Get Mystery Box with random crypto!

የስልክዎት ፍጥነት እየዘገየ አስቸገረዎት? የስልክዎን ፍጥነት ወደቀድመው ለመመለስ እነዚህን ቀላል | Techopia Tube

የስልክዎት ፍጥነት እየዘገየ አስቸገረዎት?
የስልክዎን ፍጥነት ወደቀድመው ለመመለስ እነዚህን ቀላል የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀሙ፡፡
1. ችግሩን ለመለየት ይሞክሩ
የስልክ ፍጥነት ችግር በበርካታ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል፡፡
እነዚህን ችግሮች ምናልባት የተከሰቱት ኮራብት በሆኑ አፕልከሽኖችና ፋይሎች፤በRAMና በstorage መጣበብ ወይም በቫይረስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ማወቅ ስንችል የቅርብ ግዜ(latest) የሆኑ ስልኮች እራሳቸው cleaner አላቸው።
በነዚህ አፕልኬሽኖች ታግዘው የስልክዎን ብቃት
(performance) ሪፖርት ማየት ይችላሉ፡፡ ቀጥሎም የሚከተሉትን ዘዴዎችን ይሞክሩ፡፡
2. አላስፈላጊ የሆኑ አፕልከሽኖችን ያጥፉ
ተጠቅመው የማያውቅትን አፕልከሽኖችን ያጥፉ ወይም freeze ያርጓቸው(ለ latest ስልኮች)
3. የአፕልከሽኖችን cach data ያጥፉ ካች ዳታ ማለት አፕልከሽኖች ለሌላ ጊዜ ለፍጥነት እንዲረዳቸው
በራሳቸው የሚያስቀምጡት ዳታ ነው ነገር ግን ይህ ዳታ እየበዛ ስሄድ የስልኩን የውስጥ storage ቦታ በከፍተኛ ሁኔታ ሊይዝ ይችላል።
ካች ዳታ ለማጥፋት setting =>apps(all application) ውስጥ ገብተን በየአንዳንዱ አፕልኬሽን ውስጥ እየገባን "clear cache" የምለውን በመምረጥ ካች ዳታ ማጥፋት ይቻላል፡፡
4. የስልክዎን ስቶረጅ( storage ) ያጽዱ
የስልክዎ storage አላስፈላጊ በሆኑ ፋይሎች ተጣቦ ሊሆን ይችላል። እነዚህን ፋይሎች ማጥፋት በተለይም የስልኩን የውስጥ ስቶሬጅ(internal storage) ማጥፋት ለስልክዎ ስራ ጥሩ የመተንፈሻ ቦታ ይሰጣል፡፡
5. (widgets), በአንመሽን የተሞሉ launcher እና(animated launchers and live wallpapers ) አይጠቀሙ። ውድጌቶች(widgets), በአንመሽን የተሞሉ ላውንቸረችንና ዋልፔፐሮች(animated launchers and live wallpapers ) የስልካችንን ራምና ፕሮሰሰር ሊያጣብቡና ሊያጨናንቁ ስለሚችሉ ውድጌቶችን ያለመጠቀም ይምረጣል፡፡ በተጨማሪም ውድጌቶች(widgets), በአንመሽን የተሞሉ
ላውንቸረችንና ዋልፐፐሮች(animated launchers and live wallpapers ) የባትሪ ጠላቶች ናቸው፡፡
6. በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን አይጠቀሙ
በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን መክፈት ከስልካችን አቅም በላይ ሆኖ የስልኩን ፕሮሰሰርና ራም ልያጨናንቅና ልያስቸግር ይችላል፡፡ስለዚህ በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን አይጠቀሙ፡፡
7. ፎርማት(format) ያድርጉ (ፋክተሪ ሪሲት)
ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች አንድሮይድ ስልክዎን ፍጥነት ልያሻሽሉ ይችላሉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ልያጠፉ አይችሉም፡፡
ፎርማት(format) ማድረግ ግን ወደ ቀድመው ፍጥንት ልመልስ ይችላል፡፡ ነገር ግን ስልከዎን ፎርማት ከማድረገዎ በፊት ባክአፕ
(backup) ማድረግ የግድ ነው።

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
━━━━━━━━━━━━━━━
: @techopiatube2
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬ Share ▬