Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር እና ህይወት

የቴሌግራም ቻናል አርማ sura16722 — ፍቅር እና ህይወት
የቴሌግራም ቻናል አርማ sura16722 — ፍቅር እና ህይወት
የሰርጥ አድራሻ: @sura16722
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 607
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ደና መጣቹ ወደ አስተማሪ ታሪኮች ብዙ ትምህርታዊ ነገሮች አባባሎች ልብ ወለዶች ቀልዶች ዘፈኖች ብዙ ብዙ ይገኙበታል ። እናም ከአነበባቹ በኃላ ከተመቻቹ share ካልተመቻቹ comment አድርጉ ይመቻቹ ። ፈታ በሉ😁😁😁
ግን leave ማለት አይቻልም ከደበራቹ Comment ብቻ እናስተካክላለን ።
ለሰው ለማጋራት
@Sura16722
Call
0988145369
Comment
@Komose22

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 21:49:41 ፅናት

ክፍል

"""""
""""""
፨ፅናትም "አዎ ሙታን ሙታን ነው ያሉት ልክ ነሽ በፀሎቴ ልቤ
ሊፈነዳ ነው ምን ይሻላን ኧረ ወይኔ" አለች። በድንገት 1 ከ
እንቅልፍ የነቃ ድምፅ "ምንድነው?" አለ።ፅናት በድንጋጤ ዘላ
በፀሎት አልጋ ላይ ወጣች። ፅናት ተኝታበት ከነበረበት አልጋ
እግርጌ ሊባኖስ ቀና አለች። ፅናት ደነገጠች "እንዴ ሊቦ አንቺ
አንቺ አንቺ ቆይ የት ነበርሽ? "አለቻት። በፀሎትም ግራ ተጋብታ
"እንዴ ቆይ ምን እየተፈጠረ ነው?" አለች። ሊባኖስ በፅናት ሁኒታ
ግራ ተጋብታ "ሚጢጢዋ ምንድነው የሆንሽው? እየተንቀጠቀጥሽ
እና በፍረሀት አይን እያየሽኝ ያለሽው ቆይ ለምድነው?" አለቻት።
፨በፀሎት የፅናትን እጅ ጥብቅ አድርጋ ይዛዋለች። ሊባኖስ አሁን
ይበልጥ ግራ በተጋባ አስተያየት እያየቻት "በፀሎት አንቺስ
ለምንድነው ቆይ የፅናትን እጅ እንዲ አጥብቀሽ የያሽው?" አለቻት
። በፀሎትም ምንም ሳትል በቶሎ የፅናትን እጅ ለቀቀችው።
ሊባኖስ አሁን ደሞ ወደ ፅናት እያፈጠጠች "ሚጢጢዋ ቆይ ምን
ተፈጥሮ ነው?አለቻት ቀዝቀዝ ለማለት እየሞከረች። ፅናት
በሚንቀጠቀጥ ድምፅ " አይ ከእንቅልፌ ስነሳ አንቺ አጠገቤ
አልነበርሽም ከዛ ከዛ..." እያለች የተሰማትን ስሜት ከፈጠረባት
ጭንቀት ጋር ደምራ ነገርቻት ፅናት ንግግሯን ያቆመችው ሊባኖስን
ሙታን ማን እንደሆኑ በመጠየቅ ነው። ሊባኖስ ግን "አይ አይ
ጆሮዋቹ ነው" በሉ አሁን ተኑ እኔም ልተኛ ብላ ወደ ፅናት እግርጌ
ሄዳ ተኛች።
፨ ፅናትም ረዥም ደቂቆች በፀሎትን አቅፋ ከቆየች በኋላ
ከበፀሎት አልጋ ተነስታ "ሊቦ ትራስ አለሽ?" ብላ ስትሄድ ሊባኖስ
የለችም። ፅናት እየተዝለፈለፈች ወደ በፀሎት አልጋ ሂደች።
በፀሎት ፈዛለች ተቃቅፈው ለሊቱን እንቅልፍ በአይናቸው ሳይከትም
አሳለፉ እና ሊነጋጋ ሲል ሁለቱም እልም ያለ እንቅልፍ እንደተቃቀፉ
ወሰዳቸው።
፨ጠዋት ቀድማ የተነሳችው በፀሎት ነበረች።የቀሰቀሳት
በመስኮቱ በኩል የሚገባው ሀያል የፀሀይ ጨረር ነበር። በፀሎት
ፅናትን "ፅናቴ እህቴ የኔ ንቂ ንቂ ነግቷል" አለቻት። ፅናት አይኗን
እያሻሸች ስትነሳ የተኑበት ክፍል በር በረገግ( ከፈት) ብሏል። ግን
ተነስታ መሬቱን መረገጥም ፈራች። አልጋው ላይ እንዳለች አይኗን
ወደ ጣሪያው እጇቿን ወደ አፎቿ አድርጋ መፀለይ ጀመረች። ፅናት
ስትፀልይ በትንሹም ቢሆን ድምፅ ስለምታወጣ በፀሎት ፅናት
ፀሎት ላይ እንዳለች ተረዳች። በፀሎትም መፀለይ ጀመረች።
ሁለቱም ፀልየው ጨርሰው በዝምታ ቆዩ።
፨ በድንገት በሩ ቧ ብሎ ተከፈተ በፀሎትን ያዳንዋት ስውዬ አባ
በሬሳ ነበሩ። ፅናት ከአልጋው ላይ ተነሳች። በፀሎት ግራ ገብቷት
"ፅናቴ ማነው" አለች። ፅናትም ሀኪምሽ ናቸው አለቻት።" ደና
አደራቹ ፍጥረታት?"አሉ። ማንም መልስ አልስጣቸውም። ይህንን
ያስተዋሉት አባ በሬሳም "ምነው ልሳናቹ ጠፋ ልክ እንደ ሙታን?"
አሉና በፀሎትን ከጭንቅላቷ ብድግ አድርገው ከኪሳቸው የሚቀባ
ነበር አውጥተው ቀብተዋት ወጡ። ፅናትና ትግስት በድንጋጤ
ፈዘዋል።
፨ የአቶ በሬሳ እግር ከክፍሉ እንደወጣ ሊባኖስ መጣች። ደና
አደራቹ አለች ለእሷም መልስ የሰጣት የለም።ፅናት ቅድም
ከቆመችበት አልተነቃነቀችም በፀሎትም አልጋዋ ላይ ፈዛ እና
ደንዝዛ ነው ያለችው። ሊባኖስ " እናተ ልጆች" ስትል ሁለቱም
ደንግጠው ከፍዘታቸው ነቁ። "ሚጢጢዋ በሉ ቶሎ በሉ ወደ ቤታቹ
የመሄጃ ስአት ደረሷል ቁርስ ቤታቹ ትበላላቹ" ብላ ወጣች። ቆየት
ብላ ከአንድ ፈረጣማ ወጣት ጋር የበፀሎትን ዊልቸር ይዘው
መጡና በፀሎት ዊልቸሯ ላይ እንድትሆን እረድተዋት
አስቀመጡዋት። ከዛ ሊባኖስ የበፀሎትን ዊልቸር እየገፋች ከክፍሉ
ወጣችና "ሚጢጢዋ በይ ነይ" አለችና ወደ ፈረጣማው ሰውዬ
ዞራ "ጎረምሳው በል ቶሎ መኪናውን አዘጋጅ" አለችው። እሱም
እሺታውን ገልፆላት ወጣ።
፨ ልጁ እንደወጣ እነሱም ተከተሉት ፅናት ጊቢውን ቃኘችው
አስፈሪ ደባብ አለው። ብዙ ዛፎች መሬት ላይ ደሞ በየመጠኑ ኤሊ
እና ግዙፍ የፎቅ ቤት አለ። ከዛ ጊቢ ሲወጡ ፅናት እና በፀሎት
እፎይይይይይ እስይይይይይ ተመስገን አሉ።
፨ ከዛማ ፅናት እና በፀሎት ወደ ቤታቸው ከሊባኖስ እና ከሹፌሩ
ጋር ሄዱ። ቤታቸው ሲደርሱ ነፃነት ተሰማቸው። ሊባኖስ ነበረች
በፀሎትን እየገፋች ያስገባቻት።ቤት ከገቡ በኋላ ሊባኖስ ሹፌሩን
"ማርቆስ በል ቅድም መኪና ውስጥ ያስቀመጥኩትን አምጣው"
አለችው። ሹፌሩም ምንም መልስ ሳይሰጣት ወጣ። ወዲያው
በፌስታል ያለ ነገር ይዞ መጣ። ሊባኖስ ቁጭ በል ማርቆስ
አለችው። እሱ አሁንም መልስ ሳይሰጣት ቁጭ አለ። የሹፌሩ
ማረቆስ አለመናገር በፀሎት እና ፅናትን ግራ አጋብቷቸዋል።
፨በእዛች ቤት ውስጥ ሊባኖስ ፣ ፅናት እና በፀሎት ሆነው በሳቅ
እና በወሬ ድምቅ አረጉት። ማርቆስም አለ ግን ይስቃል እንጂ
አያወራም ፅናት ማርቆስን ሳታቋርጥ እያየችው ነው። አንዴም
እንኳን ሊያወራ አልቻለም። ፅናት ግራ ተጋብታ ወደ ሊባኖስ ጠጋ
ብላ "ሊቦ ቆይ ሹፌሩ ለምንድነው ምንም ሳያወራ የሚስቀው?"
አለች። ሊባኖስም " ዝም በይ አንቺ ልጅ በኋላ እነግረሻለው
አለቻት። "እሺ ሊቦ አትናደጂ ይቅርታ" አለች ፅናት ፈገግ ብላ
ሊባኖስም "ምንም አደል በቃ እኔ አሁን ልሂድ ማርቆስ በል ተነስ
እንሂድ ፅናቴ ያን ቆጠሮ ያመጣውት ለእናንተ ነው ሙዝ ብርቱካን
እና ብዙ ፍራፍሬ" አለው። ስትላት ፅናት "ውይ ሊቦ ብትነግሬኝ
ጥሩ ነበር እኮ ቀምሳቹ ትሄዱ ነበር" ስትል በፀሎትም "አዎ በቃ
ፅናቴ ቢያስ የሆነ እየሄዱ እሚበሉትን ነገር ስጫቸው" ስትል
ሊባኖስ "አይ አይሆንም በሉ በሉ ደና ዋሉ" ብላ ከማርቆስ ጋር
ሄዱ።
፨ ፅናት ማርቆስን እና ሊባኖስን እስከበር በእግሯ መኪና ውስጥ
ከገቡ በኋላ ደሞ በአይኗ ሸኝታቸው ወደ ደሳሳ ጎጆቸው
ተመለሰች።ቤት ከገባች በኋላ ፅናት ወደ በፀሎት ሄዳ "የእኔ ውድ
እህት እየውልሽ አሁን ሁለታችንም እንቅልፍ ያስፈልገናል በቃ
እንተኛ ለሊቱን ሙሉ ያሳለፍነው በቃ ቆይ ፍራሹ ላይ እንደትሆኒ
ላግዝሽና ፍራሹ ላይ ሁኔ ከዛ እቅፍቅፍ ብለን እንተኛለን" አለች
ፅናት። በፀሎትም "እሺ የእኔ ልዩ ልክ ነሽ በሩን ዝጊውና በቃ
እረፍት እናግ" አለች።ፅናት "እሺ" አለችና በፀሎትን ወደ ፍራሽዋ
እንድትወጣ ከረዳቻት በኋላ አደላድላ አስተኛቻት ከዛም በሩን
ዘግታ መጣችና።
፨ፅናት ፍራሹ ዳር ላይ ቁጭ ብላ "እህቴ በቃ አሁን ሁሉንም
እንረሳውና ጥሩ እንቅልፍ እንተኛ ከባድ ጊዜ ነበር ያሰለፍነው"
አለቻት።በፀሎትም "ልክ ነሽ እህቴ በጣም አስቀያሚ እና አስፈሪ
ነበር በቃ እንተኛ ነይ" አለችና ክንዷን ዘረጋችላት።ፅናት ፈጠን ብላ
የበፀሎትን ክንድ ተንተረሳ ፊቷን ወደ በፀሎት አዙራ ተኛች።
ብድግ ብላ በድጋሜ በፀሎትን አንገቷን ሳመቻት። በፀሎት ፈገግ
ብላ የፅናትን ጭንቅላት ሳመችው ከዛም ፀጉሯን እያሻሸች ቆየች
ከደቂቃዎች በኋላ እልም ያለ እንቅልፍ ወሰዳቸው።

ይቀጥላል
----------------------------------------------

@Sura16722
♡ ㅤ  ❍ㅤ    ⎙ㅤ  ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
----------------------------------------
93 views18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:10:06
★ሰማይነት★

'ፀሀይ ነች ሲሉኝ' ፀሀይ አይደለችም
ብዬ ምክራከር
'ጨረቃ ነች ሲሉኝ' ጨረቃ አይደለችም ብዬ ምመሰክር
'ኮኮብ ነችም' ሲሉኝ ኮኮብ አይደለችም እያልሁ ይምናገር
...ሰማይ መሆንሽን ስለማውቅ ነበር፡፡

ፀ'ሀይ ነች' የሚሉሽ ፀሀይስ እነሱ
'ጨረቃ ነች 'ያሉሽ ጨረቃስ እነሱ
'ኮኮብ ነች' የሚሉሽ ኮኮብስ እነሱ
#ሰማይ ውበትሽ ላይ
በቀን በጨለማ የሚመላለሱ፡፡

@Sura16722
207 views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:15:35 በፀሎቴ አለች።በፀሎትም "ምነው? ፅናቴ" አለች። "የሆነ ነገር ተፈጥሯል"
አለች። በፀሎትም ፍንጥር ብላ ተነስታ "ምን?" አለች። "ሊቦ የለችም" አለች
ፅናት እጆቿን በአፏ ጭና። በፀሎትም "እና ባትኖርስ?" አለቻት "እንዴ የት ሄዳ
ሊሆን ይችላል? ቆይ" አለችና ወደ በፀሎት ጆሮ ጠጋ ብላ "ግን በሩ ከ ውስጥ
ማታ እንደዘጋነው ነው እሺ ወጥታ ይሆናል ግን በየት ወጣች? በበር ከሆነስ በሩን
ከውስጥ ማን ዘጋው"? አለች። አሁን በፀሎትም በጣም መፍራት ጀመርች። ምን
አልባት በእንቅልፍ ልብሽ ከፈተሽላት እረስተሽው ነው ሚሆነው ፅናቴ" አለች
በፀሎት ግራ ቢገባት ከውጭ አንድ ድምፅ ተሰማ ሙታን የት ናቸው የሚል
"ምንድነው የምስማው" አለች በፀሎት ፅናት በተንቀጠቀጠ ድምፅ "እኔ ስልሽ
አሰማኝም እንጂ ይህ ቤት የሆነ ነገር አለው እሺ አሁን ምን ይሻለናን" አለች።
በፀሎት "እኔ አላውቅም" አለች።በድጋሜ ከውጪ ሙታን የት ናቸው አለ በጣም
ቀጭን ድምፅ ጮክ ባለ አንደበት።ፅናት ደርቃ በድን ሆና ቀርች። በፀሎትም
"ሙታን!?" አለች ቃሉን ረገጥ አድርጋ።

ይቀጥላል...
----------------------------------------------
@Sura16722
♡ ㅤ  ❍ㅤ    ⎙ㅤ  ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
----------------------------------------
243 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:15:35 ፅናት

ክፍል
.
፨ ፅናት ወደ በፀሎት ዞራ "ወይኔ ምን ጉድ ነው ምን ይሻናላን" አለች። በፀሎት
ፀጥ አለች። ፅናት ወደ በሩ ተጠግታ አንድ ቀዳዳ አግኝታ አጮለቀች ግቢው
ሙሉ በመብራት ተጥለቅልቆል ከበሩ እራቅ ብላ የምታንኳኳ ሴት አለች። ፅናት
ይህቺን ሴት ከወገቧ በታች ብቻ ነው ማየት የቻለችው። በድጋሜ አንኳኳች ፅናት
ደርቃ ቀርች። ለምን ፈራቻት? አታውቅም።ከዛም ወደኋላ አፈገፈገች ከቆይታዎች
በኋላ ያ የሚያስጨንቅ ድምፅ ጠፋ ፅናት በድጋሚ እየተርበተበተች ወደ በሩ
ማጮለቂያ አጎንብሳ አይኗን ወረወረች።አሁን የግቢው መብራትም ሆነ ማንም
ሰው ሊታያት አልቻለም። የሚያስጨንቀው ድምፅ ግን አሁንም ይሰማ ነበር።
፨በፀሎት ስቅቅ ባለ ድምፅ "ፅናቴ ድምፁ ከየት ነው" አለቻች። ፅናት
"አላውቅም፤ እኔ ምንም አላውቅም፤ እማውቀው እንደፈራሁ ብቻ ነው" አለችና
በፀሎት ያለችበት አልጋ ላይ ወጥታ ቁጥጥ ብላ ቁጭ አለች። የበፀሎት እጆች
እየተንቀጠቀጡ ነው። ይህንን ያስተዋለችው ፅናት በቶሎ የበፀሎትን እጅ
ጭብጥ አርጋ ያዘችው። ከዛም "በፀሎቴ እንፀልይ?" አለቻት። ከተቀመጠችበት
ሳትነሳ እዛው ባለችበት ለመመቻቸት እየሞከረች። በፀሎትም "እሺ እንፀልይ
አዎ መፀለይ አለብን ህልም ቢሆንም እንኳን እንዲያነቃን አምላካችንን እንማፀን
አለች።
፨ፅናት እና በፀሎት እጆቻቸውን ሳያላቅቁ ሁለቱም በእየፊናቸው ለፈጣሪያቸው
ምልጃቸውን ላኩ ከልባቸው ነበር ፍራቻ በወረሰው የውስጥ ነውጥ ውስጥ
በጭንቀት እና በእምነት ውስጥ ሁለቱም ከፈጣሪያቸው ጋር በሀሳብ ተገኛኝተው
እየፀለየዩ ነው።በተመስጦ በመሀል የበሩ መንኳኳት ከተመስጦ ፀሎታቸው
አባነናቸው። ግን አሁንም እራሳቸውን ሰብስበው ፀሎታቸውን ጨረሱ።
፨በሩ መንኳኳቱን አላቋረጠም። ከዛም ሁለቱም በጋራ እና በደከመ ድምፅ ልክ
እንደተመካከረ ሰው "ማነው?" አሉ።" እኔ ነኝ ክፈቱ ምንድነው ተኝታቹ ነው
እንዴ ደሞ ከሆነስ እራት ሳትበሉ እንዴት ትተኛላቹ። በይ ክፈችልኝ ሚጢጢዋ"
አለች ሊባኖስ ነበረች። ፅናት ተስፈንጥራ ተነስታ ምንም ድምፅ ሳታጣ ወደ በሩ
ሄደች። ከዛም በሩን ከፈተችው ሊባኖስ በመቋጠሪያ ሰሀን እራት ይዛ ሰሀሩን
በጥቁር ዳንቴል ሸፍናው ነበር።
፨ፅናት እንድትገባ ወዲያው ከበሩ ገለል ብላ ቆመች ልትገባ ስትል በፈጥነት
ተጠምጦማባት ማልቀስ ጀመረች። ሊባኖስም አቀፈቻት እና "ቆይ ምን
ተፈጠረ?" አለች። ፅናትም ሳግ በተደመረ ድምጿ "እኔ ለእራሱ ምንም
አላውቅም በጣም ጨንቆኛል ሊቦ እባክሽ ይህ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች
ምንድናቸው። ያ ያ ሰውዬ መተው ከሞት እና ከህይወት መካከል ያለችዋን
እህቴን በሰአታት ውስጥ ወደ ጤንነቷ መለስዋት።
፨ ሰለተሻላት እና ደና ስለሆነችልኝ ደስ ቢለኝም ግን የሰውየው ሁኔታ ያስፈራል።
ከዛ ከዛ ከዛ ደሞ ምን እንደተፈጠረ ታውቂያለሽ ከጥቄት ቆይታዎች በፊት እዚህ
በር ላይ ሰው ነበር ተጠጋው እና ወደ በሩ አጮለኩኝ 1ሴት ነበርች ይህቺ ሴት
ደሞ አስጨናቂ እና ሞትን የሚጠራ የሚመስል ድምፅ እያወጣች ነበር።
፨ ከዛ በድጋሜ ቆይቼ ድምፁ ሲጠፋ ወጥቼ ሳይ ምንም ማንም የለም ግን ያ
ድምፅ ነበር። ድምፁ በሩን ስዘጋው አለ በሩን ስከፍተው የለም "። አለችና ፅናት
እንባዋን አዘራችው። ሊባኖስ ምንም ነገር ልትነግራት የምትፈልግ አትመስልም
"በቃ አትጨቁ ነገ ወደ ቤታቹ ትመለሳላቹ በሉ ይህንን ብሉ አለችና መሬቱ ላይ
ቁጥጥ ብላ ተቀምጣ የያዘችውን ሰሀን ፈታችው ከላይ ያለውን እንጀራ አንስታ
የሰሀኑ እፊያ ላይ አረገችው። ፅናት "ምንድነው?"አለቻት። ቅፍፍ እያለች።
፨ሊባኖስም "ነጩ እልበት ነው አረጓዴው ደሞ ሳማ ወጥ"አለቻት። ፅናት
በህይወቷ አንዴም ነጭና አርጓዴ ሽሮ ወጥ መሳይ ምግብ አይታ ስለማታውቅ
ሌላ አለም ውስጥ ያለች መሰላት። ምግብን ከበላች እምትሞት መሰላት። ያ ስለ
ሊባኖስ መጥፎ ነገር ያላት ሰውዬ አስታወሰች ።ቃል በቃል የሰውየው ድምፅ
ጆሮዋ ላይ አቃጨለባት ፅናት መፈራት ጀመረ።" ሊባኖስ ምን አይነት ሰው
ናት?" አለች። ግን መልስ የሚሰጣት የለም። ፅናት በጣም ፈርታለች።
፨በፀሎት ግራ በመጋባት "ምንድነው?"አለች። ሊባኖስም "ሳማ ወጥ እና
እልበት" አለቻት። " ውይ እሱን ነገር ድሮ ቀምሼው ነበር። በጣም ነው
ምወደው" ስትል በፀሎት ፈገግ ብላ 1 ነገር ትዝ ያላት ትመስላለች። " ሳማ
ወጥ ግን አላውቅም" አለች ፅናት ወደ በፀሎት ዞራ እያየቻት "እህቴ
አለቻት"።" ወዬ ፅናቴ" አለች በፀሎት።" ቆይ የት ነው የቀመሽው?" ስትላት።
፨ " ድሮ እማማ ሳይሞቱ በፊት አንቺ ትምህርት ቤት ሆነሽ ሰርተው በልተን
ነበር። ግን በጣም ስለወደድኩት እማማ ላንቺ ብለው ያስቀመጡትን ቀስ
እያልኩ ሳላስበው ጨረስኩት።ከዛ ለእማማ እንዳይነግሩሽ ለምኛቸው እሺ
አሉ"ብላ ሳቀች። ፅናትም "ሆሆ ብላ ሳቀች" ሊባኖስም ከእነሱ ጋር ተደምራ
ቤቱን የሳቅ ድግስ አስመሰሉት።
፨ ከዛም በጋራ እራታቸውን በልተው ሊባኖስ ልትሄድ ስትል ፅናት ፍረሀቷ
ጀመራት። "ሊቦ አትሂጂ ከእኛ ጋር እደሪ እባክሽ" አለቻት ሊባኖስም "እንዴ
ፅናቴ ለምን?" አለቻት። ትግስትም "እሺ በይ እባክሽ በጭንቀት እና በፈረሀት
ከመሞታችን በፊት ስትላት እሺ ጥሩ በሉ እንተኛ እኔ እንቅልፊ በጣም መጥቶል
አለች። ፅናትም ፈገግ ብላ "እሺ እኔና አንቺ አንዱ አልጋ ላይ መተኛት እንችላለን
አለቻት።ሊቦኖስም "እሺ ጥሩ የኔ ሚጢጢ" አለችና ፅናት ተኝታበት የነበረበት
አልጋ ላይ ተኛች።
ፅናት ሁሌም ሊባኖስ ሩቋ ስትሆን ፈረታት አጠገብዋ ስትሆን ለምን መላክ
እንደምትመስላት አይገባትም።
፨ፅናትም ወደ በፀሎት ሄዳ በፀሎትን አልጋ ልብሷን አልብሳት አልጋ ላይ
ወጣች። በድጋሜ ከ አልጋው በመነሳት በሩን ዘጋችው ከዛም ሊባኖስን ስላሉበት
ቤት ኑዋሬዎች እድትነግራት መጨነቅ ጀመረች። ሊባኖስ ግን ምንም ነገር
ልትነግራት ፍቃደኛ አደለችም። "የሰማሽው እንጉርጉሮም በምናብሽ የፈጠርሽው
እንጂ በጭራሽ የእውነት አደለም ወዳላችሁበት ቤትም ማንም አልመጣም"
አለቻት። ፅናት "እሺ እኔስ በምናቤ ፈጥሬው ነው ይባል ግን እህቴ በፀሎቴም
ሰምታለች" ስትላት ሊባኖስ እረብሽብሽ ብላ ፅናትን ተቆጥታ እንድትተኛ
ነገረቻት። በፀሎት "ምንድነው እምትንሾካሾኩት?" ስትል ፅናት አይ ምንም በቃ
ተኑ እንተኛ አለች። በድጋሜ ያላስቻላት ፅናት ብዙ ከራስዋ ጋር ከተከራከረች በኋላ
ወደ ሊባኖስ ጆሮ ጠጋ ብላ "ውሸት ውሸት ነው ሴቲቱንም አይቻታለው አዎ"
አለች። ሊባኖስም "እንዲህ አይነት ሴት እዚህ ጊቢ እንደሊለች ደጋግሜ
ነገረኩሽ ተኚ ስትላት ፅናት መከራከሩ ቢሰለቻት ፀጥ ብላ ጣራ ጣራውን ማየት
ጀመረች።
፨ ሁለት ሀሳብ ያዛት ሊባኖስ ከእነ እህቴ አንድ ነገር ብታረገንስ የሚል እና
መጉዳት ብትፈልግ ለምን እህቴን አዳነቻት የሚሉ ጭንቀቶችን እያስተናገደች
በእዛው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ተመመች። እንቅልፍ የተባለ ደሴት
ውስጥ ከተመች።በፀሎትም እንደዛው ለጥጥጥጥ አሉ።የሆነ ሰአት ላይ እኩለ
ለሊት ሆኖል።
፨ ፅናት ያ የሞት ጣር የሆነ እንጉርጉሮ ጆሮዋ ላይ አቃጨለባት። ብንን አለች ሊባኖስ የለችም በፀሎትም ተኝታለች። ፅናት በቀስታ ወደ በፀሎት ሄዳ "በፀሎት
219 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 09:54:55 ማውራትና መሆን ይለያያል በማውራት ውስጥ ሆኖ መገኘት ትልቅ ውበት ነው
.........እራስህን ሁን ስለራስህ እወቅ ከዛ ውጭ ያለው ትርፍ ነው ..... መንገድህን እንጂ መንገደኞችን አትይ

@Sura16722
252 views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 09:53:26 ስለ ሴት ልጅ ከጠየቁህ እንዲህ በላቸው
እሷ ነብስ እንጂ አካል አይደለችም
አዛኝ እንጂ ደካማ አይደለችም
እውቀት እንጂ ፅልመት አይደለችም
ብርሃን እንጂ ጨለማ አይደለችም
ጥሩ እንጂ ሞኝ አይደለችም
አምላክ ከአዳም አጥንት የሰራት
የሁሉም አዳም አደራ ናት በላቸው

መልካም ቀን...

@Sura16722
249 views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:51:10 ፅናት

ክፍል
.
.
፨ ሹፌሩ በጣም ተደናግጦ የሚያረገው ጠፋው መንደሩን ዞር ዞር ብሎ አየው
በሰአቱ ሰው አደለም ነብስ ያለው ፍጥረትም አልታየውም ከዛም ፅናትን
በጥድፊያ ያ በጣም የሚስፈራት ድባብን የተላበሰ ጊቢ ተሸክሞ ይዟት ገባ።
ሊባኖስ ከእሩቅ አይታው በፍጥነት ሮጣ ወደ ሹፌሩ በመምጣት ተባብረው አንድ
አነስ ያለች የጭቃ ቤት ውስጥ አስገቧት ቤቷ ስትታይ ልትወድቅ ያሰፈሰፈች
ትመስላለች በፈጥነት አንድ የሽቦ አልጋ ላይ አስተኑዋት።
፨ በክፍሉ ውስጥ ፅናት ከተኛችበት ትይዩ ካለው ግድግዳ አጠገብ አንድ
ተጨማሪ የሽቦ አልጋ ይታያል። በእዚህ አልጋ ላይም በፀሎትን በደረቷ
አስተኝተው የጭንቅላቷን ደም ለማስቆም እየጣሩ ያሉ አንድ የእድሜ ባለ ፀጋ
ይታያሉ። እኒ ሰው ፀጉራቸው ሙሉ ሽበት ሲሆን ልክ እንደ ባህታዊ ፀጉረ
ተቆጣጥሮ ወገባቸው ላይ የተንዠረገገ ነው ። ጥቁረ መነፀረ እና የመነቸከ ነጭ
ባረኒጣ አረገዋል። ልብሳቸውም እንደነገሩ ነው ልክ እንደ ኮፍያቸው ነጭ ሆኖ
ነገረ ግን የመነቸከ ሰፋፊ ሹራብ እና ሱሪ አድረገዋል። በጣም አጭረ ቁመት እና
ቀይ መልክን ተላብሰዋል።
፨ የትግስትን የጭንቅላት ደምን በያዙት መጣጭ ጨረቅ ላይ የሆነ ፈሳሽ ውሀ
መስል ነገረ እያረጉ ካፀዱ በኋላ ደሙ ሲቆም አንድ አረጓዴ የተጨቀጨቀ ነገረ
ከብልቃጥ አውጥተው የበፀሎት የተጎዳ ጭንቅት ላይ በዳበሳ አረገው ቀቡትና
በፋሻ ጠቀለሉት። ከዛም ከእሳቸው የማይጠበቅ ጉልበት እና ቅልጥፋና
ተጠቅመው በፀሎትን በእፍታ ፍጥነት በጀረባዋ አስተኙዋት።እኒ ሰው አንድ ሰው
እያከሙ ሳሉ የሚያወራቸን ሰው አጥብቀው የሚጠሉ ናቸው።
፨ ልክ በፀሎትን አክመው እንደጨረሱ ሊባኖስ "አባ በሬሳ የእሷ እህትም
ተጓድታለች እራስዋን ስታ ነው" አለች። ሊባኖስ ፅናት ፅናትን እያየች ምን ሆና?
ለምን እንዲ ሆነች? ብለውም ሳይጠይቁ ወዲያው ከዛች ጭቃ ቤት
ወጡ።ሊባኖስ ፈገግ አለች። አባ በሬሳም አፍታ ሳይቆዩ የፈላ ውሀ
እየተግለበለበ ይዘው መጡ። የፈላ ውሀውን ከመሬቱ ላይ ካስቀመጡ በኋላ
በኪሳቸው የያዙትን በፌስታል የተቋጠረ ቢጫ ዱቄት ሊያረጉ እየፈቱ ሳለ ሊባኖስ
ክፍሉን ለቃ ወጣች እና በሩን ዘጋችው ።
፨አባ በሬሳ ስራቸውን ቀጠሉ። የፈላው ውሀ ላይ ቢጫ ዱቄቱን ሲጨምሩት
ውሀው ይበልጥ መፈላት ጀመረ።ከዛም ቤቱ በእንፋሎት መታጠን ሲጀምረ
እሳቸውም ያቺን የጭቃ ቤት ለቀው ወጡ። ፅናት እና በፀሎትም በጭቃ ቤቷ
ውስጥ የሚሸታቸው ጠረን ሰአታት አስቆጥሮ በእኩል ሰአት አስነቃቸው። ሲነቁ
ደና ሆነው ነበረ። ፅናት ብድግ ብላ ወደ በፀሎት ሄደች።በፀሎት ግራ ገብቶት
"ፅናቴ የት ነው ያስተኛሽኝ ፍራሻችን ዛሬ ደሞ ትንሽ ምቾት አለው። ደሞ
ምንድነው የሚሸተኝ" አለቻት። ፅናት ግራ ተጋባች።
፨ በአይኑዋ የቤቱን ዙሪያ ቃኘችው። የቆመችበት መሬት ያለችበት ቤት የት
እንደሆነ አታውቅም ፈጠን ብላ ወደ በሩ ሆደች። በሩ ከውጪ ተቀረቅሯል። ግራ
ገባት። ወደ እህቷ ሄዳ። እጇን ያዘቻት ፍረሀት ሰውነቷን በሀያሉ ወረራት። ፅናት
ቤቱ ውስጥ ከ ሁለቱ አልጋዎች እና ተንጋላ ከተኛችው በፀሎት እንዲሁም
ከእራሷ ውጪ ምንም ሊታያት አልቻለም ።ፈራች በፈጥነት በፀሎት የተኛችበት
አልጋ ላይ ወጥታ አቀፈቻት። አሁን በፀሎት በተራዋ ግራ ገባት። ልክ የፅናት ግራ
መጋባት ወደ ፍራቻ ሲዞረ።
፨ በፀሎት ፅናትን በዳበሳ እየነካካቻት "ፅናቴ ምነው ዝም አልሽ" አለቻት።
ፅናት በፀሎትን በደንብ እቅፋ እያረገቻት "በፀሎቴ ፈራው" አለቻት በፀሎት
በአሁንም ግራ ገብቷት "እንዴ ለምን አለቻት" ፅናት አሁን በፀሎትን ይበልጥ
እያቀፈቻት። "ቤታችን አደለንም" ስትላት። በፀሎት ፈገግ ግረም እያለች "እና
የት ነን" ስትላት። አላውቅም ብላ ሊባኖስ ቤታቸው ከመጣች ጀምሮ ያለውን
ሁሉ እስከምታስታውሰው እራሷን የሳተችበት ቅፅበት ነገረቻት አሁን በፀሎትም
በጣም ፈራች። እረብሽብሽ አለች።
፨ተቃቅፈው በጭንቀት ሳሉ ያሉበት ክፍል በሩ ቡዋዋዋ ብሎ ተከፈተ ፅናት
ብረግግ ብላ ተነሳችና ቁጭ አለች። በፀሎት የፅናትን እጅ አጥብቃ ያዘቻት።ፅናት
አይኖቿን ወደ በሩ ወረውራ አየች። አባ በሬሳ ነበሩ ወደ እነ ፅናት ጠጋ ማለት
ሲጀምሩ የፅናት ልብ ምት ፈጠነ። ጠጋ አሉ ፅናት ፈራች። አባ በሬሳ "ተነሽ"
አሉዋት ፅናትን።ፅናት በድንጋጤ በረግጋ ከበፀሎት እጇን አላቃ ከአልጋው ወረዳ
ቀጥ ብላ ቆመች።
፨ አባ በሬሳ ወደ በፀሎት በመሄድ የበፀሎትን ሁለት እጆች በመያዝ "ተነሽ"
አሉዋት ቁጣ በተሞላበት ድምፀት በፀሎት ብድግ አለች። ፅናት ግራ ገባት
ከሰአታት በፊት ከጭንቅላቷ ደም በሀያሉ እየፈሰሳት እራሷን እማታውቀው እህቷ
ምንም እንዳልተፈጠረ ብድግ ብላ መነሳቷ። ፅናት የሚሆነውን በአትኩሮት ማየት
ጀመረች። አባ በሬሳ በፀሎትን አልጋው ላይ ቁጭ ካረጉዋት በኋላ በሁለቱ
እጃቸው ጉንጭ እና ጉንጮን ይዘው በሀይል ካወዛወዙዋት በኋላ ልቅቅ
ሲያረጉዋት በፀሎት ወደ ኋላ ወደቀች። ፅናት ጩከቷን አቀለጠችው።
፨ የሚመጣ ሰው ግን አልነበረም አባ በሬሳ "ዝም ብለሽ ተቀመጭ" አሉዋት።
ፅናት መሬቱ ላይ ተቀምጣ የሚሆነውን ማየት ጀመረች። ከጥቂት ቆይታዎች
በኋላ በፀሎት "ፅናቴ እህቴ" ስትላት ሰማች። ፅናት ፈጠን ብላ ወደ እህቷ
አመራች ጋሽ በሬሳም በግረምት በተራቸው ቆመው ሁኔታውን ማየት ጀመሩ።
በፀሎት ያለ ማንም ድጋፈ ተነስታ ቁጭ አለች። ፅናት ህልም ላይ ያለችም
መሰላት ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ባይገባትም እህቷ ስለተሻላት ግን ተደስታለች።
ተቃቅፈው አለቀሱ ረዥም ደቂቃዎች አነቡ።
፨ ጋሸ በሬሳ እረጅና ባንቀጠቀጠው ድምፃቸው "በቃ ተላቀቁ" አሉና
አላቀቋቸው። ጋሽ በሬሳ በፀሎት ጭንቅላት ላይ ያለውን ፋሻ አነሱላት። ከዛ በቃ
"ከእዚህ በኋላ ህመም የለም ህክምናሽን ጨረሰሻል። አሁን ስለመሸ ተኙ ነገ
ጠዋት ቤታቹ ትሄዳለቹ። ልጅ ሊባኖስ የምትመገቡትን ይዛላቹ ትመጣለች" አሉና
ወደ ፅናት ዞር ብለው ልጄ እህትሽን እንድትንቀሳቀስ እረጃት ሲሉ ፅናት "ግን እኮ
እህቴ መሄድ አትችልም በዊልቸረ ነው የምትንቀሳቀሰው" አለች ። አባ በሬሳ
አውቃለው አውቃለው ልጅ ሊባኖስ ነግራኛለች ግን ሰው በእግሩ ብቻ ሳይሆን
በአይምሮም መጓዝ እና መንቀሳቀስ ይችላል አዝናኛት በወሬ ለማት ነው"
ብለው ወጡ።
፨ ፅናት በፍጥነት በሩን ከውስጥ ሸንጉራ በፀሎት ጋረ በመጠጋት የበፀሎትን
ፓንክ ቁረጥ ፀጉር እና ጭንቅላቷን ዳበሰችው ምንም የለም ለምልክትም
የተቀነጠ አንዳች ጠባሳም የለም። ፅናት ግራ ገባት። "በፀሎቴ ጭንቅላትሽ ላይ
ምንም አይነት የቁስል ወይም የጠባሳ ምልክት የለም እሺ ጠባሳው ቆይቶ ነው
ሚመጣው ግን ቁስሉስ" አለች።በፀሎትም "እንዴት ሆኖ ቆይ የት ነን?"
ስትልላት።"አላውቅም ሽማግሌው እኮ እህትሽ እንድትቀሳቀስ እረጃት ሲሉኝ
መቼም በአንድ ጊዜ እንዲ ጤነኛ ካረጉሽ መራመድም እንድትችይ ያረጉሽ
መስሎኝ በጣም ልቤ በደስታ እየመታ ነበር"አለች እንዲ እያወሩ በሩ ተንኳኳ
ፅናት ማነው አለች። መልስ የለም ግን የሆነ የሚያስጨንቅ እንጉረጉሮ ይሰማታል
ሁለቱም ፋረሀት ወረራቸው።

ይቀጥላል...

@Sura16722
♡ ㅤ  ❍ㅤ    ⎙ㅤ  ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
----------------------------------------
278 viewsedited  18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:32:07 ​ "ጥቅስ".

1) ብቸኛው ጥሩ ነገር ማወቅ ሲሆን፤ብቸኛው መጥፎ ነገር ደግሞ መሃይምነት ነው።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

"ልብ እየጠበበ ጨጓራ ሲሰፋ
ታዋቂ ሰው በዝቶ አዋቂ ሰው ጠፋ!!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

"ድህነት ይገልበጥ ባፍጢሙ ይደፋ
ድሃ ግን ይበርክት ፍቅር እንዳይጠፋ!!
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

@Sura16722
285 views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:30:00 ​​ወንድ ሆይ ሴት ልጅ ካንተ ምን ትፈልጋለች :-

➊ ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት ፡፡

➋ ሴት ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች ። (ባገኘከው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል።

➌ ሴቶች ግትር ወንዶችን
ይጠላሉ። ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ፡፡ አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር።

➍ ሴቶችን መልካም ንግግር፡ ውብ ገጽታ፡ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም ነገሮች እንዲኖሩህ ጥረት አድርግ።

➎ ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው። ቤቷ ስትሆን ዙፋኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል። በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር እንዳትፈጽም። ከንግስና ዙፋኗ ላይ ልታወርዳትም አትሞክር። ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ።

➏ ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም።
አንተን ከቤተሰቦቿ በላይ እንድትወድህ
ለማድረግ አትጣር። ይህን ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል።

➐ ሴት ከጎንህ (ጠማማ አጥንት) መፈጠሯን አትዘንጋ። ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን እወቅ። ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለሁ እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ። ስብራቷ ፍቺ ነው።ልታቃናት ከሞከርክ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት። መካከለኛ ሰው ሁንላት።

➑ ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋትችላለች። (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ነገር ግን እንዲህ አደረገች በማለት ብቻ እንዳትጠላት። ይህን
ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚስቡህ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ ።

➒ ሴት አካላዊ ድካምና ስነልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል። SO ትእዛዝ አታብዛባት።

➓ ሴት አንተ ዘንድ ያለች (የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን
አትዘንጋ። ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት፡ እዘንላት፡ በድክመቷ (የምትፈጽመውን ስህተት) እለፋት። ምርጥ የሂዎት አጋርህ
ትሆናለች።

መልካም ቀን

@Sura16722
273 views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:00:10 ብቸኝነቴን እኔ
እኔ ማስታውሰው
አልጀመሩኩም ነበር
ፍቅር ከሌላ ሰው
ዛሬ ተረታውኝ
ድንገት ሳላስበው


@Sura16722
281 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ