Get Mystery Box with random crypto!

#ይገርማል! በአንድ ወቅት፤ አንድ እጅግ ሀብታም የሆነ ሰአሊ በአንዲት ትንሽዬ መንደር ውስጥ | Teklu Tilahun - ተክሉ ጥላሁን

#ይገርማል!

በአንድ ወቅት፤ አንድ እጅግ ሀብታም የሆነ ሰአሊ በአንዲት ትንሽዬ መንደር ውስጥ ይኖር ነበር። እጅግ ማራኪ ስእሎችን በውድ ዋጋ በመሸጥም ነበር የሚተዳደረው።

ታዲያ በመንደሯ የሚኖሩ ድሀ ሰዎች እጅግ ይጠሉት እና ስግብግብ እንደሆነ ያሙታል።

ወደ ቤቱም በመሄድ ''አንተ ብዙ ገንዘብ ያለህ ሰው ነህ። ነገር ግን በመንደሯ ያሉትን ድሆች አትደግፍም። ስጋ የሚሸጠውን ሰው ብትመለከት ያንተን ያህል ሃብታም አይደለም። ነገር ግን ከሚሸጠው ስጋ ላይ ለድሆች ያካፍላል። የመንደሩ ሰዎችም ይወዱታል። እንዲሁም ዳቦ ሻጩን ተመልከት እሱም ድሀ ሲሆን ብዙ ቤተሰቦች አሉት። ነገር ግን ለድሆች በነጻ ዳቦ ይሰጣል። አንተ ለምን በዚህ ልክ ስግብግብ ትሆናለህ?'' አሉት።
ሰአሊውም ለወቀሳቸው መልስ ሳይሰጥ ሁሌም በፈገግታ ይመልሳቸው ነበር።

የመንደሯ ነዋሪዎችም የሰአሊው ፈገግታ ግራ ያጋባቸው ነበር። በዚህም ራስ ወዳድ እና ሀብት በመሰብሰብ ብቻ የተጠመደ ስግብግብ አድርገው ይቆጥሩት ነበር።

አንድ ቀንም ሀብታሙ ሰአሊ በጠና ታመመ ነገር ግን አንድም የመንደሯ ኗሪ ሊጠይቀው ወይም ሊረዳው አልመጣም። ስለዚህ ብቻውን የሚኖረው ሰአሊ ህይወቱ ያልፋል።

ከዚያም በኋላ ስጋ-ሻጩ እና ዳቦ-ጋጋሪው ለመንደሩ ይሰጡት የነበረውን ስጋ እና ዳቦ መስጠት ያቆማሉ።
ስለዚህ የመንደሩ ድሆች ለምን እርዳታቸውን እንዳቆሙ በሀዘን ተሞልተው ይጠይቃሉ።

ሁለቱም ከዚህ በፊት ወር እስከ ወር ለሚሰጧቸው ስጋ እና ዳቦ ህይወቱ ያለፈው ሰአሊ ሰው ይከፍላቸው እንደነበር እንዲሁም አሁን ያ ሰው ስለሞተ ለስጋም ሆነ ለዳቦ ዋጋ የሚከፍላቸው እንደሌለ ይነግሯቸዋል።

በዚህም የመንደሩ ኗሪዎች ይጠሉት እና ስግብግብ እያሉ ያሙት የነበረው ሰአሊ ይረዳቸው እንደነበር ይገነዘባሉ።

ቁምነገሩ~ ሰዎችን በውጫዊ ገጽታቸው እና ስለ እነሱ በሚወራው አሉባልታ ልንገምታቸው አይገባም። እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች የሚያደርጉትን መልካም ነገር በግልጽ ማሳየት አይፈልጉም ማለት ክፉ ናቸው ማለት አይደለም።

መልካምነት ራስ ጋር የሚቆይ ሰላም ነውና።

#በልኬት_ወደ_ስኬት_መጽሐፍ በገበያ ላ#ድሀ


(በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣ ከምናሳትማቸው መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ የገንዘብና የመጽሐፍት ሽልማቶችን ለማግኘት የፌስቡክና ቴሌግራም ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።)


Telegram- https://t.me/teklu_tilahun
Facebook- https://www.facebook.com/booklandbook/?