Get Mystery Box with random crypto!

#Monkeypox የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) በተለያዩ ሀገራት እየተሰራጨ ነው። ጎረቤት | ታማኝ ዜና

#Monkeypox

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) በተለያዩ ሀገራት እየተሰራጨ ነው። ጎረቤት ኬንያም ከዚህ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ አግኝታ ናሙናዎችን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሴኔጋል ልካለች።

ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር በተያያዘ ማወቅ ያለብን ጉዳዮች ፦

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው ?

በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ሰዎች መጀመሪያ ላይ ሙቀት፣ራስ ምታት፣ የጀርባ ሕመም፣ የጡንቻ ሕመም፣ የሰውነት ማበጥ እና በማንኛውም ነገር ላይ ፍላጎት ማጣት ይታይባቸዋል።

ሙቀቱ ጋብ ሲል ሰውነት ከፊት ጀምሮ ማሳከክ ይጀምራል። መላው ሰውነትን ቢያሳክክም ክንድና እግር የበለጠ ያሳክካሉ።

የሚከሰተው እከክ በጣም የሚያምና በተለያየ ደረጃ የሚያልፍ ነው።

ቆዳ ላይ የሚከሰተው እብጠት ኋላ ላይ ቆዳ እንዲቆስልና እንዲረግፍም ያደርል። ጠባሳ ጥሎም ሊያልፍ ይችላል። ሕመሙ በራሱ ጊዜ የሚጠፋ ሲሆን ከ14 - 21 ቀናት ይወስድበታል።

በሽታው እንዴት ይይዛል ?

በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ሰዎች ተጋላጭ ናቸው። በቆዳችን ክፍተቶች በኩል፣በዓይን፣ በአፍንጫ ወይም በአፍ በኩል ቫይረሱ ወደ ሰውነታች ይገባል።

በወሲብ ወቅት ባለ ንክኪም ቫይረሱ ይተላለፋል።

በቫይረሱ ከተያዙ ዝንጀሮዎች፣ አይጦች ወይም ሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ከተደረገ ቫይረሱ ወደሰው ይተላለፋል። ቫይረሱ በልብስ/በሌሎች ንክኪ ባላቸው ጨርቆች በኩል ይተላለፋል።

ምን ያህል አስጊ ነው ?

አብዛኞቹ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ለከፋ ሕመም አይዳረጉም።

ልክእንደ ፈንጣጣ በተወሰኑ ሳምንታት ውስጥ ይጠፋል። ሆኖም ግን በሽታው ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስም ይችላል።

በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ሳቢያ የሞቱ ሰዎች አሉ።

ሕክምና አለው ?

ሕክምና የለውም። ስርጭቱን ግን መቆጣጠር ይቻላል።

Via BBC/WHO #tikvah

@tamagnzena