Get Mystery Box with random crypto!

#መስከረም_9 በአዲስ አበባ መስከረም 9 የመማር ማስተማር ስራ ይጀምራል! በአዲስ አበባ ከተማ | ትምህርት በቤቴ🔝

#መስከረም_9

በአዲስ አበባ መስከረም 9 የመማር ማስተማር ስራ ይጀምራል!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ በሁሉም ትምህርት ቤቶች መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ስራ እንደሚጀመር ተገለጸ።የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ ከመጀመራቸው በፊት የቅድም ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ ቆይቷል።በዚህም የትምህርት ቤቶች እድሳት፣ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የመጻሕፍት ማስተዋወቅ እና የትምህርት ጉባዔ የማካሄድ ስራ ይከናወናል ብለዋል።

ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ እና ሳቢ እንዲሆኑ ለማድረግ ከጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የዕድሳት እና የጽዳት መርሐ-ግብር እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።ትምህርት ቤቶችን የማሳመር ስራ ሲጠናቀቅ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም የመማር ማስተማር ስራው ይጀመራል ነው ያሉት።

እንደኃላፊው ገለጻ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሌሎች የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚደግፉ ሥራዎች ይሰራሉ።በዚህም መሰረት ከመስከረም 2 ቀን እስከ 6 2015 ዓ.ም ድረስ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የተዘጋጁ መጽሓፍትን የማስተዋወቅ ስራ ይሰራል ብለዋል።በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለመምህራን እና ተማሪዎች የትውውቅ ፕሮግራም እንደሚያካሂዱም ጠቁመዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete