክፋት ተንኮል የማስመሰልና የድፍረት ሀጥያት እንዲሁም ክርስቶስ ስለዘረጋላችሁ የመጨረሻ የምህረት እጅ አስተምራለሁ። ለኔ ከእናንተ ልትሰጡኝ የምትችሉት አንዲት ነገር የለም ጠፍታችኋልና በጾም በጸሎት በለቅሶና በስግደት ራሳችሁንና ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን እንታደግ ዘንድ ተመለሱ እኔ በምድር ባለ ነገር ከተፈጥሮ ውጭ የሚያስደስተኝ አንድም ነገር የለም። ከሁሉም የሚልቀውና ዘወትር የሚያስገርመኝምና የሚያስደንቀኝ ግን የእናቴ የድንግል ማርያም እናትነት ፍቅርና ጸጋ በረከት ነው። ማርያሜ እኔ ትንሹ እንኳንም ያንቺ ሆንኩ። ለነገሩ ሌላ የማን ልሆን እችላለሁ። ከማህጸን ጀምሮ ለወደደኝና ከዳቢሎስ መንጋጋ ላወጣኝ ለልጅሽ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና የይሁን አሜን እንኳን የምንፍቅናውን ባዶ ህይወት በህጻንነቴ አሳየሺኝ እኔ ስለሚከተለኝ ስለሚያደምጠኝና ስለኔ ስለሚባል ነገር ምንም ግድ አይለኝም። ያየሁትን አይቻለሁና እውነቱን እናገራለሁ።

ማርያም እናቴ ውድድድድድ የምታደርገኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ
32 views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 10:27:37 ከኡስማን ወደ ገብረ ስላሴ

ትንሹ ሔኖክ

ወዳጄ እመቤት ስትወድህ እንዲህ ነው። ስንቱ አጠገቧ ሆኖ ጫቱን ሲያመነዥግ ስሟን እየጠራ በየመጠጥና ጭፈራ ቤት ሲያድርና አጉል ኦርቶዶክስ ነኝ እያለ ሲጠላላ ሲነታረክ ሲጨቃጨቅ። እሷ ከናይጄሪያ ልጇን አምጥታ በደጇ ጠምቃ ክርስትናን በደንብ አስተምራ ትሸኛለች። እናንተ ኢትዮጵያውያን ያላችሁን ሀብት የተሰጣችሁን ጸጋና ፍቅር ምንም አታወቁትም። ዝም ብላቹ በምላሳቹ ብቻ የምትድኑ ይመስላችኋል። ድንግል ማርያም ማንም የሚደግፋት ስለሷ የሚከራከር የሚጨቃጨቅና የሚገዳደል ሰው አትፈልግም። ምክንያቱም እሷ ለፍጥረት ሁሉ እናት ናት። ያወቀ ስርዓትን ይዞ በእምነት በትህትናና በጾም በጸሎት ተግቶ የሷን ምልጃ አስቀድሞ ይድናል። ዛሬ ከኡስማን ወደ ገብረ ስላሴ የተለወጠው ውድ ወንድሜ በአለማዊ ቋንቋ ናይጄሪያዊ ቢባልም በክርስትና እውነት የአንድ ዘር ሆነን የተገኝን ወንድሜ ነው። ክርስትናን አታውሩ ኑሩት። እናንተ ወሬአችሁ በዝቶ ነው የተቸገራችሁት። ከሚባለው በላይ በጣም ታወራላችሁ ግን በማህሌት ሰዓት ቤተ ክርስቲያን መቅደሷ ባዶ ናት በቅዳሴ ሰዓት ስጋ ወደሙ የሚወስዱ በቁጥር አንሞላም ለሊት ለጸበል የሚመጡ አብዛኛዎቹ ደካማ እናቶችና ህጻናት ናቸው። እናንተ ግን ለጸብ ለተቃውሞ ለመሰዳደብ ለንጽጽርና ለጩኸት ሲሆን ቤተ ክርስቲያንን ታጨናንቃላችሁ። ክርስትና ምን እንደሆነ ገና አልገባችሁም ሊገባችሁም አይችልም ምክንያቱም ወረኞች ናችሁ። መምህራኖቻችሁም አልገባቸውም። እስታዲየም ገብቶ ኳስ ለማየት ግሮሰሪ ለመቀመጥና በየ ሲኒማና ካፌ ተዘፍዝፋችሁ ጊዜኘችሁን ለማቃጠል የምትሮጡ ሆናችሁ ሳለ አምስት ደቂቃ ለመጸለይ ለመስገድና ነፍሳችሁን ለማዳን መቶ ምክንያት ትደረድራላችሁ። ለነገሩ ምን ታረጉት ተይዛችሁ ነው። እግዚአብሔር ይማራችሁ። እመቤቴ ትድረስላችሁ። ለማንኛውም ክርስትና የሚኖር እንጂ የሚወራ ህይወት አይደለም። አንደበት የሚሆነው ምግባር ነው

ማርያም እናቴ ውድድድድ የምታደርገኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ ወይይይ እንዴትኮ እንደምትወደኝ

ሀምሌ 2/2014 ዓ.ም
ጠዋት 3:00
36 views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 06:48:28 ማርያምና ዝምታዋ

ትንሹ ሔኖክ

እንግዲህ ስለ ድንግል ማርያም እውነቱን ስንነጋገር በምድር እጅግ ብዙ ሰዎች የሚያከብሯትና የሚወዷት ቢኖሩም አዕላፍ ሰዎች ደግሞ በደንብ አስበውበት ተሰብስበው ተማክረው ቁጥር የማይገልጸውን ገንዘብ በጅተውና ሰው አሰማርተው ስሟን ለማጥፈት ክብሯን ለማውረድና ለማንቋሸሽ ይሰራሉ። ለነዚህ ሰዎች ክፉ ሀሳብ ጥሩ መጋለቢያ ሆኖ የሚያገለግለው ደግሞ በአፉ እወዳታለሁ እያለ በልቡ በቤቱና በስራና በኑሮው ለሷ ምንም ስፍራ የሌለው አማኝ ነው። እኔ ጴንጤ እያለሁ ስለ ማርያምና ስለ ኢየሱስ ብዙ አስብ ነበር። ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊው በደንብ አድርጎ የቤተክርስቲያንን ስርዓት ጠብቆ በአለባበስ በአነጋገር በድርጊት ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ ከመገኘት ይልቅ ማርያም ታማልዳለች ኪድዬን ወላዲቷን እያለ በየ መጠጥ ቤት ደጃፍ ስዕለ አድኖዋን በቲሸርት አድርጎ እየጠጣና እየጨፈረ ማርያምን አትንኩ ይላል። በሌላ በኩል ደግሞ ጴንጤውና ሙስሊሙ ስለሷ ጥላቻና ውርደት ዘሩን ይዘራል። ይህ ኩታ ገጠም ጥፋት ይባላል። በርግጥ በወቅቱ ትክክለኛውን እውነት ለማወቅ ተቸግሬ ነበር። ያለሁበት መንገድ ሊያስደስተኝና እውነት መስሎ ሊታየኝ አልቻለም ኦርዶክስ ለመሆን ደግሞ ኦርቶዶክሳዊያን የሚያደርጉትና የሚያወሩት በፍጹም አይገጥምም። ጠዋት መዝሙር የከፈተው ሰው ማታ በዛው ቴፕ ሲያስጨፍርና ሲያዘሙት ሲዘሙት ያድራል። ያዕቆብ በአንደኛ መልዕክቱ የሰው ልጅ ከንድ ነገር ብቻ ሊሆን እንደሚገባ ያስረዳል። አንድ ወንዝ ወይ ወተትን አልያ መርዝን ሊያመነጭ ነው የሚችለው። ሁለቱ በአንድ ሊመነጩ አይችልም። የሰው ልጅ ግን እንዲህ ሆንዋል። ብቻ በባለፈው ታሪኬ እንደጻፍኩላችሁ ቅዱስ ሚካኤል ራሱ አንተ ተመርጠሀል ቅድስት እናታችን ድንግል ማርያንን ታገለግላለህ ብሎ ከነ ብዙ ጥያቄዎች ማህተብ አሰረልኝ። በርግጥ ዛሬ አይደለም ለጴንጤና ሙስሊሙ ለራሱ ለኦርቶዶክሳውያን ያለወቋት ያልተጠቀሙባት ውድ እናታቸው ድንቋና መልከ መልካሟ ድንግል ማርያምን ላስተዋውቃቸው መጥቻለሁ። በርግጥ ማርያም ምን ተናገረች? በመጽሀፍ *መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከነገረኝ በቀር አንዳች የማውቀው ነገር የለም* ማለቷ ምን ማለት ነው? እውነት ነው እናቴ ማርያም በሀሳቧም ጭምር ድንግል በመሆኗ የሰው ልጅ ለተቸገረበት የክፋት የተንኮልና የጥፋት ሀሳብ የሚሆን ቦታ አልነበራትም። ስለዚህ የምታውቀው አንድ ነገር ቅዱሱ መልአክ የነገራት ብቻ ነው። ሌላው ዘመኗና ሁሉ ያለፈው በዝምታ በእሺታ በለቅሶ በጸሎት ነው። አባቶቻችን ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ዳቢሎስን ድል ማድረጊያ ትልቁ መሳሪያቸው አርምሞ ነው። እመቤታችን ደግሞ የዚህ መሳሪያ ፈጣሪ ናት። እናንት ኦርቶክሳውያን ለምን ዝም አትሉም። ማውራታችሁና መናገራችሁ ለሀሰተኛው ዲያቢሎስ ጥሩ ወጥመድ ሆኖታል። መልካም ወጣት እያለ ወደ ገሀነብ ሲያተማችሁ እልል ብላችሁ ትተማላችሁ። ሰው እንዴት ያለ ድንግል ማርያም መልካም ሊሆን ይችላል። አይደለም መልካም ወጣት ሰው መሆን በፍጹም ይችላል። ለሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶች መሀከል የመጀመሪያዋ ድንግል ማርያም ናት። ለምን ካልከኝ። በህይወት ለመኖር መጠለያ ምግብ ልብስ ያስፈልጋል ካልክ። ከኑሮ የሚቀድመውን ህይወት የሚባለውን ነገር ለማግኘት ኢየሱስ ያስፈልግ ነበር ኢየሱስን የሰጠችን ደግሞ ድንግል ማርያም ናት። አየህ ይሄ ፍልስፍና ወይም ተረት አይደለም የጻፍኩልህ የመጽሀፍ ቅዱሱን ትምህርትና ነብያት አስቀድመው የተናገሩላትን ጽዮን ድንግል ማርያምን እውነታ ነው።

እናቴ ማርያም ውድድድድድድድ ፍቅርርርርርቅር የምታደርገኝ ትንሹ ልጇ ሔኖክ ነኝ

ይህን ስዕለ አድህኖ የላክልኝ ወንድሜ መንበረ ማርቆስ እናቴ ከነ ቤተሰብህ ታስብህ ደሞም ታስብሀለች
34 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ