Get Mystery Box with random crypto!

31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ህዳር 8 /2015ዓም ይጀመራል። ህዳር 8/2015 ዓም . | ትምህርት በቤቴ🔝

31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ህዳር 8 /2015ዓም ይጀመራል።

ህዳር 8/2015 ዓም . የከፍተኛ እና አጠቃላይ ዘርፎች እቅድ ፣ አፈጻጸምና የየዘርፎቹን ዝርዝር ተግባራት ከየዘርፎቹ ተጠሪ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት ጋር በተመሣሣይ ጊዜ የሚከናወን ልዩ መርሃ ግብር የሚካሄድ መሆኑንና ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤው ህዳር ዘጠኝ ሁለቱም ዘርፎች እና ባለድርሻ አካላት በጋራ በተገኙበት የሚካሄድ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ተመላክቷል።

በጉባኤው የአጠቃላይ ትምህርት እና የከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የለውጥ ስራዎችና ሌሎችም ተዛማጅ የትምህርት ጉዳዮችም ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።

የክልል ትምህርት ቢሮዎች አፈጻጸም ሪፖርት እና የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ እቅድ ፣ የምርምር ተቋማትና ሌሎችም ዓመታዊ ክንውኖችም እንዲሁም የትምህርት ዘርፍን የወደፊት አቅጣጫ አመላካች ጥናታዊ ጽሁፎች እና የትምህርት አጋር ድርጅቶች ሞሽን በጉባዔው እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

በአገራዊ የትምህርት ዘርፍ አፈጻጸሞችና የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ የሚመክረው ጉባዔ መፍትሄዎችን በማመላከትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ ቅዳሜ ይጠናቀቃል ።

በጉባዔው ላይ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ዘርፍ ኃላፊዎችና የትምህርት ስራ ባለድርሻዎችን ጨምሮ 400 በላይ እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete