Get Mystery Box with random crypto!

ጠላት መጣ ካሉ ሰው የለንም በሉ ‍ …………………… …………………… ከዛ ከሩቅ አድማስ ድንበር | 𝕡𝕒𝕤𝕤𝕔𝕠𝕕𝕖 🤟

ጠላት መጣ ካሉ ሰው የለንም በሉ ‍
…………………… ……………………

ከዛ ከሩቅ አድማስ ድንበርን ተሻግሮ፣
ጠላት ከመጣብን ከስተጀርባ ዞሮ፣
መትረየስ ሳይተኩስ ሰይፉንም ሳይመዘው፣
ሠው የለንም ብለህ ሳይገባ መልሠው።
ለምን ያለህ እንደው አሻፈረኝ ብሎ፣
ልጅዋን ልውሠድ ካለ ከዛች መካን በቅሎ፣
ሳይገባ አፋፉ ላይ ላፉታ አቁመኸው፣
ለዛ እሳት ተፊ ሳብያውን ንገረው።
ድንጉላ የለንም ባዝራችን እርጉዝ ናት፣
ልቶልድ ተቃርባለች እንዳንመጣባት።
ዳሩሥ ፈረሥ ቢኖር መች እንመጣ ነበር፣
ሠው የላት ይች ሀገር።

ጠላት ሳይመጣብን ጠላት ሆነን እኛ፣
ተጋድለን አልቀናል ፈራጅ ሳይኖር ዳኛ።
በገዛ ስጋችን ፎቄውን ሠክተን፣
ባተሌ ሆነናል አንድነትን ትተን።

ጅብራዋ ሀገራችን ሠፊ ቅጠል ያላት፣
ቅጠሏ ረግፎዋል ግንዱ ተንጋሎባት።
አሸን በቁም በልቶት ያ ግንዷም ወድቆዋል ፣
ችብሀነቱን ትቶ አሜካላ ለብሶዋል።
ብለህ ንገራቸው ከድንበር ሣያልፉ፣
ፉቅር እረግጦ ማለፉ ኪሳራነው ትርፉ።
አልሠማ ያለ እንደው ልምጣ ልምጣ ብሎ፣
ታርግዝልኝ ካለ ለማትወልደው በቅሎ፣
የድሮ ማንነቴን ንገርና ሸኘው፣
ያኔ ይፈራናል ቃሌን ተቀበለው።

እሣቱን ጎርሼ እሳት የምተፋ፣
ባተሌ ታታሪ ላገሬ ምለፋ፣
ጠላት ማይበግረኝ በወኔ ሥነሳ፣
ኮሥታራ ደም ያለኝ ግሳቴ ያንበሳ፣
ደሜን ማፈሥላት ሀገር የነበረኝ፣
መሆኔን ንገረው።
ሸኘው ከድንበሩ።
ለምን አትበለኝ፣
ሠው የለንም ዳሩ።

ሀገሬ ባዶ ናት ሠው የላትምና፣
በልመና ሸኘው የመጣውን ጀግና።
እንዲ በለውንና፣
እኛው አሳይተን ያንድነትን ተስፋ፣
ሌሎቹ ወሠዱት እኛ ሥንጋፋ።
አሳይተናቸው የውቀትን መገኛ፣
እነሱ ወሠዱት እኛ ሥንተኛ።
ብቻ ሳናሥበው እንዲ እንዳንቀላፋን፣
እኛ የመሠረትናት ሀገር እንዳጠፋን፣
ዳሩም ለዛ ብለን ጠላት ከሩቅ ገፋን።

እቺን ምሥኪን ሀገር ተዋት ሠው የላትም፣
ጡቷ ደርቆባታል አምጣ ብቶልድም።
ለዚም በዚ ሳብያ፣
ጠላት መጣ ካሉ፣
ሠው የለንም በሉ።

እፁብ ዘመቻ