ፍሬሽ ተማሪዎች እንዴት አሳይመንት መስራት አለባቸው? ፍሬሽ ተማሪዎች ብዙ ጊዜ የአሳይመንት አ | ትምህርት በቤቴ🔝

ፍሬሽ ተማሪዎች እንዴት አሳይመንት መስራት አለባቸው?

ፍሬሽ ተማሪዎች ብዙ ጊዜ የአሳይመንት አሰራር ላይ የሚያደርጉት ትንንሽ ስህተት ብዙ ማርክ ያሳጣቸዋል። ይህንን ታሳቢ በማድረግ ይህንን መመሪያ አዘጋጅተንላችኋል።

1) የሕዳግ መስመር አስምሩ።

እያንዳንዱ ወረቀት ላይ (Cover page ጨምሮ) ከግራ በኩል 20 mm, ከላይ፣ ከታችና ከቀኝ ጠርዞች ደግሞ 5 mm አስምሩ። ለማሳመር ብላችሁ ሌላ የስዕል ስራ እንዳትሰሩ። መስመሮቹ ብቻ በቂ ናቸው።

ስትፅፉ በፍፁም ከመስመሮቹ እንዳትወጡ። ሁሉንም ፅሁፍ መስመሩ ውስጥ አድርጉ።

2) ፅሁፋችሁን ተነባቢ አድርጉ።

የፊደል አጣጣላችሁን አሪፍ ለማድረግ ሞክሩ። የተለያየ አይነት የፊደል አጣጣል ቢኖርም ለብዙዎች ተነባቢ የሚባለው የፊደል አጣጣል "Case Letter Handwriting" ይባላል። Google ላይ ምርጥ sample ስለሚኖር እሱን እያያችሁ ለመፃፍ ሞክሩ።

3) ከቻላችሁ በኮምፒውተር ፃፉ።

የዚህ ዘዴ ጠንካራ ጎኑ በኮምፒውተር ስለሚፃፍ ምርጥ ፅሁፍ ስለሚሆንና ለማስተካከል በጣም አመቺ ስለሆነ ነው። ነገር ግን ኮምፒውተር ካላገኛችሁ፣ ፈጠን ብላችሁ መፃፍ ካልቻላችሁ እና Calculation ያለው አሳይመንት የምትሰሩ ከሆነ በእጃችሁ መፃፍ ሊኖርባችሁ ይችላል።

ለማንኛውም የመምህራችሁን (ማለቴ "የዶክተሩን") ባህሪ እና የአሳይመንቱን አይነት ካወቃችሁ በኋላ በኮምፒውተር ብትሰሩ አሪፍ ነው።

4) አሳይመንት በጊዜ ጀምሩ።

አሳይመንት በተቻላችሁ መጠን ከማስገቢያው ጊዜ ቀደም ብላችሁ መጨረስ አለባችሁ። የሚገጥማችሁ ነገር አይታወቅም። ህመም ሊኖር ይችላል፣ የሌሎች የትምህርት አይነቶች አሳይመንት ሊደረብባችሁ ይችላል፣ እንደውም መሃል ላይ ፈተና ራሱ ሊኖር ይችላል። ስለዚህ በተቻላችሁ መጠን በፍጥነትና በጥራት ለመጨረስ ሞክሩ።

5) ቀላል የቋንቋ አገላለፅ ተጠቀሙ።

#አንዳንድ የግቢ መምህራን የእንግሊዘኛ ቋንቋ አቅማቸው በጣም የወረደ ነው፣ በቃ ይሄ እውነታው ነው። ክፍል ውስጥ በሚያስረዱበት አገላለፅ የእንግሊዘኛ ቋንቋ አቅማቸውን በቀላሉ መገመት ይቻላል። ስለዚህ እናንተም ቀላል ቋንቋ እና አገላለፅ ተጠቀሙ፣ አለበለዚያ ይነስራቸዋል።

6) Bulleting and Numbering

እነዚህ ሁለት ነገሮች በጣም አስፈላጊ ናቸው። Bulleting ማለት በሰረዝ፣ በኮኮብ ወይም በሌላ ምልክት ዝርዝር ሀሳቦችን የማቅረቢያ ዘዴ ነው። Numbering ደግሞ ቁጥሮችን በመጠቀም ተመሳሳይ ነገር ማደረግ ነው።

እነዚህን ለዝርዝር ሀሳቦች ስትጠቀሙ አሳይመንታችሁን ይበልጥ ተነባቢ ያደርገዋል፣ ማርክም ያሰጣችኋል።

7) ቀይ እስክርቢቶ በፍፁም እንዳትጠቀሙ።

ይሄ በቃ ክልክል ነው። Don't do it!

8) ጥያቄ እና መልስ ምንጊዜም አንድ ላይ አድርጉ።

"ጥያቄ መጀመሪያ ፅፌ ከዚያ መልሱን እሰራለሁ" ክልክል ነው። ጥያቄውን ከፃፋችሁ በኋላ መልሱን ከስሩ በግልፅ ማስፈር ይኖርባችኋል።

9) በፍፁም እንዳትኮርጁ!

በቃ ይቅርባችሁ፣ ለጊዜውም ቢሆን አይጠቅማችሁም። የግቢ መምህራን ይህንን ካወቁ ኮራጁም አስኮራጁም ዜሮ ይሰጧችኋል። እደግመዋለሁ በፍፁም እንዳትኮርጁ! ቢያንስ በራሳችሁ አገላለፅ ፃፉ።

የሌላ ሰው አሳይመንትም እንዳትፅፉ። አንድ አይነት እጅ ፅሁፍ ሲያዩ ዜሮ የሚሰጡ መምህራን አሉ። ተጠንቀቁ!

ቀሰም Academy

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete
ትምህርት በቤቴ🔝

ትምህርት በቤቴ🔝

@temhert_bebete
1.20K ተመዝጋቢዎች
ትምህርት ምድብ
A channel created for sharing . 🔺study tips,. 🔺short notes,. 🔺tutorials,. 🔺educational news,. 🔺life tips and some motivational quotes ... For com...