Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት እስከ ሦሥት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን | ትምህርት በቤቴ🔝

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት እስከ ሦሥት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ገለጹ።

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሦሥት ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ራስ ገዝ ሆኖ ከመንግስት ዩኒቨርሲቲ ምድብ ይወጣል ብለዋል።

"አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ተከትሎ ባህር ዳር፣ ሀራማያ፣ ጅማ፣ መቐለ፣ ሀዋሳ ... የመሳሰሉት ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች በፍጥነት ከመንግስት በጀት ወጥተው ራስ ገዝ (Autonomous) መሆን አለባቸው" ብለዋል።

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት 10 ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ መንግስት አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete