Get Mystery Box with random crypto!

ቡሄ በሉ ቡሄ በሉ/2/ ልጆች ሁሉ የኛማ ጌታ ሆ የዓለም ፈጣሪ ሆ የሰላም አምላክ | 𝕡𝕒𝕤𝕤𝕔𝕠𝕕𝕖 🤟

ቡሄ በሉ

ቡሄ በሉ/2/
ልጆች ሁሉ
የኛማ ጌታ ሆ
የዓለም ፈጣሪ ሆ
የሰላም አምላክ ሆ
ትሁት መሃሪ ሆ
በደብረ ታቦር ሆ
የተገለጠው ሆ
ልብሱ እንደፀሀይ ሆ
በርቶ የታየው ሆ
ልብሱ እንደብርሃን ሆ
ያንፀባረቀው ሆ

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

ያዕቆብ ዮሐንስ ሆ
እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ
አምላክን አዩት ሆ
ሙሴ ኤልያስ ሆ
አባትም አለ ሆ
ልጄን ስሙት ሆ
ቃሌ ነውና ሆ
የወለድኩት ሆ

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

ታቦር አርቦኒየም ሆ
ማን ጠየቃቸው ሆ
ቅዱስ ተራራ ሆ
እጅግ ደስ አላቸው ሆ
ሰላም ሰላም ሆ
የታቦር ተራራ ሆ
ብርሃነ መለኮት ሆ
አንቺ ላይ አበራ ሆ

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

በተዋህዶ ሆ
ወልድ የከበረው ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ
ወልደ ማርያም ነው ሆ
ቡሄ በሉ/2/ ሆ
የአዳም ልጆች ሆ
ብርሃንን ሆ
ተቀበሉ ሆ

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

አባቴም ቤት አለኝ ለከት
እናቴም ቤት አለኝ ለከት
አጎቴም ቤት አለኝ ለከት
አክስቴም ቤት አለኝ ለከት
ተከምሯል እንደ ኩበት

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

የዓመት ልምዳቸሁ ሆ
ከጥንት የመጣ ሆ
የተከመረው ሆ
ከመሶብ ይውጣ ሆ
ከደብረ ታቦር ሆ
ጌታ ስለመጣ ሆ
የተጋገረው ሆ
ሙልሙሉ ይምጣ ሆ

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

ኢትዮጲያውያን ሆ
ታሪክ ያላችሁ ሆ
ባህላችሁን ሆ
ያዙ አጥብቃችሁ ሆ
ችቦውን አብሩት ሆ
እንደ አባቶቻችሁ ሆ
ሚስጥር ስላለው ሆ
ደስ ይበላችሁ ሆ

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

አባቶቻችን ሆ
ያወረሱን ሆ
የቡሄው ትርጉም ሆ
ያሳወቁን ሆ
እንድንጠብቀው ሆ
ለኛ የሰጡን ሆ
ይሄን ነውና ሆ
ያስረከቡን ሆ

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

ለድንግል ማርያም ሆ
አስራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ፃድቃን ሆ
የሞሉብሽ ሆ
በረከታቸው ሆ
ያደረብሽ ሆ
ሁሌም እንግዶች ሆ
የሚያርፉብሽ ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ሆ
ኢትዮጲያ ነሽ ሆ

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

ለሃዋርያት ሆ
የላከ መንፈስ ሆ
ዛሬም ለኢትዮጲያ ሆ
ፀጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር ሆ
እንድንታደስ ሆ
በቅን ልቦና ሆ
በጥሩ መንፈስ ሆ
በረከተ ቡሄ ሆ
ለሁላችን ይድረስ ሆ

ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

ዓመት ዓውደ ዓመት ድገምና ዓመት ድገምና
በጋሽዬ ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ያውርድ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገምና ዓመት ድገምና
በእማምዬ ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ይግባ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
ማርና ወተት ድገምና ዓመት ድገምና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገምና ዓመት ድገምና

እንዲሁ እንዳላችሁ በፍቅር
አይለያችሁ በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም በፍቅር
ያድርሳችሁ በፍቅር
ክርስቶስ በቀኙ በፍቅር
ያቁማችሁ በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር
ያድርጋችሁ በፍቅር

እንዲሁ እንዳለን በፍቅር
አይለየን በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም በፍቅር
ያድርሰን በፍቅር
አማኑኤል በቀኙ በፍቅር
ያቁመን በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር
ያድርገን በፍቅር

የቅዱሳን መላክ የፃድቃን ሰማዕታት
እረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
የቅዱሳን መላክ የፃድቃን ሰማዕታት
እረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት
ይግባ በረከት
በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት
ይግባ በረከት

እንዲሁም በሐይማኖት
ፀንተው በፍቃድ
የአስራታችን
በደል የሌለባት
ያቆዩልንን
የአበው ቀሳውስት
ይገባልና
ልንጠብቅ በእውነት
ባህላዊውን የአባቶች ቱውፊት/4/
§usewøchu