Get Mystery Box with random crypto!

#10_መረዳት_ያለብህ_እውነቶች #አንድ- ደሞዝ ማለት ህልምህን እንዳትኖረው ቀጣሪዎችህ የሚሰጡህ | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

#10_መረዳት_ያለብህ_እውነቶች

#አንድ- ደሞዝ ማለት ህልምህን እንዳትኖረው ቀጣሪዎችህ የሚሰጡህ አደንዛዥ እጽ ማለት ነው።

#ሁለት- ነገሮችን ለመጀመር ጥሩ ጊዜ የምትጠብቅ ከሆነ፣ ሙሉ ህይወትህን ታባክናለህ እንጂ ምንም የሚፈጠር አዲስ ነገር አይኖርም። ምክንያቱም ትክክለኛው ጊዜ አሁን ስለሆነ።

#ሶስት- ምንም ያህል ቅርብ የምትላቸው ጓደኞችህን እና ቤተሰቦችህን ብታምናቸው እንኳ፣ ስላንተ ሁሉን ነገር እንዲያውቁ አታድርግ።

#አራት- ሙሉ ለሙሉ የቅርብ ጓደኞችህን የምታጣው ያኔ ነው... ራስህን መለወጥ ስትጀምር!

#አምስት- አስር እጥፍ ደስተኛ መሆን ከፈለግክ ይቅር ባይ ሁን እና ለችግርህ ማንንም ተወቃሽ ማድረግ አቁም።

#ስድስት- በሳል ሰው የምትሆነው ራስህን መምራት ስትጀምር ነው።

#ሰባት- ራስህን እንዴት እንደምትቀይር የሚያስተምሩ መቶ መጽሐፎች አያስፈልጉህም። የሚያስፈልግህ ተግባራዊ መሆን እና በራስህ የምትከተለው ስነ-ስርአት ነው።

#ስምንት- በአለም ላይ ያለህ ከባዱ ተልእኮ ቢኖር ትኩረትህን አላማህ ላይ ማድረግ ነው። ቀላሉ ደግሞ እያማረሩ መኖር ነው። የቱን ትመርጣለህ?

#ዘጠኝ- ሰዎች አስፈላጊ ያልሆነ ጓደኝነት ላይ የሚቆዩት ብቸኝነትን ስለሚፈሩ ብቻ ነው። አንተስ?

#አስር- ከላይ ያነበብካቸው አንተን እንደሚጠቅሙህ ካሰብክ #የሕይወት_መመሪያን መጽሐፍ እንድታነብ እንዲሁም ይሄን #ሼር በማድረግ ወዳጆችህን እንድትጋብዛቸው በትህትና እጠይቅሀለሁ፡፡

መልካም ጊዜ

#የሕይወት_መመሪያ_መጽሐፍ 9ኛው ዕትም በገበያ ላይ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun