Get Mystery Box with random crypto!

@Techopiatube2 Android ምንድን ነው Android Open Source የሆነ Opera | Techopia Tube

@Techopiatube2
Android ምንድን ነው
Android Open Source የሆነ Operating System ሲሆን በብዛት ለስማርት ስልኮች ያገለግላል!

ጎግል በ 2003 አንድሮድን ያገኘ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ለተንቀሳቃሽ ስልኮች በጣም ታዋቂው Operating System ሲስተም ሊሆን ችሏል!

Android ስራው ምንድን ነው

አንድሮድ Operating System ሲስተም ስለሆነ ዓላማው ተጠቃሚውን እና መሣሪያውን ማገናኘት ወይም ማግባባት ነው!
ለምሳሌ : አንድ ተጠቃሚ Text መላክ በሚፈልግበት ጊዜ አንድሮይድ ለተጠቃሚው የመፃፊያ Keyboard ይሰጣል! ፅፎ ሲጨርስ ደግሞ ተጠቃሚው መላኪያውን በሚነካበት ጊዜ Android መልእክቱ እንዲልክ ስልኩን ይመራዋል!
Google በየአመቱ ለ Android System Update ይለቃል! ምንም እንኳን Google ለ Android እድገት ትልቅ ሚና ቢጫወትም ጉግል የ Android Operating ሲስተምን ለሞባይል አምራቾች በነፃ ይሰጣል!
Electric ፣ Samsung ፣ LG ፣ Huawei ፣ Lenevo እና Sony አንድሮይድን በሚያመርቷቸው ስልኮች ላይ ከሚጭኑ አምራቾች ጥቂቶቹ ናቸው! በአሁን ሰአት Android Operating System በአንድ ቢሊዮን ሞባይሎች ላይ ተጭኖ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል!
ብዙ ሰዎች የሚያነሱት አንድ የተለመደ ጥያቄ Android ለምን በተለያዩ ስልኮች ላይ የተለያየ መልክ ይይዛል? የሚል ነው! መልሱም ብዙ የ Android ስሪቶች አሉ ምክንያቱም Android Open Source ሶፍትዌር ስለሆነ የሞባይል አምራቾች በሶፍትዌሩ ላይ የሚፈልጓቸውን ለውጦችን ማድረግ ይችላሉ።

አንድሮይድ ስማርት ስልካችንን እንዴት ማሻሻል /update/ ማድረግ ይቻላል?
በስማርት ስልኮች ኦፕሬቲንግ ሲስተም ገበያ ውስጥ አንድሮይድ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።
የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ባለቤት የሆነው ጎግል፥ በየጊዜው በአንድሮይድ ላይ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ያደርጋል።
በዚሁ ጊዜም የተሻለ አገልግሎት ለማግኘት የአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተማችንን ማሻሻል /update/ ማድረግ ይጠበቅብናል።

አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን በየጊዜው ለምን ማሻሻል ያስፈልጋል…?
1 የስልካችን የመስራት አቅም እንዲጨምር
2 የስልካችን እድሜምን ለማርዘም
3 አዳዲስ ማሻሻያዎችን ለመጠቀም
4 የሰልካችንን ደህንነት ለመጠበውቅ
5 ስልካችንን ከተለያዩ የቫይረስ ጥቃት ለመከላከል
6 የስልካችን ባትሪ የቆይታ እንድሜን ለማርዘም
አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለማሻሻል /update/ ለማድረግ መከተል ያለብን ቅደም ተከተል..
1. የአንድሮይድ ስልካችን መተግበሪያ ውስጥ በመግባት ሴቲንግስ /Settings/ መክፈት
2. ከሚመጡልን ዝርዝር ውስጥ “About phone” ወይም ሌላ ተመሳሳይ አማራጭ መክፈት
3. ከዛም “System Updates” ወይም “Software Update” የሚል አማራጭ የሚመጣልን ሲሆን፥ እዛ ውስጥ በመግባት ማሻሻል እንችላለን።
4. “System Updates” በምንከፍትበት ጊዜ በርከት ያሉ አማራጮች የሚመጡ ከሆነ “Check for updates now”፣ “Software update check” ወይም ሌሎች ተመሳሳይ አማራጮች ውስጥ በመግባት የስማርት ስልካችን ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማሻሻል /update/ ማድረግ እንችላላን።
ማስጠንቀቂያ፦
በ WiFi Update ቢያደርጉት ይመረጣል።
በቅድሚያ ስልክዎትን በበቂ ሁኔታ ቻርጅ ያድርጉ Update እያደረገ ባለበት ሁኔታ ቻርጅ ቢዘጋ ስልኮ አደጋ ውጥ ሊገባ ይችላል።
share በማድረግ ሌሎችንም ያሳውቁ!!

በዚህ የቴሌግራም ቻናል ስለ computer, smartphone እና በአጠቃላይ የተለያዩ ምርጥ ምርጥ የቴክኖሎጂ መረጃ እና ዕውቀቶችን ያገኙበታል ።