Get Mystery Box with random crypto!

በእዚህ የእግዚአብሔር ቃል ክፍል ውስጥ ዳዊት የእግዚአብሔር መንገድ ፍጹም እንደሆን እና ዳዊትም ሊ | Tesfa

በእዚህ የእግዚአብሔር ቃል ክፍል ውስጥ ዳዊት የእግዚአብሔር መንገድ ፍጹም እንደሆን እና ዳዊትም ሊከተለው የሚገባውን መንገድ፤ እግዚአብሔር እንደሚያበራለት፤ እግዚአብሔርም መንገዱን እንደሚመራው ይናገራል።
የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ ስትጀምር፤ የራስህን ፈቃድ ማድረግ ታቆማለህ የዛኔ ወደ ትክክለኛው መንገድ  መሄድ ትጀምራለህ ማለት ነው፤ እናም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስትከተል እና ስትፈጽም ያኔ መንገድህንም ፍፁም ያደርገዋል:: መንገድህንም ያቀናዋል::
ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ የለምና!
ከእግዚአብሔር በቀር አምባ የለምና!
እንደዕርሱ ያለ አምላክ የሌለውን፤ እንደዕርሱ ያለ መሸሸጊያ አለት የሌለውን፤ ፍፁም ወደሆነው፣ መንገድህን ወደሚያቀናው፤ ወደራሱ መንገድ የሚመራህን አምላክ ልታውቅ ትወዳለህ?
ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው? ኃይልን የሚያስታጥቀኝ፤ መንገዴንም የሚያቀና፤ እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ፤ በኮረብቶችም ላይ የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው። (2ሳሙ. 22÷32-34)
ልንረዳችሁ በዚህ አለን:@tesfa_mentor

#tesfa #hope
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube