Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ተወለደ። በወላይታ ዞን በገሱባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁ | ታማኝ ዜና

ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ተወለደ።

በወላይታ ዞን በገሱባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ትላንት ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተገላገለች።

ይህ ክስተት " Natal teeth " ተብሎ እንደሚጠራ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚገልፁ ሲሆን ከዚህ በፊት ብዙም ያልተለመደ ቢሆንም አዲስ ከሚወለዱ ከ2000 - 3000 ሕጻናት ውስጥ በአንዱ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

ትላንትና የተወለደው ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ምንም ሳይቸገር ጡት እየጠባ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን መረጃ ያሳያል።

በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ሊሰጥ የሚችል ፅሁፍ በዚህ ድረገፅ ማግኘት ይቻላል ፦ https://www.stanfordchildrens.org/en/topic/default?id=natal-teeth-90-P01862

#ወላይታዞንኮሚኒኬሽን #tikvah

@tamagnzena @tamagnzena