Get Mystery Box with random crypto!

ስማርት ስልኮቻችን ሀይል እንዴት መሙላት አለብን…? በርካታ ተግባራትን የሚያከናውኑበት ስማርት ስ | Techopia Tube

ስማርት ስልኮቻችን ሀይል እንዴት መሙላት አለብን…?

በርካታ ተግባራትን የሚያከናውኑበት ስማርት ስልክዎ ባትሪ በፍጥነት እያለቀ ተችገረዋል?

የተለያዩ ስልቶችን ተጠቅመው የስልክዎን ባትሪ ቢያንስ ሙሉ ቀን እንዲያስጠቅምዎትስ ጥረት አድርገዋል?

በቴክኖሎጂው መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች የስልካችን ባትሪ በፍጥነት እያለቀ የምንቸገረው በሶስት ምክንያቶች መሆኑን ይገልፃሉ።

የመጀመሪያው በስማርት ስልኮቻችን የጫንናቸው መተግበሪያዎች መብዛት እና እያወቅንም ይሁን ሳናውቅ ተከፍተው ባትሪ መብላታቸው
ነው።
የስማርት ስልካችን ላይ ሙጭጭ ብለን አልላቀቅ ማለትም ሌላኛው የባትሪ እድሜን የሚያሳጥር ልማድ ነው።

ሶስተኛው እና ዋነኛው የባትሪ ህይወትን የሚያሳጥረው ተብሎ በባለሙያዎች የተጠቀሰው ደግሞ የሀይል አሞላላችን (ቻርጅ አደራረጋችን መሆኑ ተገልጿል።

ብዙዎቻችን የስማርት ስልካችን ባትሪ ሙሉ በሙሉ ሲያልቅ ቻርጅ ማድረግ እንዳለብን እናምናለን።

በአንዳንዶቻችን ዘንድ ደግሞ ቻርጅ እንደሰካን ሞባይላችንን መጠቀም የባትሪውን አገልግሎት ያራዝማል የሚል አመለካከት አለ።

ይሁን እንጂ የሞባይል ባትሪ እንደ ሰው ልጅ ሁሉ “መጨናነቅን” አይወድም ነው የሚለው ባትሪ ዩኒቨርሲቲ የተሰኘ ኩባንያ።

ስልካችንን ቻርጅ እያደረግን መጠቀም የባትሪውን እድሜ ያሳጥራልም ይላል።

ስለ ስማርት ስልክዎ ባትሪ ከመጨነቅ የሚገላግሉ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችም ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች አስቀምጧል።

የስልክዎ ባትሪ ሙሉ ቻርጅ ከተደረገ በኋላ ሞባይሉን ከቻርጀሩ ይንቀሉት፡

ኩባንያው እንደሚለው የስማርት ስልካችን ባትሪ ከአቅሙ በላይ ቻርጅ ሲደረግ የረጅም ጊዜ አገልግሎቱ እየወረደ ይመጣል።

ስልካችን 100 ፐርሰንት ቻርጅ ከሆነ በኋላ እንደተሰካ መተው ለከፍተኛ መጨናነቅ በመዳረግ የባትሪውን ሀይል የመያዝ አቅም ይቀንሰዋል።

(እስከ 100 ፐርሰንት ቻርግ ማድረግም ለመጀመሪያ ጊዜ ካልሆነ አስፈላጊ አይደለም፡

ከአድካሚ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኋላ ጡንቻዎችን ማፍታታት እንደሚገባ ሁሉ ስልካችንም ሙሉ በሙሉ በሀይል ከተሞላ በኋላ ከቻርጀሩ መንቀል ይገባል።

ባትሪውን ከሙቀት ይጠብቁት
የስማርት ስልክ ባትሪዎች በቀላሉ በሙቀት ይግላሉ።

ለዚህም ነው አፕል ራሱ የአይፎን ስልኮችን ቻርጅ ስታደርጉ መሸፈኛ (ኬዞቹን ብታወጡት በማለት የሚመክረው።

ስለሆነም ስልካችን ቻርጅ ስናደርግ መሞቁን ካስተዋልን ሽፋኑን ማውጣት ይኖርብናል።

የባትሪያችን ጤና ለመጠበቅ ስማርት ስልካችን ቻርጅ የምናደርግበት አካባቢ የፀሀይ ሙቀት የሌለበት ቢሆንም ጥሩ ነው።

100 ፐርሰንት ላይ እስከሚደርስ መጠበቅ የለብንም፡

እንደ ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ገለፃ ከሆነ ከፍተኛ ቮልቴጅ ባትሪውን ስለሚያጨናንቀው ባትሪን መቶ በመቶ ሀይል መሙላት አያስፈልግም።

ስማርት ስልካችን ቀኑን ሙሉ ቻርጅ ማድረግም በባትሪው እድሜ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብሏል።

ቻርጅ ለማድረግ የባትሪውን ማለቅ አይጠብቁ።

ስልካችን ቻርጅ ለማድረግ ባትሪው ተሟጦ እስኪያልቅ መጠበቅ የለብንም።

ባገኘነው አጋጣሚ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን ሀይል ይዞ የመቆየት አቅም ያሳድገዋል።

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ስልቶች የስማርት ስልካችን ባትሪ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል እና ቀኑን ሙሉ ከስጋት ነፃ እንድንሆን ይረዳናል ።

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
━━━━━━━━━━━━━━━
: @techopiatube2
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬ Share ▬▬▬▬▬