Get Mystery Box with random crypto!

በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ teklesawirossundayschool — በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ teklesawirossundayschool — በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @teklesawirossundayschool
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.58K
የሰርጥ መግለጫ

ተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት
በ1957 ተመሰረተ።
ይህ በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው::የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን እምነት ስርዓት ዶግማ ቀኖና ትውፊት በጠበቀ መልኩ መንፈሳዊ ማዕዶችን ሳቢና ለየት ባለ መልኩ እናቀርብላችኋለን ።https://youtube.com/channel/UCMgN4_

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 20:03:42
173 views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:00:09 የማ/ስ/ቅ/ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ለብዙ ዘመናዊ ስራዎች አብነት መሆኑ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነው።

በ2013 ዓ.ም በደብሩ ውስጥ የሚካሄዱ ማኑዋል ስራዎችን ወደ ዲጂታል ስርዓት ለመቀየር በማሰብ በደብሩ ውስጥ አስፈላጊ ሶፍትዌሮችንና የቴክኖሎጂ መንገዶችን ያበለጽግ ዘንድ የአይሲት ክፍል ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል። ክፍሉ በ8 ወራት ውስጥ Lideta Employee & Parishioners Management System (LEPMS) የተሰኘ መተግበሪያ አበልጽጎ ለስራ ዝግጁ አድርጓል።

ሲስተሙ የሰራተኞችን አጠቃላይ መረጃ በዘመናዊ እና በቀላል መንገድ የሚያስተዳድር ሲሆን ይህም የአስተዳደር ጽ/ቤቱን ስራ እና ተግባር በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲፈጸም የሚያስችል ነው። ሌላው የሲስተሙ ክፍል የምዕመናን አጠቃላይ መረጃ ይኸውም የሰበካ ጉባኤ አባልነት ፣ የመዝገበ ሙታን ፣ የመዝገበ ጥምቀትና የመዝገበ ከብካብ መረጃዎችን የሚያስተዳድር ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረውን የመረጃ አያያዝ የሚያዘምን ሲሆን ምዕመናን መረጃ ለማግኘት የሚያባክኑትን ጊዜ ፣ ገንዘብና ድካም የሚቀንስ ነው። ለወደፊቱም የሰንበት ት/ቤቱን የደብሩን ወጣቶች እና ሌሎች ተጓዳኝ መረጃዎችን የሚመዘግብ ሆኖ ይታደሳል።

በዛሬውም ዕለት የአድባራቱ ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ሀብተወልድ ተገኝ ፣ የደብሩ ዋና ጸሀፊ ሊቀ ስዩማን መሐሪ አድማሱና የደብሩ ዋና ሒሳብ ሹም ሊቀ ኅሩያን ሸዋንግዛው ወልደ ጻድቅ የመጀመሪያ ተመዝጋቢዎች በመሆን የምዝገባ ስርዓቱን አስጀምረዋል። ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ በደብሩ የአይሲቲና የስታትስቲክ ክፍሎች ጥምረት የምዕመናኑ መረጃ ወደ ዳታቤዝ የሚገባ ይሆናል። በመቀጠልም ለሌሎች የአስተዳደር ክፍሎች የሚያስፈልጉ የሶፍትዌር ግብዓቶችን ክፍሉ አበልጽጎ የሚያቀርብ ይሆናል።

የደብሩ አይሲቲ ክፍል
178 views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:46:43
#Update

ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል።

በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው  የጉዞ መርሐ ግብር መሠረትም ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
126 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:51:49
413 views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:33:12 ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ የክብር ዶክትሬት ሰጠ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜንና የደቡብ ወሎ እና የከሚሴ ዞን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የክብር ዶክትሬት ሰጠ።

ዩኒቨርሲቲው ለብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ የክብር ዶክትሬቱን የሰጣቸው÷ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር እየኖሩ ያሉ እንዲሁም ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ ታላቅ ዓርዓያ ሰብ በመሆናቸው ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል፡፡
398 views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:23:16 #ዜና ቤተክርስቲያን
የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በስብከተ ወንጌል ክፍሉ አዘጋጅነት 1ዓመት ከ5 ወራት ያስተማራቸውን የአካባቢው ወጣቶችና ማኅበራት #ሊያስመርቅ ነው!!
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

(ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ክፍል አዘጋጅነት ለተከታታይ1 ዓመት ከ5 ወራት ያስተማራቸውን 200 የአካባቢው ወጣቶችና
ማኅበራት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ከ1 ወር በኋላ ሊያስመርቅ መሆኑ ተገልጿል።

ዓመታዊና ወርኃዊ እንዲሁም ሳምንታዊ ጉባኤያትን ከማከናወን ባለፈ የካህናት ንስሐ ልጆች በአንድነት ስብስቦ ትምህርተ ወንጌል በመስጠት፣
ሰ/ት/ቤቱን በማጠናከር ላይ የሚገኘው የደብሩ ስብከተ ወንጌል ክፍል የአካባቢውን ወጣቶችና ማኅበራት ተከታታይ ትምህርት በማስተማር ብዙዎችን ያስደነቀ ተግባር ላይ እንዳለ ብዙዎች ይመሰክራሉ።

በአሁኑ ስዓት የአካባቢውን ወጣቶችና ልዩ ልዩ ማኅበራትን ታሳቢ ተደርጎ ለ1 ዓመት ከ5 ወራት ሲሰጥ የነበረው ተከታታይ ትምህርት መጠናቀቁን ተከትሎ ተመራቂ ተማሪዎቹ የመመረቂያ ጽሁፎቻቸውን ባለሙያዎችና በርካታ ታዳምያን በተገኙበት ማቅረብ ጀምረዋል።

ከበዓለ ጥምቀት መከበር በኋላ በደብሩ በተዘጋጀው የምሥጋና መርሐግብር ላይ ከአካባቢው ወጣቶችና ማኅበራት ጋር በተደረገው ውይይት አጭር ሥልጠና ለመስጠት በማሰብ ከመጋቢት 20-25 ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን ጨምሮ ሌሎችም መምህራን የተሳተፉበት የ5 ተከታታይ ቀናት ሥልጠና ተሰጥቷል።

820 ታዳምያን የተሳተፉበት ይህ የአጭር ጊዜ ሥልጠና በፈጠረው መንፈሳዊ መነቃቃት የተነሣ ለ1 ዓመት ከ5 ወራት ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚለውን ስሁት አስተምሮ ጨምሮ 13 የትምህርት ዓይነቶችን በዲ/ቆን ያረጋል አበጋዝ (ዶ/ር)፣ በመ/ር ግርማ ባቱ፣በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣በመ/ር አብነት አሥራት፣ በመ/ር አባ ጌድዮን (ዶ/ር) እና በመ/ር መታሰቢያ ደምሴ በጥቅሉ በ6 መምህራን ሲሰጥ መቆየቱን ከአስተባባሪዎቹ ለመረዳት ችለናል።

የነገረ ሃይማኖት መግቢያን ጨምሮ አንጻራዊ ትምህርተ መለኮት፣ዕቅበተ እምነት፣ ወጣትነትና መንፈሳዊ ሕይወት፣ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፣የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓተ አምልኮ እና ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚለው ስሁት አስተምሮን የሚዳስሰው ትምህርት ከተሰጡ የትምህርት ዓይነቶች ተጠቃሾች መሆናቸውም ተገልጿል።

በደብሩ ስብከተ ወንጌል ክፍል ከሚሰጡ ሌሎች መርሐ ግብሮች ባልተናነሰ መልኩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በርካታ ተማሪዎችን በመመዝገብ የተጀመረው ትምህርት ከ17 ወራት ቆይታ በኋላ አጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተጠናቆ ለምርቃት በመዘጋጀት ላይ የሚገኙት ተማሪዎች በተደራጁበት ቡድን ጥናታዊ ፅሁፋቸውን በደብሩ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ማቅረብ መጀመራቸውን በቦታው ተገኝተን ተመልክተናል።

በጥናት አቅራቢዎቹ እና አማካሪዎቻቸው አማካኝነት ከተመረጡት አንገብጋቢ እና ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ርእሰ ጉዳዮች ውስጥ 17 ጥናታዊ ፅሁፎች የተሠሩ ሲሆን 4ቱ ጥናታዊ ፅሁፎች በዛሬው ዕለት ቀርበው በጥናት ባለሙያዎችና በታዳምያኑ ተደምጠዋል፣ በጥናት ዝግጅቱና በአቀራረቡ ዙሪያም የሰላ ሂስ ተሰጥቶባቸዋል።

"አማኞች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ወደ ሌሎች ቤተእምነቶች የሚሄዱበት ምክንያቶችና መፍትሔዎቻቸው ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያበረከተችው አስተዋጽኦ፣ኦርቶዶክሳዊ ሥርዓተ ጋብቻ በአማኞች ዘንድ የማይተገበርበት ምክንያቶችና መፍትሔዎቻቸው እንዲሁም ተግባራዊ ክርስትና እንዴትና በምን ይገለጣል?" በዕለቱ የቀረቡ 4 የመመረቂያ ጥናታዊ ፅሁፎች ናቸው።

ቡድናቸውን ወክለው ወ/ት ተስፋነሽ ስሜ ፣የሽወርቅ ፈንታብል ሊያ አምባቸውና ፀጋው ደረጄ በተባሉ 4 ጥናት አቅራቢዎች በቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፎቹ ለተነሡት ልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች አነሳሽ ናቸው የተባሉ ምክንያቶች፣ ጉዳቱ በቤተክርስቲያኒቱና አማንያኑ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ ያመጣው ውጤትና የመፍትሔ ሐሳቦች ተዳሰዋል።

የደብሩ ስብከተ ወንጌል ኃላፊ ሊቀጉባኤ አምባዬ አባተ በመርሐ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ጥናት አቅራቢዎቹን አበረታተው ለ1 ዓመት ከ5 ወራት ሲሰጥ የቆየውተከታታይ ትምህርት በየአደባባይ በዓላቱ እየተገኙ ምንጣፍ ከማንጠፍ፣ የበዓሉን ድባብ የሚያጎሉ ክንውኖችን ከማከናወን ባሻገር ሕይወታዊ ለውጥ የማይታይባቸውን ወጣቶች ለማነፅና በዙሪያችን ያለው የመንጋ ንጥቂለመመከት ነው ሲሉ የተጀመረበትን ምክንያት አስረድተዋል።

ስብከተ ወንጌል ክፍሉ በዓመታዊ ዕቅዱ ከያዛቸው ቋሚ የአገልግሎት ክንውኖች በተጨማሪ በልዩ ትኩረትና እንቅስቃሴ ለአካባቢው ወጣቶችና ማኅበራት እየተሰጠ የቆየውን ተከታታይ ትምህርት ከመፍቀድ ጀምሮ በልዩ ልዩ መንገዶች ሲደግፍ ለነበረው የደብሩ ሰ/ጉ/ጽ/ቤት፣በሙያቸው ያገለገሉ መምህራንና ሌሎችም በጎ አድራጊ ኦርቶዶክሳዊ ምዕመናን ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

ስብከተ ወንጌል ኃላፊው አክለውም በዚህ መልኩ ተምረው የጨረሱትን ደቀ መዛሙርት በደብሩ መንፈሳዊ መዋቅር ውስጥ በማቀፍ በበጎ ፈቃደኝነት የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱን እንዲደግፉ፣ ባሉበት አካባቢና በሚሰሩበት የሥራ ቦታ ስለቤተክርስቲያንና ስለቃሉ ምስክሮችና አቃብያን እንዲሆኑ የተቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ገልጸው የሂደቱን ቀጣይነትም አረጋግጠዋል።

መርሐ ግብሩን አስመልክቶ ካነጋገርናቸው ተሳታፊዎች መካከል በማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ክፍል እየተሠራ ያለው ሰው ተኮር እንቅስቃሴ በሌሎች ገዳማትና አድባራትም በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ሐሳባቸውን አካፍለውናል።

ደብሩ በዕለቱ ከቀረቡት 4 የመመረቂያ ጥናታዊ ፅሁፎች በተጨማሪ ቀሪዎቹ 14 ጥናታዊ ፅሁፎች በሂደት ቀርበው ከተጠናቀቁ በኋላ #መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለማስመረቅ ማቀዱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በመርሐ ግብሩም የቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ የመሠረተ ዕምነት ፋክሊቲ ዲን መ/ር አብነት አሥራትን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶች፣ የደብሩ ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎችና አገልጋዮች እንዲሁም በርካታ የጥናቱ ታዳምያናን ተገኝተዋል።

በመ/ር ሽፈራው እንደሻው
ምንጭ :- አዲስ አበባ ሀገረስብከት
365 views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:25:12
401 views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:37:38
ዜና እረፍት
የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው ፍቅር ጌቱ ወላጅ አባት ስላረፋ ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ 20/12/2014 ዓ.ም ከረፋዱ 5:30 ሰዓት ላይ የተፈጸመ ሲሆን በአካል መገኘትና የምንችል አባላት በመኖሪያ ቤታቸው በመገኘት እህታችንን ና ቤተሰቦቿን እንድናጽናና ይሁን ፡፡

አድራሻ:- ከአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወረድ ብሎ

እግዚአብሄር አምላክ የአባታችንን ነፍስ በአፀደ ገነት ያሳርፍልን ለቤተሰቦቻቸውም መፅናናትን ያድልልን እመ አምላክ የልባቸውን ሀዘን ታቅልልን!!!!
409 viewsedited  10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:35:21
403 views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 17:39:38
ዜና ቤተክርስቲያን
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ልዑክ በሕመም ያሉትን ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊን ጎበኘ !!!
ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም (አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች ልዑክ በሕመም ላይ የሚገኙትን ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊን መጎብኘቱንየጉባኤው ጠቅላይ ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ አስታውቀዋል።

የበላይ ጠባቂ አባቶች ልዑኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በሚገኘው የብፁዓን አባቶች ማረፍያ በመገኘት ነው በቅርቡ በሕመም ላይ የሚገኙትን ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊን የጎበኘው።

ቀሲስ ታጋይ ታደለ አብሮነት ፣ መከባበር እና መጠያየቃችን ለጋራ ዕሴታችን ይጠቅማል ከመበሻሸቅ መከባበርን እንምረጥ ሲሉ ለበላይ ጠባቂ አባቶች ምስጋና አቅርበዋል።

ምንጭ:- አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት
429 views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ