Get Mystery Box with random crypto!

ወንጌል ለምን እንመሰክራለን?   ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሄር ጋር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ባ | Tebazu Bekele Official

ወንጌል ለምን እንመሰክራለን?

  ሰዎች ሁሉ ከእግዚአብሄር ጋር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ባለ እምነት ታርቀው የዘላለምን ህይወት እንዲያገኙ ካለን ልባዊ ፍላጎት  የተነሣ ወንጌልን እንሰብካለን። ሰዎች የምስራቹን ካልሰሙ በኃጢአታቸው ምክንያት የዘላለም ሞትን ይሞታሉ። የእግዚአብሄርም ቁጣ በአለማመናቸው ምክንያት በእነሱ ላይ ይኾናል። የምንመሰክርበትን አንኳር ምክንያት በሁለት መንገድ ማስቀመጥ እንችላለን።  ሰዎችን በክርስቶስ ፍቅር ስለምንወድዳቸው ወንጌልን እንነግራቸዋለን። “..የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል..” (2ቆሮ.5፡14)። የተካፈልንውን የክርስቶስ ፍቅር ፣ ያገኘንውን የዘላለም ህይወት ለሰዎች ማካፈል ደስታችን ነው (1ዩሐ.1፡1-4)። ወንጌልን መመስከር ከፍቅር የተነሣ የምናደርገው ተግባር ነው። ሰዎች በኃጢአታቸው እንዳይጠፉ፣ የዘላለምን ህይወት እንዲያገኙ ስለምንፈልግ ወንጌልን እንመሰክራለን።

ሌላው ምክንያት ወንጌልን መመስከር ከጌታ የተሰጠን ትዕዛዝ ስለሆነ እንመሰክራለን። የምስክርነት ተግባር በአራቱም ወንጌላት እና በሐዋርያት ስራ ተጠቅሷል (ማቴ.28፡18-20፣ ማርቆ.16፡15፣ሉቃ.24፡47 ፣ ዩሐ.20፡21 ሐዋ.1፡8)። ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ለማድረስ ለሆነው አገልግሎት በእግዚአብሄር  ተልከናል።

በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሄር ጋር የተራቁ ሰዎች ሁሉ ሌሎች እንዲታረቁ የማስታረቅን አገልግሎት ተቀብለዋል፣ “እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን..”(2ቆሮ.5፡19-20)። ይሄ አገልግሎት በእግዚአብሄር ለሁላችንም ተሰጥቶናል።

ከጨለማው ዓለም የጠራንን፣ የዘላለም ህይወት የሰጠንን፣ ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ ያልተገባንን ቸርነት ያደረገልንን የጌታን በጎነት ለሌሎች መናገር የምድር ቆይታችን አገልግሎት ነው። ሐዋርያው ጴጥሮስ ስለዚህ አገልግሎታችን እንዲህ ብሎ ይናገራል፣ “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ..”(1ጴጥ 2፡9-10)።
Join us
  @gototheworld1
@gototheworld1