2021-02-19 15:28:41
#Attention
በ5 ክልሎችና በ2 የከተማ አስተዳድሮች ኤችአይቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌዴራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ።
በጋምቤላ፣አማራ፣ ሀረሪ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በላይ በመሆኑ በወረርሽኝ ደረጃ እንደሚገኙ የፌዴራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ማሳወቁን etv ዘግቧል።
በሀገር ደረጃ የኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ከፍተኛ የስርጭት መጠን ያለባቸው ፦
- ጋምቤላ 4.6 በመቶ
- አዲስ አበባ 3.4 በመቶ
- ድሬዳዋ 2.5 በመቶ
- ሀረሪ 2.4 በመቶ
- አፋር 1.4 በመቶ
- ትግራይ 1.2 በመቶ
- አማራ 1.2 በመቶ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
በWHO መረጃ ከሆነ አንድ በሽታ ወረርሽኝ ነው የሚባለው የስርጭት ምጣኔው 1 በመቶ እና ከዚያ በላይ ሲሆን፣ እንደ ሀገር የኤች አይ ቪ/ኤድስ የስርጭት መጠን 0.93 በመቶ ስለሆነ በወረርሽኝ ደረጃ አይደለንም ተብሏል።
በማህበረሰብ ደረጃ ከፍተኛ የስርጭት ምጣኔ የሚታይባቸው ሴተኛ አዳሪዎች ሲሆን ቁጥሩ 23 በመቶ ነው ተብሏል።
በመቀጠልም፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ ሴቶች ላይ 19 በመቶ ሆኖ ይታያል።
የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ ኮንስትራክሽን ሳይት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች፣ አፍላ ወጣቶች ላይ ከ2 በመቶ በላይ የስርጭት ምጣኔ ያሳያል።
በከተማ ያለው የስርጭት ምጣኔ 3 በመቶ ሲሆን በገጠር ያለው ደግሞ 0.4 ደርሷል ተብሏል።
በተጨማሪ በወንዶች ያለው የስርጭት ምጣኔ ከሴቶች ይልቅ ዝቅ ብሎ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የHIV የስርጭት ምጣኔ 61 በመቶ የሚሸፍኑት ሴቶች ሲሆኑ ፣ 39 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍኑት ወንዶች እንደሆኑ ተገልጿል። (ኢብኮ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
1.1K viewsSO ዘውዱ, 12:28