Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈቺ ዌብ ሳይት ያበለጸጉ ተማሪዎችን ሸልሟል። ዩኒቨርሲቲው ወደተለ | ትምህርት በቤቴ🔝

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈቺ ዌብ ሳይት ያበለጸጉ ተማሪዎችን ሸልሟል።

ዩኒቨርሲቲው ወደተለያዩ የ Google Company ሀገራት ለሥራ እና ለ Internship ለሚሄዱ ተማሪዎች የገንዘብ እና የሽኝት መረሃ ግብር አካሂዷል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የአፍሪካ ሲልከን ቫሊ በተሰኘ ኩባንያ ትብብር የተዘጋጀ ቴክኖሎጂን የማበልጸግ ውድድር ተካሂዷል።

የህክምና አገልግሎት መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል፣ የኦንላይን ላይብረሪ አጠቃቀም የሚያበልጽግ፣ የተሻለ ምግብን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል እና ሌሎች ችግር ፊቺ ቴክኖሎጂዎች  በውደድሩ ላይ ቀርበዋል።

የተሻለ የህክምና አገልግሎት መረጃ የሚገኝበት ቴክኖሎጂ ያበለጸጉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በውድድሩ ያሸነፉ ሲሆን የ8 ሺህ ዶላር ሽልማት አግኝተዋል።

ሁለተኛ የወጡት ተሸላሚዎች የ4 ሺህ ዶላር ሽልማት ያገኙ ሲሆን ሌሎችም የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነዋል።

ተወዳዳሪዎቹ ላለፉት ሦሥት ወራት ዓለም ዓቀፍ እውቀቶችን የሚያገኙበትን ስልጠና ማግኘታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።

ተማሪዎች የቴክኖሎጂ ዕውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ከዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ጋር የማገናኘት ሥራውን ዩኒቨርሲቲው እንደሚያጠናክር የተቋሙ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ገልጸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete