Get Mystery Box with random crypto!

ደስ ብሎኛል! መድኃኒት ተወልዶልኛል! #day_5 የሰውን ልጅ ከኃጢአታቸው ለማዳን የተላከ የእግዚ | Tesfa

ደስ ብሎኛል! መድኃኒት ተወልዶልኛል! #day_5

የሰውን ልጅ ከኃጢአታቸው ለማዳን የተላከ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።ኢየሱስ!
ከነብያት ሰምተው ለሺህ አመታት የዚህን አዳኝ መወለድ ሲጠብቁ ለነበሩ ሁሉ የምስራቹን እንዲያበስሩ፤ መልአኩም ለእረኞች ተገልጦ የምሥራቹን ነገራቸው። እነርሱም መንጎቻቸውን ትተው የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደውን አዳኙን ሕፃን አይተው ደስታን አበሰሩ፤ አዳኙን ነገሩ። እግዚአብሔር ልጁን ስለ ኃጢያታችን ስለላከልን፣  በራሳችን ቅጣቶቻችንን እንድንሸከም ስላልተወን፣ ይልቁንም ከእርሱ ጋር እንድንታረቅ ልጁን ስለሰጠን፣  መድኃኒታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ስለተወለደልን   እድለኞች ነን።
ወዳጄ ሆይ ክርስቶስ በህይወትህ  እንዴት መድኃኒትህ እንደሆነ ለማወቅ በእርሱ ማመን እና በእርሱ መኖር አለብህ። እናም እሱ ስለተወለደ እና መሞትን ስለመረጠ፣ የመዳንን ስጦታ እንደተቀበልክ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። ዋናው ማድረግ ያለብህ እርሱን እንደ ግል ጌታህ እና አዳኝህ አድርገህ መቀበል ብቻ ነው። ደስ ይበላችሁ!  ክርስቶስ መድኃኒት ተወልዶላቿል!
#ደስብሎኛል

change your profile with #ደስብሎኛል frame
use @add_frame_bot
share with ur friends!

ደስ ያለው ሰው ሼር በማድረግ ይህን የደስታ ምክንያት ለሌሎች እናጋራ!
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube