Get Mystery Box with random crypto!

#ማጠቃለያ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሲጠናቀቅ ከመርሐ ግብሩ መገባደድ አስቀድሞ | Tengert Sport

#ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሲጠናቀቅ ከመርሐ ግብሩ መገባደድ አስቀድሞ አስተያየቶች ተሰጥተዋል ።

የኢፌዴሪ ባህል እና ስፖርት ሚንስትሩ ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ " እጩ የነበሩ ተፎካካሪዎች ለተመረጠው ፕሬዝዳንት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ እጠብቃለሁ " ብለዋል።

አያይዘውም " ኩርፊያ እንደማይኖር አውቃለሁ በሰለጠነ ዘመን ምርጫው ሰላማዊ በመሆኑ ደስተኛ ነን ፣ ጉባኤ ማድረግ ቀላል አይደለም ከባድ ነው ውጤት ያመጣ ይደገፋል ይበረታታል " ብለዋል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በሰጡት የመዝጊያ ንግግር " አምናችሁ ይሰራሉ ብላችሁ ሀላፊነት ስለጣችሁን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።

ምርጫ በደረሰ ቁጥር የሚነሳን ግሪሳ ሳትሰሙ ለምንም ሳትመኩ ይህን በማድረጋችሁ አመሰግናለሁ ነፃም ስለወጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።

የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያን ኢንፋንቲኖ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ለፕሬዝዳንቱ ሲያስተላልፉ በቀጣይ ፌዴሬሽኑን በተቻለ መጠን እንደሚያግዙ ቃል ገብተዋል።

ከመርሐ ግብሩ መጠናቀቅ አስቀድሞ በስፋራው የነበሩ የካፍ እና ፊፋ ታዛቢዎች ለአቶ ኢሳያስ ጅራ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

@tengertsport    
@kidusyoftahe
@ቤቢ የአማኑኤል ልጅ