Get Mystery Box with random crypto!

ደስ ብሎኛል! የሰላም አለቃ ስላለኝ #day_4 ከእግዚአብሔር ጋር በሰላም እንድንኖር ብቸኛው ምክን | Tesfa

ደስ ብሎኛል! የሰላም አለቃ ስላለኝ #day_4
ከእግዚአብሔር ጋር በሰላም እንድንኖር ብቸኛው ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። 
ሰውን ከኃጢአት ባርነት እና ከዘላለም ሞት  የሚያድነው ምንም አይነት መልካም ስራ እንደሌለ እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለሚያውቅ  የእግዚአብሔር ፍፁም በግ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን  ከድንግል ማሪያም እንዲወለድ አደረገ። 
በእርሱም የሚያምኑ ሁሉ በሰላም እንድንኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋን ለብሶ ወደ ምድር መጣ።
"ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፥ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።  ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።  ( ኢሳይያስ 9:6 )
የኢየሱስ ስም በብዙ ተገልጧል። ከዚህም ውስጥ  የሰላም አለቃ  ነው። ሰላም ከሌለ የህይወት ቀጣይነት ሊኖር አይችልም።  የእግዚአብሔር ልጅ የነገሥታት ንጉሥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደፈጠረው ዓለም ስጋን ለብሶ የመጣው ለዚሁ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ሊያደርገን።
ደስ ብሎኛል የሰላም አለቃ ተወልዶልኛል።
#ደስብሎኛል

change your profile with #ደስብሎኛል frame
use @add_frame_bot
share with ur friends!

ደስ ያለው ሰው ሼር በማድረግ ይህን የደስታ ምክንያት ለሌሎች እናጋራ!
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube