Get Mystery Box with random crypto!

በልጅነት ፍሎራይድ የበዛበትን ውሃ መጠቀም የጥርስ ቀለምን ወደ ቢጫ እንዲቀየር እና እንዲበልዝ ያደ | ትምህርት በቤቴ🔝

በልጅነት ፍሎራይድ የበዛበትን ውሃ መጠቀም የጥርስ ቀለምን ወደ ቢጫ እንዲቀየር እና እንዲበልዝ ያደርጋል።

ይህ ሁኔታም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ያጋጥማል። ፍሎራይድ የጥርስን የላይኛውን ክፍል በመጉዳት ቀለሙ እንዲቀየር እና እንዲሸራረፍ ምክንያት ይሆናል።

በዚህም ሳቢያ በርካታ ሰዎች በጥርሳቸው ቀለም እፍረት እና መገለል ይገጥማቸዋል። የወደፊት ዕቅዳቸው ተሰናክሎብናል የሚሉም አሉ።

የታንዛኒያዋ አሩሻ በውሃ ውስጥ ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ካለባቸው ስፍራዎች መካከል አንዷ ስትሆን፣ እዚያ የአሩሻ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ወጣት ሴቶች ስለገጠማቸው ችግር ይናገራሉ።

ሁለቱ ወጣቶች በጥርሳቸው ቀለም መቀየር ምክንያት መድሎ እንደሚደርስባቸው ገልጸዋል። መፍትሔ ይኖረው ይሆን

የጥርስን ቀለም የሚቀይረውን ከፍተኛ የፍሎራይድ መጠን ያለውን ውሃ ማጣራት እጅግ ከባድና ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ነው። አሁን ግን ቀላል የውሃ ጣሪያ ዘዴ ተፈጥሯል።

መረጃው የ BBC ነው
https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete