2022-07-04 23:54:57
#አማኑኤል_ሆይ - ስለሚወጣው ስለሚገባውም ተመስገንልን
•••
ስምህን ሰምቶ ሞት ይደንግጥ ፤ ቀልያት ይሰንጠቁ ፤ ዲያቤሎስ ይረገጥ አንተ ሳትደክም ሁሉን ትሸከማለክ ፤ ዝም ሳትል ለሁሉ ታስባለክ ፤ ጠላት ግን አንተን መጥፎ አለክ
•••
" #የፍቅር ዓለት ፤ የሕይወት ራስ ፤ የጽድቅ መዝገብ ሆይ " አንተ በነፃ ሥጋህን ቆርሰህ ደምህን አፍሰክ የሁሉን #ኃጢአት ይቅር ትላለክ ፤ ጠላት ግን አንተን ኀጥአ አለክ " የድሆች አባት ፤ የፍትህ ቱንቢ ፤ የእውነት ማማ ሆይ " አንተ በዙፋንክ ለሁሉ በጽድቅ ትፈርዳለክ ፤
ጠላት ግን አንተን ግፈኞች ፍርድ አቆመክ
•••
6666 ግዜ በመንዶል አጥንትክ እስኪታይ እየተቀያየሩ ከበው ፤ #ግፍ_ግፍ_ገረፉክ ፤ ኀያላን ኩሪቤል ቀና ብለው እማያዩትን ውብ ፊትህን 120ግዜ በጭካኔ በድንጋይ #መቱክ ፤ #ተፋብክ #አፌዙብክ ፤ የተመሳቀለ እንጨት አሸከሙክመው 136ግዜ ገፍትረው ከመሬት ጣሉክ ፤ እየጎተቱ ወደ ጎለጎታ ወስደው ከነፍሰ ገዳዮች መሐል ሰቀሉክ #በመንግስተ_ሰማይ የተመላለሱ እግሮች መስቀል ቀኖ ተቸነከሩ ፤ " አዳምን የፈጠሩ ቸር እጆች በመስቀል ቀኖ ተቸነከሩ " " ለአዳም እፍ ብለው ሕይወት የሰጡ መለኮታዊ ከንፈሮች ፤ የዝሆን #ሐሞት ተጋቱ " ወደ
ውኆች መሠረት ሊወርድ ፤ ኀይለኛውን ሊያስር ፤ ምርኮን ከጥልቁ ሊበዘብዝ ፤ ቤተክርስትያኑን በደሙ ሊዋጅ ፤ መሠዊያውንም ሊሰራ ፤ እንደሚታረድ በግ በዝምታ #ጎኑን_በጦር ተወግቶ ሕይወቱን ሰጠ ••• ኦ ክርስቶስ
•••
#አማኑኤል_ሆይ ሙሽራክ ተዋህዶ ትገዛልሀለች ፤ ሕዝብህም ይሰግዱልኻል ፤ ሕይወትህን ቤዛ አርገህ ከሞት ዋጅተኻቸዋልና የአብ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ሥም ከፀሐይ መውጫ ፤ እስከ ፀሐይ መጥለቅያ ፤ ለዘላለም #የተመሰገነ ይሁን
•••
የማይለወጠው ቅዱስ አማኑኤልን ግን ትምህክት አድርገን በኦርቶዶክሳዊነት አምድ እንቆማለን ።
ቅዱስ አማኑኤል አባቴ ሆይ ተመስገንልኝ ••• አማኑኤል ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
•••
https://www.facebook.com/terbinos
683 viewsየእኔ ሀብት, 20:54