Get Mystery Box with random crypto!

Tesfa

የቴሌግራም ቻናል አርማ tesfaevent — Tesfa T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tesfaevent — Tesfa
የሰርጥ አድራሻ: @tesfaevent
ምድቦች: ጥቅሶች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.66K
የሰርጥ መግለጫ

አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው?
እግዚአብሔር አይደለምን?

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-01-02 10:40:01
ደስ ብሎኛል!
ያለወንድ ፈቃድ ስለተወለደልኝ ኢየሱስ፤ ከብፅዕት ድንግል ማሪያም ስለተወለደልኝ ፤ ቀድሞም በሰማይ የነበረ ከክብሩ ወርዶ ስለተወለደልኝ፤ 
ነፍሱን ሊሰዋልኝ ሰለተወለደልኝ፤
የኃጢአቴ መስዋዕት ሊሆን ስለተወለደልኝ፤
እኔን ኃጢአተኛውን ሊያድን ስለ ተወለደልኝ፤ የእግዚአብሔር ፅድቅ ሊያደርገኝ ስለተወለደልኝ፤ ልደቱ ልደቴ ስለሆነ
ደስ ብሎኛል!
#ደስብሎኛል #tesfa

ደስ ያለው ሰው ፕሮፍይል ፒክቸር በመቀየር እና ሼር በማድረግ ይሀን የደስታ ምክንያት ለሌሎች እናጋራ!

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
2.1K views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 11:59:01
ከማንም እና ከምንም ነገር ይልቅ አንድ የእግዚአብሔር ቃል የሚታመን ነው። 
እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ይናገርሀል። በፍጥረታት፣ በነቢያት፣ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም  አሁንም በወንጌል አገልግሎት በተሰማሩ ባሪያዎቹ  እየተናገረ ነው። እግዚአብሔር የተናገረው ነገር የሚያፀና፣ የማይለውጥ ነው። ቃሉን አያጥፍም፣ አይጸጸትም፣ አይዋሽም ከአንደበቱ የወጣውን አይለውጥም። ለቃሉ ታማኝ አምላክ ነው።  እናም በቃሉ  ልትታመን ይገባልሀል።
ኃይል የእግዚአብሔር ነው። ታላቅ ኃይል፣ ሁሉን ቻይ የሆነው ኃይል፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል ሀይል።
እግዚአብሔርን በመስማት ውስጥ ወዳለው እረፍት ልትመጣ ትወዳለህ? @tesfa_mentor

#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
1.1K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 12:01:42
በእግዚአብሔር ላይ ያለህን እምነት  የምንትገልፅበት መንገድ  አንዱ እርሱን መጠባበቅ ነው።   በእግዚአብሔር በመታመን ምህረትን እንደሚሰጠህ እያወክ በሙሉ እምነት ወደ እግዚአብሔር ልትቀርብ ይገባል። ደግሞም እግዚአብሄር ለሚታመኑት ተስፋ  ነው።  ምንም እንኳን ምድራዊ ፈተናዎችህ  ቢበዙብህም ፤ እግዚአብሔር አብሮህ ካለ የሚገዳደርህ ምንም ነገር የለም።
የእግዚአብሔር አሰራር  ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ተመሳሳይ ሊሆን አይችልም። እርሱ እንደወደደ፤ በራሱ ግዜ ሁሉን መልካም ያደርጋል። ጌታ አይቸኩልም፤ ደግሞም አይዘገይም።  በምትጠራው  ጊዜ እንደሚሰማህ ፣ እንደሚመልስህ  ቃል ገብቷል።  ነፍስህን እግዚአብሔርን በመጠባበቅ ተስፋ  እንድታደርግ እና በእርሱ እንድንትደገፍ የህይወትህም መጠጊያ እርሱን እንድታደርገው ዛሬ ይሄን መልካም ዜና እነግርሀለሁ።
እግዚአብሔር ለነፍስህ ተስፋ ነው።
እግዚአብሔር ለነብስህ መሸሸጊያ ነው።
እግዚአብሔር ለነብስህ መጠጊያ ነውና።
ወደዚህ አባት ሊሆንህ፤ ሊያሳርፍህ ወደሚወድ አምላክ ልትቀርብ ትወዳለህ?
ለሚኖሩብህ ጥያቄዎች ሁሉ ልንረዳህ በዚህ አለን:@tesfa_mentor

#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
632 views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 11:59:01
እግዚአብሔር ስሜትህን እንዴት እንደሚረዳ፣ የሀዘንን ሸክም እንደሚሸከምልህ፣እንደሚራራልህ ታውቃለህ? ታላቁ ሊቀ ካህን ኢየሱስ በድካምህ ይራራልሀል። እንደማንኛውም ሰው የተፈተነ ነገር ግን ያለ ኃጢአት የኖረ፤ የሚረዳህና የሚያስብልህ አምላክ እንዳለህ ታውቃለህ?
እግዚአብሔር ልባቸው የተሰበረን ይመለከታቸዋል፣ ጩኸታቸውንም ይሰማል፣
ከመከራቸው ያድናቸዋል፣ ወደ እነርሱም ይቀርባል፣ ይጠብቃቸዋል ይቤዣቸዋል።
ወደዚህ መልካም አባት መቅረብ እንድትችል ልንረዳህ አለን  :@tesfa_mentor

መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!
#tesfa #hope #brightmonday


#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
604 views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 12:01:53
በእዚህ የእግዚአብሔር ቃል ክፍል ውስጥ ዳዊት የእግዚአብሔር መንገድ ፍጹም እንደሆን እና ዳዊትም ሊከተለው የሚገባውን መንገድ፤ እግዚአብሔር እንደሚያበራለት፤ እግዚአብሔርም መንገዱን እንደሚመራው ይናገራል።
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ ስትጀምር፤ የራስህን ፈቃድ ማድረግ ታቆማለህ የዛኔ ወደ ትክክለኛው መንገድ  መሄድ ትጀምራለህ ማለት ነው፤ እናም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስትከተል እና ስትፈጽም ያኔ መንገድህንም ፍፁም ያደርገዋል:: መንገድህንም ያቀናዋል::
ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ የለምና!
ከእግዚአብሔር በቀር አምባ የለምና!
እንደዕርሱ ያለ አምላክ የሌለውን፤ እንደዕርሱ ያለ መሸሸጊያ አለት የሌለውን፤ ፍፁም ወደሆነው፣ መንገድህን ወደሚያቀናው፤ ወደራሱ መንገድ የሚመራህን አምላክ ልታውቅ ትወዳለህ?
ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው? ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፤ መንገዴንም የሚያቀና፤ እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ፤ በኮረብቶችም ላይ የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው። (2ሳሙ. 22÷32-34)
ልንረዳችሁ በዚህ አለን:@tesfa_mentor

#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
709 views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 12:21:16
እስከ እርጅናህም ድረስ የማይተውህ
ለዘላለም የማይለወጥ እና የማይጥል  ያው የሆነ፤  በእሱ ፍቅር ውስጥ  በእሱ ርህራሄ እና እንክብካቤ ውስጥ፤  በእሱ ኃይል እና ጥበቃ፤ በተስፋ ቃሉ፤ እውነት እና ታማኝነት ለህዝቡ የሚራራ አምላክ ነው።    በጣም የቅርብ ወዳጅ ከሚያደርግልህ፣ ወይም ከሚችለው፣  ከሚያስፈልግህ በላይ ላንተ ቅርብ እግዚአብሔር ነው።  አንተን በሕይወትህ  ማሽቆልቆል ወቅት ፣በድካም ውስጥ ባለህ ግዜ  አይተውህም። ድክመቶች በላይህ  ላይ ሲሆኑ፣ መደገፍ እና መሸከም በሚያስፈልግህ  ጊዜ ሁሉ አብሮህ  ይቆማል! ይደግፍሀል። የእጁ ሥራ የሆንከውን አንተን አይተውህም።
ልንረዳችሁ በዚህ አለን:@tesfa_mentor


Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
647 viewsedited  09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-20 12:01:35
የእግዚአብሔር እቅዶች ትክክለኛና ልብህን በሰላም የሚሞላ ነው። በጭራሽ ተስፋ ለመቁረጥ፣ ለመበሳጨት፣ አይሳካልኝም ለማለት ምንም ምክንያት አይኖርህም :: የአንተን ዕቅዶች እንደፈቃዱ የሚያፀናልህ እግዚአብሔር ነው።  እግዚአብሔር መሥራት የሚፈልገውን ይሠራል። 

ይሄንን እውነት በመረዳት ውስጥ ለህይወትህ ሰላም ማግኘት ትችላለህ። አንዳንዴ እቅዶችህን ምታሳካው እራስህ እንደሆንክ በምታስብበት ጊዜ በመጨነቅ ብዙ ጉልበትህ ይባክናል፤ ነገር ግን  ሁሉን ለእርሱ አደራ ሰጥተህ  እንደ ፈቃዱ መኖር ስትጀምር ሰላም፣ ደስታ፣ እርካታህ  የተትረፈረፈ ይሆናል።
ልንረዳችሁ በዚህ አለን:@tesfa_mentor

#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
1.4K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 09:34:56
ይሄ ቃል በጣም ከሚያንጹ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንዱ ነው:: ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ጥላ ውስጥ መኖር ማለት በእግዚአብሔር ጥበቃ ቃል ኪዳን ስር መኖር ማለት ነው።
ልዑል የሚለው የእግዚአብሔር ስም እያንዳንዱን ፍርሀትህን ምታልፍበት ስም ነው:: "መጠለያ" እግዚአብሔር ከኃይላት ሁሉ የላቀና ከማንኛውም አምላክ በላይ የበላይ እንደሆነ ነው። ልዑል ካቀረበው የበለጠ አስተማማኝ መጠለያ የለም! ይህ ሀያል ስም ለየዓለሙ ሁሉ ሉዓላዊ ገዥ እና ኃይል ያለው ስም ነው:: እግዚአብሔርን ተከላካይህ፣ መሸሸጊያህ፣ እና ታማኝ ጠባቂህ ነው:: ዛሬ ቀንህን በልዑሉ ተሸሽገህ በእርሱ ተማምነህ የምትጀምርበት፤ ደግሞም ብዙ የምታፈራብት ሆኖ ምትጀምረው ይሁንልህ::

መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!
#tesfa #hope #brightmonday

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
2.1K viewsedited  06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 13:01:39
በእግዚአብሔር ብቻ ዕረፍት ታገኛለች። መዳን ከእርሱ ዘንድ ነውና:: እርሱ ብቻ አለት ነው፤ እርሱ ብቻ መሸሸጊያህ ነው:: በእርሱ ዘንድ ፍርሀት የለም:: ሁል ጊዜ መታመኛህን እግዚአብሔርን አድርግ:: ልብህን ለእርሱ አስገዛ:: እርሱ መጠጊያህና ተስፋህ ነው።
#tesfa #hope

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube
713 views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ