Get Mystery Box with random crypto!

❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ terbinos — ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ terbinos — ❤️ የአማኑኤል ልጆች ❤️
የሰርጥ አድራሻ: @terbinos
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.69K
የሰርጥ መግለጫ

« ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል ዘበ ትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ »
••••
« ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ሰሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ
••••
ቻናላችንን ይቀላቀሉ ዘንድ ግብዣችን ነው‼️
-------------------------------------------

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 15:00:33 ቅዱስ መርቆሪዎስ || እኔ ጌታዬን አልክድም
•••
አንሰ ኢይክህዶ ለአግዚአብሔር አምላኪየ / እኔ ጌታዬን አልክድም / ቅዱስ መርቆሬዎስ በንጉሱ ፊት ሳይፈራ ሳያፍር ከተናገራቸው የተወሰደ። “ ሰማዕት ጣዕማ ለዛ ዓለም ወከዓው ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር ወተዐገሱ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት ተሣሃለነ በከመ ዕበየ ሣህልከ ” / ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ። ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ እንደ ይቅርታው ብዛት ይቅር ይበለን። ” አሜን። (ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁጥር ፯)
•••
ቅዱስ መርቆሬዎስ አገሩ ሮም አስሌጥስ ነው። አባት እናቱ አረማውያን ነበሩ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከተወለደ በኋላ መልአኩ የተናገረው ቃል ሁሉ እንደተፈጸመ ሲያውቅ አባቱ ከነ ቤተሰቡ አምነው ተጠምቀዋል። የመርቆሬዎስ ስመ ጥምቀቱ “ ፕሉፖዴር ” ነው ፤ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው። በጥበብ በፈሪሀ እግዚአብሔር አድጎ አባቱ ሲሞት የአባቱን ሹመት ወረሰ።
•••
ንጉሱ ዳኬዎስ ይባላል። መምለኬ ጣዖት ነበር። በርበሮች በጠላትነት ተነስተውበት እንደምን ላድርግ ብሎ የምክር ቃል ሲልክበት መልአኩ በአምሳለ ወሬዛ ቀይህ በሊህ ሰይፍ ይዞ በዚህ ጠላቶችህን ድል ትነሳለህ ደስ ብሎህ በተመለስክ ጊዜ ግን ጌታህ እግዚአብሔርን አስበው ሲለው ታይቶት ነበርና አትፍራ ጌታ ጠላቶቻችንን አሳልፎ ይሰጠናል ብሎት አጽናንቶት ዘመቱ። መርቆሬዎስም ኃይል ተሰጥቶት ጠላቱን ድል ነስቶ ሲመለስ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ወዲያው ኃይል ለሰጡን ለረዱን ለዓማልክቶቼ በዓል አድርጌአለሁና ፈጥነህ ና ብሎ ላከበት። ሄዶ ሹመት ሽልማትህ ላንተ ይሁን “ አንሰ ኢይክህዶ ለአግዚአብሔር አምላኪየ / እኔ ጌታዬን አልክድም / ላቆመው ጣኦት አልሰግድም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ።
•••
በመጨረሻም ህዳር ፳፭ ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ። መርቆሬዎስ ከዕረፍቱም በኋላ ብዙ ተአምራትን አድርጓል ፤ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል ፤ በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት ፤ እኛስ እስመ አልቦ ነገር ዘይሳኣኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን:: ዘኁልቁ 22፡28
•••
የቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕልም በአዎንታ አንገቱን ዘንበል አድርጎ ምስክርነት ሰጥቷል። ይህም ሊታወቅ ዛሬ በሀገራችን በምድረ ተጉለት በስሙ ከታነጸ ቤተ ክርስቲያን ካህናት ደነነ ስዕሉ እያሉ ሲዘምሩ ጎንበስ ቀና ሲሉ እንደሚታይ ይነገራል። የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤቱ በረከቱ አማላጅነቱ ቃል ኪዳኑ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን። እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ ዕለት ዕለት ይከተለኝ። ማቴ.፲፡፴፰-፵
•••
እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። (ዕብ ፲፪፡፩¬-፪)
•••• ════════❁✿❁══════
https://www.facebook.com/terbinos
════════❁✿❁══════
233 viewsየእኔ ሀብት, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:59:05
211 viewsየእኔ ሀብት, 11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:18:10 ለኢትዮጵያ የሚኖርባትን ሳይሆን ፥ እንደ ጻድቁ የሚኖርላትን ሰው፥
ቸሩ መድኃኔዓለም ይስጣት

እንኳን አደረሳችሁ አቡነ ተክለሃይማኖት
•••
አቡነ ተክለሃይማኖት ምድራዊ ሕይወታቸውን በተጋድሎና በሐዋርያዊ አገልግሎት ከፈጸሙ በኋላ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ የሚያልፉበት ቀን ተቃረበ፡፡ በዚህ ጊዜ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ከቅዱሳን መላእክት ፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ከቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ወደ እርሳቸው በመምጣት የሚያርፉበት ዕለት መድረሱን ነገራቸው፡፡
•••
የተጋድሏቸውን ጽናት አድንቆ በስማቸው መታሰቢያ ለሚያደርጉ፣ ለነዳያን ለሚመጸዉቱ ቤተ ክርስቲያን ለሚያሠሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ስለ ተጋድሏቸው ጽናትም ‹‹ በሰው እጅ የማይለካውን ይህንን የመንግሥት አዳራሽ ውሰድ ›› በማለት የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያለው የጸጋ ልብስ አልብሷቸዋል፤ በመስቀል ምልክት ያጌጡ ሰባት የሕይወት አክሊላትንም አቀዳጅቷቸዋል፡፡
•••
ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ጊዜ መቃረቡን ባወቁ ጊዜ የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ሁሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ ፳፬ ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም ለአንድ ቅዱስ አባትና ካህን በሚገባ ሥርዓት በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀብረዋቸዋል፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችንና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ተገልጾላቸዋል፤ ነፍሳቸውንም ‹‹ የጠራሽ ፣ ንጽሕት ነፍስ ሆይ ወደ እኔ ነዪ ›› ብሎ በክብር ተቀብሏታል፡፡
•••
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህ ዓለም የኖሩበት ዕድሜ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከዐሥር ወር ከዐሥር ቀን ነው፡፡ በእናት አባታቸው ቤት ፳፪ ዓመት፤ በከተታ ፫ ዓመት፤ በይፋት ፱ ወር ፤ በዳሞት ፲፪ ዓመት ፤ በአማራ ፲ ዓመት፤ በሐይቅ ፲ ዓመት ፤ በደብረ ዳሞ ፲፪ ዓመት ፤ በትግራይና በኢየሩሳሌም ገዳማት ፩ ዓመት ፤ ዳዳ በሚባል አገር ፩ ወር ፤ በደብረ አስቦ ገዳም ፳፱ ዓመት ከ፲ ቀን መቆየታቸውን መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል (ገ.ተ.ሃ ፶፱፥፲፬-፲፭)፡፡
•••
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸውን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት ፣ እንደ በሬ ተጠምደው ፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው ይህንን ዓለም ንቀው ፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው ባሻገር እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ ፤ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት ፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያችንም ነሐሴ ፳፬ ቀን የዕረፍታቸውን በዓል በትላቅ ደስታ ታከብራለች ፤ የጻድቁ በረከት አይለየን፡፡
•••
ምንጭ፡-መጽሐፈ ስንክሳር፣ ነሐሴ ፳፬
ገድለ ተክለ ሃይማኖት
•••
════════❁✿❁══════
https://www.facebook.com/terbinos
════════❁✿❁══════
366 viewsየእኔ ሀብት, 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:13:43
314 viewsየእኔ ሀብት, 15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:18:26 ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ ነው

ሼር በማድረግ የቅዱሳንን ክብር
እንመስክር
•••
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከክርስቲያን ቤተሰብ የተገኘ ወጣት ነው። በሕይወት ዘመኑ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ ፣ የወጣትነት ዘመኑን እግዚአብሔር እንዲከብርበት በቅድስና የኖረ ፣ ከባድ የሰማዕትነትን ተጋድሎ በጽናት የፈጸመ ታማኝ የክርስቶስ ጃንደረባ ነው።
•••
ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍቅርን ፣ ትህትናን ፣ ሰብአዊ ርኅራኄንና በጎነትን ወላጅ እናቱ ከቅዱሳት መጻሕፍት በሚገባ ታስተምረው ስለነበር ለሰዎች ሁሉ እጅግ መልካምና ቀና አሳቢ ወጣት ሆኖ አደገ። የነበረውን መልካም ባህሪና በጎ አስተሳሰብ ተመልክተውም በሀገሩ ላይ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂነት አድርገው ለሹመት እንዳበቁት የወጣትነት ዘመን ታሪኩ በሰፊው ይገልጻል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ገና በወጣትነቱ የክርስቶስ ፍቅር በልቡ የተሳለበት ፣ የመስቀሉ ውለታ በኅሊናው የታተመበት ጠንካራ ክርስቲያን ነበር። በዚህ ዘመን በዘር ፣ በብሔር ተከፋፍለን በዓለም ርኩሰት ውስጥ ለወደቅን ወጣቶች ብዙ ቁም ነገር ሕይወቱ ያስተምረናልና ጽሑፋን በጥንቃቄ እናንብ።
•••
ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥንትዋ ካፓዶቂያ በአሁኗ ቱርክ በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከክርስቲያን ቤተሰቦች ተወለደ።አባቱ በሞት ሲያልፍ እናቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዛ ወደ ትውልድ ሀገሯ ወደ ፍልስጠኤም ምድር ተመለሰች። ጊዮርጊስም በዚያው አደገ ኋላም የሮም ወታደር ሆኖ ሳለ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂነት ማዕረግ ተሾመ። በወቅቱ የሮም ግዛት ንጉሥ የነበረው ዲዮቅልጢያኖስ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ከፍተኛ ዘመቻ ጀመረ። በ303 ዓ.ም ቅዱስ ጊዮርጊስ ንጉሡ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጽመውን ማሳደድ እንዲያቆም አጥብቆ ይቃወመ ስለነበር የነበረውን ስልጣን በተቃውሞ ለቀቀ።
•••
እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ንጉሡ ሮም ታስተዳድራቸው በነበሩ ሀገራት ሁሉ ላይ ክርስቲያኖችን ያስጨንቅ ያነበረው ጣዖት አምላኪ በመሆኑ ነው። በግዛቱ ላይ ታላቅ አምባገነናዊ አዋጅ አውጆም ነበር « አብያተ ክርስቲያን ይትሃጸዋ አብያተ ጣዖታት ይትርሃዋ » « አብያተ ክርስቲያናት ይዘጉ አብያታ ጣዖታት ይከፈቱ » የሚል መመሪያ በየሀገሩ አስተላለፈ ይህንን የተቃወሙ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወታደሮች ይዘው በግፍ እያሰቃዩ እንዲገድሏቸው ፣ ሰውነታቸውን ሰም እየለቀለቁ በአደባባይ እንደ ጧፍ እንዲያቀልጧቸው ፣ ከአንበሶች ጋር እያታገሉ ሰባብረው እንዲበሏቸው ያደርግ ነበርና ቅዱስ ጊዮርጊስ ይህንን ክፉ የአጋንንት ሥራ አጥብቆ ተቃወመ።
•••
ክርስቲያኖች ልብ በሉ ክርስትና እኛ ዘመን የደረሰው አልጋ በአልጋ ሆኖ አይደለም በብዙ መከራና ስቃይ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዋጋ እየተከፈለበት ነው። የክርስቶስን ጌትነትና አዳኝነት ሳይፈሩና ሳያፍሩ በነገሥታትና በአሕዛብ ፊት ወንጌልን በሰበኩ እውነተኛ አማኞች ታላቅ ተጋድሎ ዛሬ በክብር የምንጠራበት ክርስትና የጨለማውን ዘመን በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ሥልጣን ተሻግሮ በብርሃን ሰረገላ የክብሩን ወንጌል ለእኛ አድርሷል። የቀደሙ ክርስቲያኖች ወንጌልን በአፍ ብቻ ሳይሆን በሕይወታቸው የኖሩ፣ በደሙ የዋጃቸውን ጌታ በደማቸው ያከበሩ ታላቅ የእምነት አርበኞች ናቸው።
•••
ቅዱስ ጊዮርጊስ በክርስቲያኖች ላይ የወጣውን የንጉሡን ትህዛዝ ቀዶ ስለጣለው ይህ ድርጊት ንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ አጅግ አናደደው ጊዮርጊስ እስር ቤት ውስጥ እንዲጣልና በዚያም ከፍተኛ ስቃይ እንዲፈጸምበት አደረገ ፤ ሰማዕቱ ግን እምነቱን ፈጽሞ አልካደም። በታሪክ እንደተመዘገበው ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አሰቃቂና አስከፊ በሆነ መንገድ በርካታ ስቃዮችን ተቀብሏል። መርዝ እንዲጠጣ አስገድደውታል ፣ ሁለት የሾለ ብረት ባለው መንኮራኩር መሐል አስገብተው ሰባብረውታል ፣ በትልቅ ድስት ውስጥ የቀለጠ ብረት አፍልተው ጊዮርጊስን እዛ ውስጥ ጨምረው አሰቃይተውታል። ሰማዕቱን ለመግደል ያልሞከሩት ሙከራ አልነበረም ፤ ነገር ግን በድንቅ ተአምር ሌሊት ቁስሉን ክርስቶስ ራሱ ይፈውሰው ነበር። ሰማዕቱ ለጣዖት መስዋዕት እንዲያቀርብ በንጉሡ በተገደደ ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ለሮም ጣዖታት መስዋዕትን ከማቀረብ ይልቅ ሕይወቴ ቢያልፍ እመርጣለሁ ብሎ ተናገረ። ሕዝቡም በእርሱ ላይ የሚሆነውን ለማየት ተሰብስበው ሲመለከቱ ፤ጊዮርጊስ ግን የክርስቲያኖች አምላክ ወደ ሚሆን ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር። እየጸለየም ሳለ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወደቀ ፣ ታላቅ የምድር መናወጥም ሆነ ፣ የጣዖት ካህናቱ ፣ ጣዖታቱና የጣዖታቱ መቅደሶቹ ሁሉ ወደሙ። ሆኖም እግዚአብሔር ሰማዕቱ ከዚህ በላይ እንዲሰቃይ አልፈለገምና ስለ እምነቱ ጽናት በሰማዕትነት ክብር እንዲያልፍ ሆነ።
•••
በመጨረሻም ቅዱስ ጊዮርጊስን በዛሬዋ ልዳ ከተማ ጎዳና ላይ እየጎተቱ ወስደው እስዛው በፍልስጠኤም ምድር አንገቱን ሰየፉት። የንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ሚስት ግን በቅዱስ ጊዮርጊስ የእምነት ጽናት ውስጥዋ እጅግ ተማርኮ ነበርና እርሷዋም በመጨረሻ ክርስቲያን ሆነች። ስለ ክርስትናዋም ብዙ መልካም ተግባራትን ትፈጽም ነበር። ወገኖቼ በጣም እናስተውል ሰው ወንጌል ሲገባው ቅዱሳንን ያከብራል፣ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዋጋ ከፍለው በሰማዕትነት ያለፉ የእምነት ጀግኖችን እያሰበ ሕይወታቸውን አብነት አድርጎ ይጓዛል፣ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ « የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የእምነታቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሏቸው ያለው። » ዕብ 13፥7
•••
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰማዕታትን የተጋድሎ ሕይወትና ወንጌልን በሕይወታቸው እንዴት እንደተረጎሙ ትውልዱ በየጊዜው እያሰበ እንዲኖር ቀናት በቅዱሳን ስም ሰይማ ተጋድሎና ታሪካቸውን ስታስተምር መኖሯ ከትክክል በላይ ትክክል ነው። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እግዚአብሔር ሁሌም በክብር ይጠብቅሽ። ዛሬ አንዳንድ ሰዎች ወንጌል ገብቶናል ፣ እውነት በርቶልናል እያሉ ቅዱሳንን ሲያቃልሉና ሰማዕታትን ሲያብጠለጥሉ ይውላሉ ፤ ነገርግን ስለ ክርስትና አንዲትም መከራ በሕይወታቸው አልተቀበሉም። በግል በሥጋ ድካማቸው የሚመጣባቸውን መከራ ስለ እምነታቸው እንደተቀበሉት አድርገው ይጠመዝዙታል ይሄ በጣም ስህተት ነው። እውነት ወንጌል የበራላችሁ ከሆነ እስቲ እስላም መስኪድ ሄዳችሁ ስበኩ ፣ እስቲ ጠንቋይ ቤት ያሉትን የማምለኪያ መሰዊያዎች ሄዳችሁ አፍርሱ ፣ ፌስቡክ ላይ ተጥደው እየዋሉ ቅዱሳንና ሰማዕታትን የሚነቅፉ ፣ የቤተክርስቲያንን ክብር ለማዋረድ የሚወራጩ ሰዎች መንፈሰ እግዚአብሔር የተለያቸው የአጋንንት መንፈስ በልባቸው ሰልጥኖ ምላሳቸውን የተከራያቸው የጥፋት ልጆች ናቸው እግዚአብሔር ልባቸውን ይፈውስ።
•••
ወገኖቼ የክርስቶስ ፍቅር ሲገባን እንደነ ቅዱስ ጊዮርጊስ እሳትና ስለቱን ሳንፈራ ስለ ወንጌል እንመሰክራለን ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የአማልክት አምላክ ፣ የጌቶች ጌታ ፣ የነገሥታት ንጉሥ መሆኑን ሳንፈራና ሳናፍር እንመሰክራለን። የሰማዕታት ደም የእምነት ዘር ነው ጥቂት ፈሶ ብዙ ምርኮን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ያስገባል።
•••
የሰማዕቱ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን
•••
" ... ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የፃድቅን ዋጋ ይወስዳል ማንም ከነዚህ ታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀ መዛሙርቱ ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም ... " ( ማቴ.10፥41 )
•••
404 viewsየእኔ ሀብት, 16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:15:50
337 viewsየእኔ ሀብት, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:51:52
ከሳሶቼ ቢጠነክሩ
የኔ መውደቅ ቢጠባበቁ
ሰማእቱ አለ ከኔጋ
ጋሻየ ነው ሲመሺ ሲነጋ

•••
ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥኖ ደራሽ በመከራ ጊዜ ፈጥኖ ይድረስልን አጥንታችንን ለመፍጨት ደማችንን ለማፍሰስ የተነሱትን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያፍዝዝልን ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን አሜን!
••••• ════════❁✿❁══════
https://www.facebook.com/terbinos
════════❁✿❁══════
414 viewsየእኔ ሀብት, edited  06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 16:22:44
«... ይህ #ጦርነት እንዲቆም #እማጸናለሁ! »
•••
"...ከእናንተ የምመኘውን ልንገራችሁ። ሀገራችን ከዚህ የደረሰችው ብዙ ኢትዮጵያውያን ፣ ኢትዮጵያዊያት ሕይወታቸውን ጭምር ሰጥተው ፣ መስዋእት አድርገው ነው። አንድነቷ ተከብሮ ፣ በነጻነቷ ደምቃ ለአፍሪካውያን የኩራት ፣ የክብር ተምሳሌት ሆና አገራችን የቆየችው በዚህ መንገድ ነው።
•••
አልተማሩም ያልናቸው ወገኖቻችን በዚህ መልኩ ያቆዩዋትን ሀገራችንን ተማርን ያሉ ሰዎች በየቀኑ የመለያየት ፈጠራ ፣ የማፍረስ ፈጠራ እየፈጠሩ ወገንን ከወገን ሲለያዩ የተገነባውን ሲያፈርሱ እየተመለከታችሁ ፤ እየተመለከትን ነው። ስለዚህ እናንተ የጥፋት ተቃራኒውን የሆነውን ልማትን እንድታለሙ ፣ ራሳችሁን እረድታችሁ ሀገራችሁን እንድትረዱ ይልቁንም አንድ የሆነችው ሀገራችሁ ፤ አንድ የሆነ ህዝባችሁ በአንድነቱ እንዲቀጥል ፣ ደካሞች ያፈረሷትን ሀገራችሁን እናንተ እንድትገነቡ ልታስቡ ፣ በዚህ ልክ 'ምን ላድርግ? ምን ልስራ?' ብላችሁ ፈጠራ ልትፈጥሩ ይገባል ብዬ እጠብቃለሁ። "
•••
"... ይሄ ጦርነት እንዲቆም እማጸናለሁ። ለማንም ሲበጅ አላየሁም።
•••
በዚያ ክፉ ሰዓት በጦርነቱ መካከል ነበርኩኝ። ከግራ ቀኝ ሲያተርፍ ማንንም አልተመለከትኩም። ሲከስር ሲያጣ ነውና። አሁን ደግሞ ይህ በመሆኑ በእውነት ልንቆጭ ይገባል። ክፉ አስበው ክፉ ለሚሰሩ ሰዎች አምላካችን እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው እላለሁ። አምላካችን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ይጠብቅልን። አሜን። "
ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም
•••
ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ የተበረከተላቸውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ መነሻ አድርገው ለባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ካስተላለፉት መልእክት)
••••
════════❁✿❁══════
https://www.facebook.com/terbinos
════════❁✿❁══════
453 viewsየእኔ ሀብት, edited  13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 10:40:55
#ማኅበረ_ቅዱሳን
•••
በ2013 እና 2014 ዓ.ም በማኅበራዊ ድጋፍ ከተከናወኑ ተግባራት ውስጥ 17.9 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ተደርጎል
•••
ለተፈናቀሉ ምእመናን ፣
ካህናት ፣ የአብነት ት/ቤቶችና
ለገዳማት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
•••
በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ክስተቶች ምክንያት ለችግር ለተጋለጡና ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ በአማራ ፣ በኦሮሚያ ፣ በትግራይና ቤንሻንጉል ጉሙዝ መተከልና አካባቢው ለሚገኙ ምእመናን ፣ ካህናት ፣ የአብነት ት/ቤቶችና ገዳማት ባለፉት 2 ዓመታት የተለያዩ ማኅበራዊ ድጋፎች ተደርገዋል፡፡
•••
በተጨማሪም በሙያ አገልግሎት ዘርፍ ሙያዊ ግምታቸው 29.33 ሚሊዮን ብር የሚሆኑ 85 ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸው ዲዛይኖች በነጻ ተሠርተው ለጠየቁ የቤተ ክርስቲያን አካላት ተሰጥተዋል።
•••
እንዲሁም ሙያዊ ግምታቸው 1.5 ሚሊዮን የሆኑ ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ልማት ፕሮጀክቶች ተሠርተው ለጠየቁ አካላት በነጻ ተሰጠተዋል።
•••
ምንጭ:- #ማህበረቅዱሳን
•••
════════❁✿❁══════
https://www.facebook.com/terbinos
════════❁✿❁══════
442 viewsየእኔ ሀብት, edited  07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:30:34
እምነት ባህርን ከፍሎ ያሻግራል ፣ በበረሃ መካከል ከሚገኝ ዓለም ውሃ አፍልቆ ያጠጣል። ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል የሚለው።
•••
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ከሰንበት ረድኤት በርከት ያሳትፈን እግዚአብሔር አምላካችን አሜን ከመቅደሱ ረድኤት በረከትን ይላክልን
••• ════════❁✿❁══════
https://www.facebook.com/terbinos
════════❁✿❁══════
437 viewsየእኔ ሀብት, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ