Get Mystery Box with random crypto!

ምን ይበል ፈጣሪ ትንሹ ሔኖክ በጎ ነገር ጠልተን ከክፋት እየዋልን ምን ያድርግ ፈጣሪ ምን እን | 🌹ትንሹ ሔኖክ

ምን ይበል ፈጣሪ

ትንሹ ሔኖክ

በጎ ነገር ጠልተን ከክፋት እየዋልን
ምን ያድርግ ፈጣሪ ምን እንዲል ፈለግን
ሰው አለምላኩን ትቶ ለሰይጣን ሲገዛ
ለምን ይገርመናል ጨለማው ቢበዛ
በሀይማኖት በቋንቋ እየተለያየ
ፍቅርን ሁሉ ንቆ በሀጥያት ከቆየ
ሰላም በሀገር ጠፍቶ ሞትን ከለመድን
ምን ይበል ፈጣሪ ምን እንዲል ፈለግን
ደሀ ምስኪን ሳይንቅ በዝቅታ ውሎ
ስርዓት ዘርግቶ እንዲህ ኑሩ ብሎ
የጽድቁን መገኛ እውነትን ከሸሸን
መከራ ስቃዩ እንዴት ነው የሚያልፈን
ሀገሬ አትሞኝ ፈጣሪህን ተወው
የነገረህን ቃል መቼ ተቀበልከው
በራስህ መንገድ ላይ በደመነፍስ ኖረህ
ጌታ ወዴት አለ እንዴት ትለዋለህ
ፈረሱን ከጋሪ ቶሎ አስቀድመህ
ብትኖር ይሻልሀል በንስሀ ታጥበህ
አልያ እንዳለቀስክ ነፍስህም ቆሽሻ
ገሀነብ ትወርዳለህ ወደ ርስት ድርሻ

ቆይ እውነት እግዚአብሔር ምን እንዲል ፈለጋችሁ። በየ ቤታችሁና አካባቢያችሁ እንዲሁም በምትሄዱበት ሁሉ የምታደርጉትና የምተሰሙት ሀጥያትና ግፍ እያለ እንዴት እግዚአብሔር ይቀርበናል ብላችሁ አሰባችሁ። ዳዊት በመዝሙሩ እግዚአብሔር ሀጥያትን አብዝቶ ይጠየፋል ይላል። በራዕይ ማርያምም ላይ የሀጥዕ ሰው ነፍስ ለቅዱሳን መላዕክት እጅግ ትሸታቸዋለች ይላል። አሁን እኔ የምኖርበት አካባቢ ሙሉ ቀን sex በቅናሽ ዋጋ እንደ እቃ ይሸጣል። ገዢውም ከቁጥር በላይ ነው። ትልልቅ የሚባሉ የንግድ ቤቶች ስራቸው ይህ ሆንዋል። የቤቶቹ ባለቤቶች ደግሞ ለገብሬል ለማርያም ለሚካኤል ይህን አደረጉ እየተባለ በየ ቤተክርስቲያን ይሞገሳሉ። አይ ክፉ ዘመን። እናንተ እግዚአብሔር ቸር ነው ምስኪን ነው እያላችሁ ልታልቀ ጥቂት ነው የቀራችሁ። በኖህ ዘመን የነበሩ ሰዎች ለምን ንሰሀ አትገቡም ሲባሉ አሁን እናንተ የምትሉትን የልጅ መልስ ነበር የሚመልሱት። ቆይ እግዚአብሔር ሞኝ መሰላችሁ አይደል። ቆይ ምን ቸገራችሁ ምንስ አጎደለባችሁ እንዲህ የጠላችሁት? ተው የሀገሬ ሰዎች ንሰሀ ግቡ ተው ግን

ሰኔ 29/2014 ዓ.ም
ለሊት 11:00 ተጻፈ

ማርያም እናቴ ውድድድድድ የምታደርገኝ ትንሹ ሔኖክ ነኝ