Get Mystery Box with random crypto!

የማ/ስ/ቅ/ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት | በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተክርስቲያናት የተክለ ሣዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት

የማ/ስ/ቅ/ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን አስተዳደር ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ለብዙ ዘመናዊ ስራዎች አብነት መሆኑ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነው።

በ2013 ዓ.ም በደብሩ ውስጥ የሚካሄዱ ማኑዋል ስራዎችን ወደ ዲጂታል ስርዓት ለመቀየር በማሰብ በደብሩ ውስጥ አስፈላጊ ሶፍትዌሮችንና የቴክኖሎጂ መንገዶችን ያበለጽግ ዘንድ የአይሲት ክፍል ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል። ክፍሉ በ8 ወራት ውስጥ Lideta Employee & Parishioners Management System (LEPMS) የተሰኘ መተግበሪያ አበልጽጎ ለስራ ዝግጁ አድርጓል።

ሲስተሙ የሰራተኞችን አጠቃላይ መረጃ በዘመናዊ እና በቀላል መንገድ የሚያስተዳድር ሲሆን ይህም የአስተዳደር ጽ/ቤቱን ስራ እና ተግባር በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲፈጸም የሚያስችል ነው። ሌላው የሲስተሙ ክፍል የምዕመናን አጠቃላይ መረጃ ይኸውም የሰበካ ጉባኤ አባልነት ፣ የመዝገበ ሙታን ፣ የመዝገበ ጥምቀትና የመዝገበ ከብካብ መረጃዎችን የሚያስተዳድር ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረውን የመረጃ አያያዝ የሚያዘምን ሲሆን ምዕመናን መረጃ ለማግኘት የሚያባክኑትን ጊዜ ፣ ገንዘብና ድካም የሚቀንስ ነው። ለወደፊቱም የሰንበት ት/ቤቱን የደብሩን ወጣቶች እና ሌሎች ተጓዳኝ መረጃዎችን የሚመዘግብ ሆኖ ይታደሳል።

በዛሬውም ዕለት የአድባራቱ ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ሀብተወልድ ተገኝ ፣ የደብሩ ዋና ጸሀፊ ሊቀ ስዩማን መሐሪ አድማሱና የደብሩ ዋና ሒሳብ ሹም ሊቀ ኅሩያን ሸዋንግዛው ወልደ ጻድቅ የመጀመሪያ ተመዝጋቢዎች በመሆን የምዝገባ ስርዓቱን አስጀምረዋል። ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ በደብሩ የአይሲቲና የስታትስቲክ ክፍሎች ጥምረት የምዕመናኑ መረጃ ወደ ዳታቤዝ የሚገባ ይሆናል። በመቀጠልም ለሌሎች የአስተዳደር ክፍሎች የሚያስፈልጉ የሶፍትዌር ግብዓቶችን ክፍሉ አበልጽጎ የሚያቀርብ ይሆናል።

የደብሩ አይሲቲ ክፍል